አመድ በርአሞራ ገደል እና ደብረ ታቦር መካከል የምትገኝ በፎገራ ወረዳ ስር ያለች ትንሽ ከተማ ናት። አመድ በር ውስጥ፣ እንደ 2005 ህዝብ ቆጠራ፣ 5፣ 517 ሰዎች ይኖራሉ። [1]

አመድ በር
ከፍታ 2691 ሜ
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 5517
አመድ በር is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አመድ በር

11°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°53′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ታሪክ ለማስተካከል

እቴጌ ሰብለ ወንጌል 1560 ዓ.ም. አመድ በር ላይ እንዳረፈች ይጠቀሳል። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ነገሥታቱ ክረምትን በ አመድ በርና በአካባቢው በሚገኙት አሪንጎቃሮዳ ያሳልፉ እንደንበር ዜና መዋዕላቸው ያትታል። ይሄውም እንደይባባአይባእንፍራዝጣዳወይናረብመንዘሮ ወዘተ መሆኑ ነው [2][3]። ሐዋርያ የተሰኘው የአምባሰል መሪ በዣንጥራር ተስፋ እየሱስ ተይዞ እንዲመጣ ታላቁ እያሱ የላከው ከዚሁ ከአመድ በር ነበር [4]

በ1769ዓ.ም. ራስ አሊ] የሚመራው ከላስታአምባሰልዋግ የተሰባሰበ የየጁ ፈረሰኛ በአንድ ጎን፣ በወልደ ገብርኤል የሚመራው መድፍጠመንጃ የታጠቀ ከሰሜንደምበያትግሬጎጃም የተሰባሰበ የክርስቲያን ክፍል በሌላ ጎን፣ ከፍተኛ ጦርነት አድርገው የጁዎች ጦርነቱን ያሸነፉበት ቦታ ነው። ይህ የአመድ በር ጦርነት ሽንፈት በጎንደር ከተማ ስር እየሰደደ የነበረው ስልጣኔ በዘመኑ የአውሮጳውያን ስልጣኔ መስፋፋት አይነት በተለያየ አገሪቱ ክፍል እንዳይሰራጭ ያቀጨጨው አንድ ትልቅ እንቅፋት እንደነበር በታሪክ አጥኝወች ዘንድ ይጠቀሳል [5]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ CSA 2005 National Statistics Archived ኦገስት 13, 2007 at the Wayback Machine, Table B.3
  2. ^ Stuart Munro-hay, Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide, I.B. Tauris, ገጽ 78 (2002)
  3. ^ George Wynn Brereton Huntingford, Richard Pankhurst,The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, British Academy by the Oxford University Press,ገጽ 197 (1989)
  4. ^ Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium: Scriptores aethiopica By Catholic University of Louvain (1835-1969), Catholic University of America፣ ገጽ 58
  5. ^ Jeremy Black, Kings, nobles and commoners: states and societies in early modern Europe, a revisionist history, I.B. Tauris, page 180 (2004)