ሥያው ጅያ (ቻይንኛ፦ 小甲) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል ዘንድ ለ17 ዓመት ነገሠ። በአንዱ ምዕራፍ የሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችታይ ገንግ ልጅ ይለዋል፤ በሌላ ቦታ የታይ ገንግ ወንድም ነው ይላል። ተከታዩም የታይ ገንግ ልጅ ዮንግ ጂ ነበር በማለት ይስማማሉ።

በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ደግሞ የታይ ገንግ ወንድም ያደርጉታል፣ ዮንግ ጂንም ከወንድሙ ታይ ዉ በኋላ ያደርጉታል። ታይ ዉ ግን 75 ዓመት ገዛ ሲባል ወንድሙ እንደ ተከተለው የማይመስል ነው።

ቀዳሚው
ታይ ገንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1537-1520 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዮንግ ጂ