ማልኮም ኤክስ (Malcolm X 1917-1957 ዓም) በአሜሪካ አገር ታዋቂ የብሔራዊ መብቶች እንቅስቃሴ መሪ ነበር። ማልኮም ኤክስ (የትውልድ ስሙ ማልኮም ሊትል፣ በኋላ ኤል-ሀጅ ማሊክ ኤል-ሻባዝ፣ ግንቦት 19፣ 1925 የተወለደ - ፌብሩዋሪ 21፣ 1965 በሞት ተለየ) በሲቪል መብቶች ንቅናቄ ወቅት ታዋቂ ሰው የነበረ አሜሪካዊ የሙስሊም ሚሲዮን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነበር። እ.ኤ.አ. እስከ 1964 ድረስ “የኔሽን ኦፍ ኢስላም ቃል አቀባይ”፣ የጥቁር አሜሪካውያን መብት ተሟጋች እና እስልምናን በአሜሪካ የጥቁር ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ከፍተኛ አስተዋጸኦ በማድረግ የሚታወቅ ሰው ነበር።

ማልኮም ኤክስ
ማልኮም ኤክስ በ1964 ዓም
ማልኮም ኤክስ በ1964 ዓም
ባለቤት ቤቲ ኤክስ
ልጆች 6 ልጆች
አታላህ ሻባዝ
ቃቢላ ሻባዝ
ኢልያስ ሻባዝ
ሙሉ ስም ኤል-ሀጅ ማሊክ ኤል-ሻባዝ
የተወለዱት ኦማሃ ኔብራስካ፣ ሰሜን አሜሪካ
የሞቱት ኒው ዮርክ፣ ሰሜን አሜሪካ
የተቀበሩት ፌርን ክሊፍ የመቃብር ቦታ
ፊርማ የ{መለጠፊያ:ስም ፊርማ
ሀይማኖት እስልምና

በመጀመርያ በአንድ አነስተኛ ክፍልፋይ «ኔሽን ኦፍ ኢስላም» («የእስልምና ብሔር») ውስጥ አባል ሆነና የልደቱን ስም ማልኮም ሊተል የባርያ ፈንጋይ ቤተሠብ ስም ብሎት ወደ «ማልኮም ኤክስ» ቀየረው። ክፍልፋዩ «ኔሽን ኦፍ ኢስላም» ቢባልም፣ ትምህርቱ ግን እንደ እስልምና በፍጹም አይመስልም። መሪያቸው ስለ መሥራቹ አምልኮት ይሰብክ ነበርና ነጮች ሁሉ አጋንንት እንደ ነበሩ ያስተምር ነበር። ከጊዜ በኋላ ማልኮም ኤክስ ሀሣቡን ቀይሮ ከ«ኔሽን ኦፍ ኢስላም» ለቅቆ ወጣ፣ እምነቱም ወደ ሱኒ እስልምና ቀየረ። የሌሎችን ሰብአዊ መብት ለመከልከል ያሠበው ሁሉ ማናቸውም ዘር ቢሆን እሱ ጋኔኑ ነው ብሎ ያስተምር ጀመር። በዚህም ውቅት ወደ መካና ወደ አፍሪካም ጎብኞ ነበር።

ሕይወት ለማስተካከል

ማልኮም የጉርምስና ዘመኑን ያሳለፈው አባቱ ከሞተ እና እናቱ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በተከታታይ በማደጎ ቤቶች ውስጥ ወይም ከዘመዶቹ ጋር ነው። እኤአ በ 1946 በድብደባ እና በሌብነት ወንጀል ተከሶ ከ8 እስከ 10 አመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። በእስር ቤት ውስጥ ሳለ ኔሽን ኦፍ ኢስላም የተባልውን እንቅስቃሴ የተቀላቀለ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሊትል የሚለውን የቀድሞ ስሙን በመቀየር ማልኮም ኤክስ በሚል መጠሪያ ተክቶታል። ይህንንም የስም ለውጥ ያደረገው የቀድሞ ስሙ(የቤተሰብ ስም) የነጭ ባርያ አሳዳሪ ስም ስለነበር ነው። እኤአ ከ 1952 ዓም በአመክሮ ከእስር ከተፈታ በኋላ፣ የኔሽን ኦፍ ኢስላም ተፅእኖ ፈጣሪ አመራር ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው። በዚህም ድርጅት ውስጥ ለ12 ዓመታት የጥቁሮች ተሰሚነት እንዲጭምር ይሟገት የነበረ ሲሆን፣ በተጨማሪም ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች የተለየ የራሳቸው ሀገር እንዲኖራቸው ይፈልግ ይቀሰቅስ ነበር። እነ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን እና ታዋቂ የሲቪል መብት እንቅስቃሴውችን በመተቸትም ይታወቃል። ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም በማለት እንዲሁም የጥቁር እና ነጮችን በአንድ ላይ ተቀላቅሎ መኖርን በመኮነንም ይታወቃል። በኋላም እኤአ ከ1950ቹ ዓም የአሜሪካው ፖሊስ ተቋም ኤፍቢአይ ክትትል ያደርግበት ጀመር።

