ሱሙኤል ከ1806 እስከ 1776 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ ፫ኛ ንጉሥ ነበረ። የአቢሳሬ ተከታይ ነበር። ስሙ «ሱሙኤል» በአካድኛ «የአምላክ ስም» ማለት ነው። የሱሙኤል አባት ስም አይታወቅም።

ኡር ደግሞ በግዛቱ ውስጥ ነበረችና የሱሙኤል ማዕረግ በይፋ «የኡር ንጉሥ» ነበር። በዘመኑ መጨረሻ (ከ1780 ጀምሮ) ኒፑር ደግሞ ወደ ላርሳ ስለ ተመለሰ «የሱመርና የአካድ ንጉሥ» የሚለውን ማዕረግ ወሰደ።

ለዘመኑ ከ፳፱ ወይም ፴ የዓመት ስሞቹ ሁላቸው በሙሉ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦

1803 ዓክልበ. ግ. - «አኩሱም የጠፋበት፣ የካዛሉም ሥራዊት በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
1802 ዓክልበ. ግ. - «የኡሩክ ሥራዊት በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
1799 ዓክልበ. ግ. - «በወንዞች አፍ (ወይም በጤግሮስኤፍራጥስ ምንጭ፣ «ፒ-ናራታይም») የተገኘውን ከተማ ካይዳ የጠፋበት ዓመት»
1797 ዓክልበ. ግ. - «ሳቡምና በኤፍራጥስ ዳርቻ ያሉት ትንንሽ መንደሮች የተያዙበት ዓመት»
1796 ዓክልበ. ግ. - «የኪሽ ሥራዊት በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
1792 ዓክልበ. ግ. - «ንጉሥ ሱሙኤል በመሣርያዎቹ የካዛሉን ሥራዊትና ንጉሡን ያሸነፈበት ዓመት»
1791 ዓክልበ. ግ. - «ሱሙኤል መንደሩን ናና-ኢሻ የያዘበት ዓመት»
1777 ዓክልበ ግ.? - «ኡማ የጠፋበት ዓመት»

የሱሙኤል ተከታይ ኑር-አዳድ ነበረ፤ የኑር-አዳድም አባት ስም አይታወቅም።

ቀዳሚው
አቢሳሬ
ላርሳ ንጉሥ
1806-1776 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኑር-አዳድ

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል