ቻርለስ ኢዘንበርግ, (እ.ኤ.አ. መስከረም 5, 1806 ስቱትጋርት -- ጥቅምት 10, 1864) የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ቄስ የነበረና ባለፈው ዘመኑ የቆርቆሮ ብረት አንጥረኛ የነበር ሰው ነው። ቄስ በነበረበት ዘመኑ ወደ ኢትዮጵያ እና ህንድ የተላከ ሚሲዮናዊ ሲሆን ይሄውም (እ.ኤ.አ) ከ1832-1864 መሆኑ ነው[1]። ኢዘንበርግ፣ ከ'34-38 በአድዋ ትግራይ የኖረ ሲሆን ከአካባቢው ቀሳውስት ጋር መግባባት ስላላሰየ ሊባረር በቅቷል። በሚቀጥለው አመት፣ 1839፣ በሸዋው ንጉስ ሣህለ ሥላሴ ግብዣ እርሱና ሌሎች ሁለት ሚስዮኖች ሸዋ ሄዱ። ከ4 ወር ቆይታ በኋላ ኢዘንበርግ ወደ ለንደን እንግሊዝ ተመልሶ ሄደ።

በለንደን ቆይታው ብዙ መጻህፍትን በአማርኛ ና ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አሳትሟል። እነርሱም አፋርኛኦሮምኛ (ከሉድቪግ ክራፍ የተወሰደ) እና አማርኛ መዝገበ ቃላት (1840-42)፣ የአማርኛ ሰዋሰው፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ጂዎግራፊ፣ እና የዓለም ታሪክን ያቅፋሉ።

ኢዘንበርግ በ1842 እንደገና ወደ ሸዋ ለመመለስ ሞክሮ ነበር፤ ሆኖም ግን ፍቃድ ስለተከለከለ ወደ ትግራይ በማምራት በዚያ እስከ 1843 ተቀመጠ። ደጃዝማች ውቤ በዚሁ አመት ከትግራይ ስለአባረሩት ወደ ለንደን አመራ። በ1844 የአቡ ሩሚን የቆየ አማርኛ መጽሓፍ ቅዱስ ትርጓሜ በማረም ከክራፕፍ ጋር አሳተሙ። በዚያው አመት አራቱን ወንጌሎችትግርኛ ቋንቋ ሊያሳትም በቃ። ይህ የትግርኛ መጽሀፍ ቅዱስ በበርሊንጀርመን ይገኛል።

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ H. Gundert Biography of the Rev. Charles Isenberg, Missionary of the Church Missionary Society to Abyssinia and Western India from 1832 to 1864 (1885).