መሐመድ አሚን(Mohamed Amin, ነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፻፴፭ ዓ/ም – ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ/ም) ኬንያዊ ጋዜጠኛ ሲሆን በ77ቱ የኢትዮጵያ ረሐብ ጊዜ ታዋቂ ፎቶግራፎች እና ቪዲዮ ምስሎች በመቅዳት ይታወቃል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱ አምባ-ገነኖች፤ የኡጋንዳው መሪ ኢዲ አሚንና የኢትዮጵያውን መሪ መንግስቱ ኃይለ ማርያምን አወዳደቅ በካሜራው በመዘገብ ይታወቃል። በ፲፱፻፹፫ ዓ/ም ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በነበረ ወቅት በተነሳ የመሳሪያ ማከማቻ ፍንዳታግራ እጁን አጣ። [1] ። አሚን ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ/ም በጠላፊዎች ጫና ቆሞሮስ ደሴት አካባቢ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 961 ሲጓዙ ከሞቱት አንዱ ሰው እርሱ ነበር።

ማጣቀሻ ለማስተካከል

የውጭ ማያያዛዎች ለማስተካከል