ሔርሆርግብጽ ጦር አለቃና በቴብስ አረመኔ ቤተ መቅደስ የአሙን ካህን በፈርዖኑ 11 ራምሴስ ዘመን (1100 ዓክልበ. ያህል) ነበር። በተጨማሪ ስሙ ከአግአዝያን ሥርወ መንግሥት ነገስት ዝርዝር መካከል ተገኝቶ በኢትዮጵያ፣ በኑብያና በደቡብ ግብጽ ላይ በዘመኑ የንጉሥነት ማዕረግ እንደ ያዘ ይመስላል።

ሔርሆር
የሣባ ንጉሥ
ግዛት 1120–1104 ዓክልበ.?
ቀዳሚ አሜን አስታት
ተከታይ 1 ፒያንኪያ
ባለቤት ኖጅመት
ሥርወ-መንግሥት አግዓዝያን ሥርወ መንግሥት
አባት አመንሆተፕ?

ተክለጻድቅ መኩርያ እንዳለው የሔርሆር አባት የቴብስ ካህኑ አመንሆተፕ ሲሆን፣ እናቱ የፈርዖን ልጅ ነበረች። ዳሩ ግን ሌሎች ሊቃውንት ወላጆቹ ከደቡብ ሳይሆኑ ከሊብያ ነበሩ ባዮች ናቸው።[1] ዝርዝሩ እንደሚለው፣ ከሔርሆር ቀጥሎ 1 ፒያንኪያ እንደ ገዛ በሰፊው ይታስብ ነበር። በመምህሩ ካርል ያንሰን-ቪንከልን ምርመራ ግን ይህ ፒያንኪያ በውኑ የሔርሆር ቀዳሚና ዐማት ነበር የሚል አሳብ አቀረበ።[2]

የሔርሆር ሚስት የኖጅመት በድን

በፈርዖኑ 11 ራምሴስ ዘመነ መንግሥት ሔርሆር የሠራዊቱ መኰንን ሲሆን የኑብያን አገረ ገዢ ፒነሔሲን ከቴብስ አባረረው። የሐርሆር ሚስት ኖጅመት ምናልባት የራምሴስ ልጅ ነበረች። በራምሴስ 19ኛው አመት በቴብስ መቅደስ ዋና ቅስና አገኝቶ ከዚያ ጀምሮ በደቡብ ግብጽ ውስጥ በጠቅላላ ሥልጣን ያዘ። በመጨረሻ ሔርሆር የንጉሥነትን ማዕረግ ጨምሮ እርሱና ፈሮዖኑ ራምሴስ በእኩልነት ይቆጠሩ ነበር። የወናሙን ታሪክ የተባለው ታሪካዊ ሥነ ጽሑፍ በሔርሆር 5ኛው አመት የተጻፈ ነበር።

ዋቢ መጽሐፍ ለማስተካከል

  1. ^ Ian Shaw & Paul Nicholson, The Dictionary of Ancient Egypt, British Museum Press, 1995. p.124
  2. ^ Karl Jansen-Winkeln, Das Ende des Neuen Reiches, ZAS 119 (1992), pp.22-37
  • Kees, Hermann. Die Hohenpriester des Amun von Karnak von Herihor bis zum Ende der Äthiopenzeit (1964). Leiden: E. J. Brill