ሊምፋቲክ ፍላሪያሲስ እንዲሁም ዝሆኔ ተብሎ የሚታወቀው መነሻው በጥገኛ ትልትሎች የ ፍላሪዮአይደያ በሆነው ዝሪያ ነው. በበርካታ ክስተቶች በሽታው የህመም ምልክት የለውም። በአንዳንዶቹ ግን በእጅ፣ በእግር ወይም በመራቢያ ፍሬላይ ተለቅ ያለ እብጠት ያስከትላል. ቆዳም እየፈወረ መጥቶ ህመም ሊያስከትል ይችላል። በሽታው እንዲህ ዓይነት የሰውነት ለውጥ በሚያሰከትልበት ወቅት የተጠቃውን ሰው ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችም ይዳርጋል። [1]

Lymphatic filariasis
Classification and external resources

A picture of a woman with elephantiasis.
ICD-10 B74
ICD-9 125.0-125.9
eMedicine derm/888
MeSH D005368

መንስኤውና የምርመራ ዘዴዎች ለማስተካከል

ትሎቹ (ጀርሞቹ) የሚሰራጩት በተበከሉ ትንኞችንክሻ አማካይነት ነው። በሽታው ብዙወን ጊዜ ሰዎችን የሚይይዘው በህፃንነታቸው ወቅት ነው። በሽታውን የሚያስከትሉት ትሎች (ጀርሞች) ሶስት ዓይነት ናቸው፦ ውቸረሪያ ባንክሮፍቲብራጊያ ማላዪ፣ እና ብራጊያ ቲሞሪውቸረሪያ ባንክሮፍቲ በብዛት የሚታወቅ ነው። ትሉ (ጀርሙ) የዕጢ ስርዓትንያወድማል። [1] በሽታውን በምርመራ ለማወቅ የሚቻለው በሌሊት ወቅት የተወሰደውን የደም ናሙና በ አጉሊ መነጽር ስር በማየት በማየት ነው። የደም ናሙናው በሚታይበት ወቅት The blood should be in the form of a በወፍራሙ/thick smear ሆኖ ከGiemsaጋር መቆየት አለበት። በሽታውን ለመከላከል ሰውነት የሚያመነጨውን የሰውነት መከላከያ ንጥረ ነገር ማየትም ይጠቅማል። [2]

መከላከያና ህክምና ለማስተካከል

መከላከል የሚቻለው በሽታው የሚገኝበትን ማህበረሰብ በየዓመቱ በሚካሄድ የህክምና ክትትል ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ በማድረግ ነው። ይህ ስድስት ዓመታት ያህል ይወስዳል። የሚወሰዱ መድኃኒቶች የሚያጠቃልለው አልቤንዳዞልኢንቨርሜክቲን ጋር ወይም አልቤንዳዞል ከ ዳይቲልካርባማዚንጋር ነው። መድኃኒቶቹ ያደጉ ትሎች (ጀርሞችን) አይገሉም ነገር ግን ትሎቹ በራሳቸው ጊዜ እስኪሞቱ ድረስ በሽታውን እንዳያሰራጩ ይገታሉ። በትንኝ የሚደርሰውን ንክሻ ለመከላከል የትንኞችን ቁጥር መቀነስና የአልጋ አጎበር መጠቀምን ጨምሮ ጥረት ማድረግም ይመከራል። [1]

የስርጭት አድማስ ለማስተካከል

ከ120 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በዝሆኔ በሽታ ተይዘው ይገኛሉ። 1.4 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በ73 አገሮች ለበሽታ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ ይኖራሉ። በሽታው በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኝባቸው አህጉራት ደግሞ አፍሪካና ኢሲያ ናቸው። በሽታው በየዓመቱ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የኢኮኖሚ ጉዳት (እጦት) እያስከተለ ይገኛል። [1]

ዋቢዎች ለማስተካከል

  1. ^ "Lymphatic filariasis Fact sheet °102". World Health Organization (March 2014). በ20 March 2014 የተወሰደ.
  2. ^ "Parasites - Lymphatic Filariasis Diagnosis". CDC (June 14, 2013). በ21 March 2014 የተወሰደ.