ሰውሃን ወይም ዉሰውሃን (ኮሪይኛ፦ 서한) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን ሃንዩል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።

በጠቅላላ ለ፰ ዓመታት (ምናልባት 1778-1770 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ አሱል ተከተለው።

1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ሰውሃን ካደረጋቸው ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦

  • 1777 ዓክልበ. ግ. - 5% የግቢ ግብር በጆሰን ተመሠረተ።
  • 1776 ዓክልበ. ግ. - የበለጠ ምርጥ፤ የአንድ ሩዝ ተክል ፰ ቅንጣት ሰጠ።
  • 1774 ዓክልበ. ግ. - ሰውሃን ራሱን እንደ ተራ ሰው አስመስሎ በሥያ አገር (ቻይና) ሰለየ። ከዚያ በኋላ የመንግሥት አደረጃጀቱን አስተካከለ።
  • 1771 ዓክልበ. ግ. - ሦስት እግሮች ያሉት ቁራ በቤተ መንግሥት አጸድ ቦታ ወረደ። የክንፉ ርዝመት ፩ ሜትር ያህል ነበር።
  • 1770 ዓክልበ. ግ. - ዳንጉን ሰውሃን ዓረፈ፤ አልጋ ወራሽ ልዑል አሱልም የጆሰን ዳንጉን ሆነ።
ቀዳሚው
ሃንዩል
ጆሰን ዳንጉን
1778-1770 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አሱል

ዋቢ ምንጭ ለማስተካከል