ለሃጅ ወደ መካ ሄዶ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ኤል ሃጅ ማሊክ ኤል ሻባዝ የተባለ ሲሆን፣ በቀጣዮቹም አመታት ወደ ሱኒ እስልምና አማኝነቱ እና የሲቪል መብቶች ንቅናቄ እንቅስቃሴ ላይ ትኩረቱን ያደርግ ጀመር። በ1960ዎቹ ማልኮም ኤክስ በኔሽን ኦፍ ኢስላም እንዲሁም በመሪው ኤሊጃህ ሞሀመድ ላይ ያለው ጥርጣሬ እየጨመረ መጣ። ባተለይ ለአጭር ጊዜ ያክል አፍሪካን ጎብኝቶ ከተመለሰ በኋላ፣ ኔሽኝ ኦፍ ኢስላምን በግልጽ መኮነን የጀመረ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ሙስሊም ሞስክ ኤኤንሲ እና ፓን አፍሪካን ኦርጋናይዜሽን ኦፍ አፍሪካን ዮኒቲን አቋቋመ። እኤአ 1964 ዓም ከኔሽኝ ኦፍ ኢስላም ጋር ያለው ግጭት እና ቅራኔ እየተጋጋለ የመጣበት ጌዜ ሲሆን፣ አንዳንዴም የግድያ ዛቻ ይደርሰው ጀመር። በመሆኑም ይህ የግድያ ዛቻ እውነት ሆኖ እኤአ በ1965 ዓም፣ ፌብራሪ 21 በኒውዮርክ ከተማ በሰው እጅ ህይወቱን ሊያጣ ችሏል። ከግድያው ጋር ተያይዞ ሶስት የኔሽን ኦፍ ኢስላም ሰዎች ገዳይ ተብልው እድሜ ይፍታህ የተፈረደባቸው ቢሆንም እኤአ በ 2021 ዓም ሁለቱ ከእስር ተለቅቀዋል። ይሁንና እስካሁን ድረስ ግድያው እና ስለ ገዳዮቹ ማንነት ብዙዎች የተለያየ መላምት (ጥርጣሬ) ይሰነዝራሉ። በተለይ ሌሎች (ተጨማሪ) የኔሽን ኦፍ ኢስላም አባላት ወይም አመራሮች ግድያው ላይ እጃቸው ሳይኖርበት አይቅርም የሚል ጥርጣሬ አለ። ህግ አስክባሪ ተቋማትም በግድያው አቀነባባሪነት እስካሁን ድረስ በተለያዩ ወገኖች ይወነጀላሉ።

ማልኮም ኤክስ ዘረኝነትን እና ነውጠኝነትን በመስበክ የሚከሱት ጥቂት ባይባሉም፣ በጥቁር አሜሪካውያን እና ሙስሊም አሜሪካውያን ዘንድ ግን የነገድ (ዘር) ፍትሃዊነት አቀንቃኝ ተድርጎ ይታያል። አድናቂዎቹ የማልኮም ኤክስ ቀንን በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች እና ከትሞች በየአመቱ አስበውት ይውላሉ። በሰሜን አሜሪካ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች እና መንገዶች በስሙ የተሰየሙ ሲሆን፣ ህይወቱ ያልፈበት ስፍራ ላይም በእርሱ እና በዶክተር ቤቲ ሻባዝ ስም ማስታወሻ የሚሆን የእውቀት ማዕከል ተገንብቶበታል።

