ትግራይ ከ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪዓዲ ፣ዓድዋ፣ ነበለት፣ ሸራሮ፣ዓዲግራት፣ አኽሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ማይጨው፣ ናቸው። የሕዝብ ብዛት በ1999 ህዝብ እና ቤት ቆጠራ መሰረት 7.9 ሚልዮን ነው። ትግርኛ የክልሉ ዋና ቋንቋ ነው። እምባ ኣላጀ፣ ፅበት እና ወርሐት በትግራይ ሀገር ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ናቸው። ትግራይ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሃብቶች የታደለ ሀገር ነው። የ2000 ዓመት የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የ1500 ዓመት የአክሱም ጥንታዊ ሃውልቶች፣ከ4ኛው እስከ 18ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ሀገር ነው። ትግራይን በባህልና በታሪካዊ ኣመጣጥ ከኤርትራ ነጥሎ ማየት ኣይቻለም። ከኣምሓራ ቀጥሎ የዳኣማትና የአክሱም ግእዛዊ ሥልጣኔ ባለቤት ናት። ዓድዋ

ትግራይ
ክልል
የትግራይ ሀገርን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ
አገር ትግራይ
ርዕሰ ከተማ መቐለ
የቦታ ስፋት
   • አጠቃላይ 50,286[1]
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 9,201,000[1]
  1. ^ "፳፻፬ ዓ.ም. የትግራይ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ". የትግራይ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ. Archived from the original on 2015-09-23. በሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተወሰደ.