መስተዋድድስም ወይም ስምን መስለው በሚገኙ ቃላት ላይ እየተጫነ ገብቶ በዐረፍተ ነገር ውስጥ የንግግርን ዝምድና የሚያሳይ ቃል ነው። የመስተዋድድ ትርጓሜ አስማሚ ወይም አዋሃጅ እንደ ማለት ነው።መስተዋድድ ከስሙ ወይም ስሙን መስሎ ከገባው ቃል በቀኝ በግራ ወይም በሁለቱም በኩል ሊገባ ይችላል።

ምሳሌ:-

        እሱ በዱላ መታኝ ።
        እሱ በወንበር ላይ ተቀመጠ።
        እሱ ከልጁ ጋር ይጫወታል።

በዚህ በተሰጠው ምሳሌ መሰረት መስተዋድዶቹ በ ፣ በ ፣ ላይ ፣ ከ ፣ ጋር ናቸው። ::