የመጀመሪያዎቹ አመታት ለማስተካከል

ማልኮም ኤክስ እኤአ በ ሜይ 19፣1925 ዓም በኦማሃ፣ ኔብራስካ ግዛት፣ በ ግሪናዳ ተወላጅ ከሆኑት እናቱ ሉሲ ሄለን ሊትል እና የጆርጅያ ተውላጅ አባቱ ኢርል ሊትል፣ ከሰባት ልጆች መካከል አራተኛ ሆኖ ተወለደ። አባቱ ኢርል ደፋር እና የንግግር ችሎታ ያለው ሲሆን፣ እሱ እና ባለቤቱ ሉሲ የፓን አፍሪካን አቀንቃኝ የሆነው ማርክስ ጋርቬይ ተከታዮች (አድናቂ) ነበሩ። ኢርል በአካባቢው ለሚገኝ የጥቁሮች ንቅናቄ ድርጅት ውስጥ መሪ የነበረ ሲሆን፣ ሉሲ ደግሞ የጽሁፍ ችሎታ የነበራት እና በጥቁሮች እንቅስቃሴ ላይ ለሚዘግበው ኔግሮ ወርልድ ለተባለ ጋዜጣ ዜናዎችን አዘጋጅታ ትልክ ነበር። ይህም ተግባራቸው በልጆቻችው ላይ በራስ መተማምንን እና በጥቁርነት መኩራትን እንዲያሰርጹ ረድቶአቸዋል ማለት ይቻላል። ማልኮም ኤክስ በኋላ እንደተናግረው ከሆነ፣ የነጭ አክራሪዎች አራቱን የአባቱን ወንድሞች ገድለውበታል።

የሰሜን አሜሪካ የነጭ አክራሪዎች (Ku Klux Klan) በቤተስቡ ላይ ተደጋጋሚ ማስፍራሪያ ስለሰነዘሩ፣ የማልኮም ኤክስ ቤተሰቦች በ1926 መጀመሪያ ወደ ሚላዎኪ፣ በዙም ሳይቆዩ ወደ ላንሲንግ፣ ሚቺጋን ግዛት መኖሪያቸውን አደረጉ። በዚያም ሳሉ እኤአ በ1929 ዓም ብላክ ሌጊዎን በተባለ የነጭ አክራሪ ቡድን ተድጋጋሚ ጥቃት በቤተሰቡ ላይ ይደርስ ነበር።

ማልኮም ኤክስ ስድስት ዓመት ሲሞላው አባቱ በመኪና አደጋ ሞተ ተባለ። አሟሟቱ በመኪና አድጋ ይባል እንጂ እናቱ ሉሲ ግን ብላክ ሌጊዎን የተባሉት የነጭ አክራሪ ቡድን አባላት ሳይገደል እንዳልቀረ ታምናለች። የነጭ አክራሪዎች አባቱን እንደገደሉ በሰፊው መወራቱ ለማልኮም ኤክስ የልጅነት አእምሮ በጣም የሚረብሽ ጉዳይ የነበረ ሲሆን፣ ማልኮም ኤክስ ጉልማሳ ከሆነ በኋላ ስለጉዳዩ እርስ በእርሱ የሚጋጭ አመልካከት እንደነበረው ገልጿል።

በ1930ዎቹ ሉሲ እና አንድ ወንድ ልጇ በነጮች የባፕቲስት ቤተክርስቲያን የተጠመቁ ሲሆን፣ ማልኮም "አድቬንቲስቶችን እስከ አሁን በህይወቴ ካየኋቸው ነጮች በጣም ጥሩዎች" ሲል ይገልጻቸዋል።

እኤአ በ1937 ዓም እናቱ ሉሲ ከሌላ ስው ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ወደ ፍቅራቸውም ወድ ትዳር እያመራ ሲባል፣ ፍቅረኛዋ ግን ማርገዟን ሲያውቅ ጥሏት ጠፋ። እኤአ በ1938 ዓም መጨረሻ አካባቢ፣ እናቱ ሉሲ የአእምሮ እክል ስለገጠማት ወደ ሆስፒታል ገባች። በመሆኑም ልጆቿ ወደ ተለያዩ የህጻናት ማሳደጊያ ተላኩ። ማልኮም ኤክስ እና ቤተሰቡ እናታቸውን ከ 24 ዓመታት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ እንድትወጣ አድርገዋል።

