ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1646-1643 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲ
ጀሁቲ ያለበት ድንጋይ
ጀሁቲ ያለበት ድንጋይ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1646-1643 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰኸቀንሬ ?
ተከታይ 8 ሶበክሆተፕ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

ስሙ «ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲ» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ብቻ ነው።

  • 1) የታችኛ ግብጽ ዘውድ ለብሶ የሚያሳይ ድንጋይ ክፍል አለ። ከዚህና ከስሙ «-ታዊ» በታችኛ ግብጽ ላይ ይግባኝ እንደ ጣለ ሊገመት ይችላል። ሆኖም ይህ በሂክሶስ ዘመን ስለ ነበር፣ እንዲሁም አቢዶስአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ስለሚታሰብ፣ ጀሁቲ በእውነት በታችኛ ግብጽ ላይ እንደ ገዛ አይታሰብም።
  • 2) አንድ ሌላ ስሙ የተቀረጸበት ድንጋይ
  • 3) የሚስቱ ንግሥት መንቱሆተፕ ኮስሞቲክ ሳጥን በመቃበርዋ ሲገኝ ስሙ ተገኘበት።
  • 4) በካርናክ ፈርዖኖች ዝርዝር ላይ «ሰኸምሬ ሰመንታዊ» የሚባል ፈርዖን ይዘረዘራል። ይህ ሰነድ ግን ምንም ቅድም-ተከተል አይጠብቅም።
  • 5) በቶሪኖ ቀኖና ላይ በአንድ ክፍል «ሰኸምሬ ፫ አመት፣ ሰኸምሬ ፲፮ አመት፣ ሰኸምሬ... ፩ አመት» ሲል ይህ ክፍል ባብዛኛው የ16ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ሆነ ይታመናል። መጀመርያው የተዘረዘረው ሰኸምሬ ጀሁቲ እንደ ነበር ይገመታል።


ቀዳሚው
ሰኸቀንሬ ?
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1646-1643 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
8 ሶበክሆተፕ