ሲክዮን (ግሪክ፦ Σικυών /ሲኩዎን/) የጥንታዊ ግሪክ ከተማ ነበረ።

የሲክዮን ሥፍራ በግሪክ

በግሪኮች ልማድ፣ ሲክዮን ከሁሉ አስቀድሞ በግሪክ የተሰፈረው ቦታ ነበር። መጀመርያ ንጉሣቸው አይጊያሌዎስ ሲሆን በርሱ ስም ፐሎፖኔሱስ መጀመርያ «አይጊያሌያ» እንደ ተባለ በግሪክ ታሪክ ጸሐፊዎች ተጻፈ።