 
ማልኮም ኤክስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ 1944 ዓም

ማልኮም የመጀመሪያ ደረጃ እና በኋላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በ ማሶን ሚቺጋን የተከታተለ ሲሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሳይመረቅ በፊት በ 1941 ትምህርቱን ሊያቋርጥ ችሏል። በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱ ስኬታማ የነበረ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ ወቅት ህግ ለማጥናት ፍላጎት ቢሆንም አንድ ነጭ አስተማሪው የህግ ትምህርት ለጥቁሮች የማይቻል ህልም ነው ስላለው፣ የሁለትኛ ደረጃ ትምህርቱን አቋርጦ ሊወጣ ችሏል። ይህ ክስተት ማልኮምን፣ “ምንም እንኳ የፈለገ ባለ ተሰጥኦ ብትሆን፣ ጥቁር ከሆንክ በነጮች ዓለም ምንም ቦታ አይኖርክም” የሚል ስሜት እንዲያዳብር አድርጎታል።

ማልኮም ክ14 እስከ 21 ዓመቱ ድረስ ከእህቱ ኤላ ሊትል ኮሊንስ ጋር፣ የቦስተን ግዛት የሆነችው እና የጥቁሮች መንደር በሆነችው ሮዝበሪ ከተማ እየኖረ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

በኋላም፣ ወደ ሚቺጋን ግዛት ስር የምትገኘው ፍሊንት ከተማ ለአጭር ግዜ ከቆየ በኋላ፣ ወደ ኒውዮርክ ሃርሌም ሰፈር በ እኤአ በ1943 ዓም ኒው ሄቨን የባቡር ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።

ለሁለተኛው አለም ጦርነት እንዲሳተፍ ለውትድርና በቀበሌው መልማይ ቦርድ በተጠራ ጊዜ፣ ልክ ራሱን እንደ አእምሮ በሽተኛ አስመስሎ የማይሆን ቃላት ስለቀባጠረ፣ ለውትድርና ብቁ አይደለም ተብሎ ከውትድርና ሊያመልጥ ችሏል።

በ1945 መጨረሻ አካባቢ ማልኮም ወደ ቦስተን በተመለሰ ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን የተለያዩ የነጭ ቤተሰቦችን ቤት ሰብሮ በመግባት ስርቆት አከናውኗል ይባላል። በ1946 በስርቆት አግኝቶታል የተባለን የእጅ ሰዓት፣ ለስዓት ጠጋኝ እንዲስራ ስጥቶ ነበር እና ተመልሶ ሰዓቱን ከጥገና ቤት ሊወስድ ሲል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ። ከዚያም የሰው ቤት ሰብሮ በመግባት ወንጀል ተከሶ ከ 8 እስከ 10 ዓመት እንዲታሰር ስለተፈረደበት ወደ ቻርልስታውን ስቴት ወህኒ ቤት ወረደ። ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በማሳንቹሴት ግዛት በሚገኘው የኖርፎልክ ወህኒ ቤት ተዛወረ።

