ሌውኪ (ሮማይስጥ፦ Leuci) በሎሬን ክፍላገር፣ ፈረንሳይ በጥንት ጋሊያ የተገኘ ኬልታዊ ጎሣ ነበረ። ዋና ከተማቸው በቱሉም (አሁን ቱል) ነበር። ሌላ ከተማ ናሲዩም ነበራችው።

የለውኪ መሐለቅ

ዩሊዩስ ቄሣር እንደ ተረከው ለውኪ ከሊንጎናውያንሴኳኒ ነገዶች ጋራ ስንዴ ለሮሜ ሥራዊት በ66 ዓክልበ. ያስረክቡ ነበር። ሉካን ደግሞ ለውኪ ጦርን በመጣል ጎበዞች መሆናቸውን ጠቀሰ። በ12 ዓ.ም. በይፋ ወደ ጋሊያ ቤልጊካ ክፍላገር በሮሜ መንግሥት ተጨመሩ።