ትሬቤታጌስታ ትሬቬሮሩም ዘንድ የትሪር ከተማ (በአሁኑ ጀርመን) አፈታሪዊ መስራች ነበር። የአሦር ንጉሥ ኒኑስ ልጅ እንደ ነበር ኒኑስ ንግሥቱን ሴሚራሚስን ሳያግባ በሆነችው ሚሥት እንደ ተወለደ ተጻፈ። የአባቱ ንግሥት ሴሚራሚስ ጠላችውና በኋላ መንግሥቱን በያዘች ጊዜ ትሬቤታ ከአሦር ወጥቶ ወደ አውሮጳ ሔደ። ከጊዜ በኋላ ከሠፈረኞች ጋር በትሪር ተቀመጠ።

በ1550 ዓ.ም. የተሳለ የትሬቤታ ስዕል፤ ይህ ስዕል በ2ኛው የአለም ጦርነት ጠፋ።

ዮሐንስ አቬንቲኑስ እንደ ጻፈው ግን ትሬቤታ (ትራይበር ወይም ትሬቬር) የኒኑስ ልጅ ሳይሆን በእውነት የጀርመን 2ኛው ንጉሥ የማኑስ ልጅ ነበረ። አቬንቲኑስ እንዳለው ይህ ትሬቤታ ደግሞ ከተሞች በመትዝስትራዝቡርግ (አሁን በፈረንሳይ)፣ ማይንጽስፓየርቩርምዝ (በጀርመን) እና ባዝል (በስዊስ) መሠረተ። ይህ ምናልባት 2213 ዓክልበ. ግድም ይሆን ነበር።