በኢስላሚክ ኔሽን የነበረው ቆይታ ለማስተካከል

እስር ቤት

ወህኒ ቤት ሳለ ጆን ቤንብሪ የተባለ ሌላ ታሳሪን ተዋወቀ። ጆን ቤንብሪ ራሱን በራሱ ያስተማረ ሰው ሲሆን፣ ለማልኮም የንባብ ፍቅር እንዲጨምር ተጽዕኖ ያሳደረበትም ግለሰብ ነው። የማልኮም ቤተሰብ (እህት ወንድሞቹ) በተለያየ ጊዜ ኔሽኝ ኦፍ ኢስላም የተባለ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ደብዳቤ እየጻፉ እስር ቤት ድረስ ይልኩለት ነበር። የእምነቱም አስተምህሮቶች፣ በሌሎች አህጉር ያሉ አፍሪካውያን (ዳያስፖራ) ከአውሮፓውያን እና ነጭ አሜሪካውያን ነጻ ሆነው ወደ አፍሪካ መመለስን የሚሰብክ ነበር። በመጀመሪያ እካባቢ ማልኮም ለእምነቱ ብዙም ፈላጉት ያልነበረው ቢሆንም፣ እኤአ በ1948 ዓም ወንድሙ ሬጊናልድ በላከለት ደብዳቤ ላይ የአሳማ ሰጋ አትብላ፣ ሲጋራም ማጭስ አቁም እኔ ከእስር ቤት እንዴት እንደምትወጣ አሳይካለው ሰላለው፣ የአሳማ ስጋ መብላትም ሆነ ሲጋራ ማጭስ ርግፍ አርጎ ተወ። ሬጊናልድ እስር ቤት ሊጠይቅው ሲመጣም ጭምር ስለ ኢስላሚክ ኔሽን አስተምህሮቶች ለማልኮም ያስረዳው ነበር። በዚህም የተነሳ ማልኮም ከነጮች ጋር የነበረውን የትኛውንም የቀድሞ መስተጋብር ኢፍትሃዊነት፣ ስስታምነት፣ ኢተአማኒነት፣ እና ጥላቻ የተሞላበት አድርጎ እንዲመለከት አድርጎታል ይባላል። በእስር ቤት ሳለ ሰይጣኑ የሚል ቅጸል ስም የወጣለት ሲሆን፣ ይህ ስያሜ እንደ ሰይጣን ክፉ ነው ለማለት ሳይሆን፣ በጣም ደፋር፣ እና ላመነበት ነገር ያለ ይሉኝታ ተጋፍጦ የሚናገር በመሆኑ ይባላል።

እኤአ በ1948 ማልኮም ለወቅቱ የኢስላሚክ ኔሽን መሪ ለነበረው ኢሊጃ ሞሀመድ ደብዳቤ ጻፈለት። ኤሊጃም በምላሹ ማልኮም የቀድሞ ባህሪውን እንዲተው፣ ለአምላኩ ሁልጊዜ እንዲሰግድ፣ እንዲሁም ከየትኛውም ነውጠኛ ባህሪያት እራሱን እንዲያርቅ ቃል እንዲገባለት መክሮታል። ማልኮም የመጀመሪያዎቹ የእምነቱ ጊዜያት ላይ ለመስገድ ሲነሳ ከራሱ ጋር የነበረውን የውስጥ ትግል ከባድ እንደነበር አልሸሸገም። ሆኖም ግን በኋላ የኢስላሚክ ኔሽን አባልነቱን ያጸና ሲሆን ከኤሊጃ ጋርም ከእስር ቤት ሆኖ የሚያድርግውን የድብዳቤ ልውውጥ ቀጥሎበት ቆይቷል።

እኤአ በ1950 የአሜሪካው የፌድራል ምርመራ ቢሮ የሆነው ኤፍቢአይ፣ ማልኮም የኮርያ ጦርነትን ተቃውሞ ለፕሬዝዳንት ትሩማን ከእስር ቤት ሆኖ ደብዳቤ በመጻፉ ምክንያት የክስ ፋይል ከፍቶበታል። በዛው አመት የኢስላሚክ ኔሽን መሪ ኤሊጃ ሁሉም አዲስ የእምነቱ ተከታዮች የቤተሰብ ስማቸውን ወደ ኤክስ (X) እንዲቅይሩ ባዘዘው መሰረት፣ ማልኮምም ይህንን ተግባራዊ በማድረግ፣ ሲፈርም ስሙን "Malcom X" እያለ መጻፍ ጀመረ። ኤሊጃ ይህን ኤክስ የሚለውን ስም በቤተሰብ ስም ቦታ እንዲያስገቡ ያዘዘው ለአዲስ የእምነቱ ተከታዮች ሲሆን፣ ለእምነቱ ያላቸውን ታማኝነት ሲያረጋግጡ ግን እሱ ራሱ ትክክለኛ የእስልምና ስማችውን ያሳውቃቸዋል። ማልኮም "X " የሚለውን የእንግሊዝኛ ፊደል ለቤተሰቡ መጠሪያ ሲያደርግ፣ የማያውቃቸውን የአፍሪካዊ ቤተሰብ ስም እንደሚወክልለት ስለሚያምንም ጭምር ነው።

የሚኒስትሪ ጅማሮ