«ጊንጥ» (አጠራሩ በግብጽኛ ምናልባት «ሠልክ» ነው) ከግብጽ ቀድሞ ዘመነ መንግሥት ወቅት በፊት በሆነው ጊዜ የነበረ ንጉሥ። ከናርመር ትንሽ አስቀድሞ ሲገዛ በመላው አገሩ ላይ እንደ ገዛ ግን አይመስልም። ብዙ የተበለጠ መረጃ የጊንጥ ዱላ በተባለው ቅርስ ላይ ይገኛል።

የንጉሥ ጊንጥ ቅርጽ በጊንጥ ዱላ ላይ።

አቢዶስ ከተማ፣ «ንጉሥ ጊንጥ» የተባለው ሰው መቃብር ለሥነ ቅርስ ይታወቃል። ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ፣ ይህ ግለሠብ ሌላ ንጉሥ ጊንጥ ይሆናል።