ሃኢ ጋኦን (ዕብራይስጥ፦ האיי גאון) ከ931 እስከ 1030 ዓም በባቢሎን ዙሪያ የኖረ የአይሁድና እና የተልሙድ አስተማሪ ነበር።

በተለይ የሚታወቀው «responsa» («መልሶች») ስለ ተባሉ ጽሁፎች ናቸው። ለምሳሌ ያህል የሚከተለውን ጻፈ፦

«መሢህ ወልደ ዮሴፍ፣ ከዳዊት ሥርወ መንግሥት የሆነ ታላቅ ጻድቅ፣ በይሁዳ ሕዝብ መካከል ይነሣል። መሪነቱ እንደ ንጉሥ ዘመን የሚመስል፣ ለአርባ አመት የሚቆይ ይሆናል። በዚህም ዘመን መሢህ ወልደ ዮሴፍ ብዙ አይሁዶችን ወደ ኦሪት መንገድ ይመልሳችዋል።» Responsum on Succot 52a

ይህ «አርባ አመት» ጊዜያዊ መሢሃዊ መንግሥት የሚለው ትንቢት ከሃኢ ጋኦን ዘመን አስቀድሞ ለረጅም ጊዜ ይጠበቅ ነበር። ረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ Midrash on Psalm 90:15፤ የባቢሎን ተልሙድ[1] እና የኤልያስ ራዕይ ሁላቸው የአርባ አመት ጊዜያዊ መሢሃዊ መንግሥት ትንቢት ከጥንት ዘግበዋል። እንዲሁም በእስልምናሙሐመድ ጓደኛ አቡ ሑራይሓህ (595-673 ዓም) በሀዲስ Book 37, Number 4310 ይህን ተመሳሳይ ትንቢት ጠቀሰ።

  1. ^ http://www.come-and-hear.com/sanhedrin/sanhedrin_99.html