ከ«ምጽራይም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
የ«''ሚጽራዪም''» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ [[ግብጽ]] (ምሥር) አገር ነው። እንዲሁም በ[[አረብኛ]] የአገሩ ስም '''مصر''' (ምጽር) ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በ[[አካድኛ]] መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በ[[ኡጋሪት]]ም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል።
 
አባ [[አውሳብዮስ]] በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ [[ማኔጦን]] (3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከ[[ማየ አይህ]] አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በ[[ፋርስእስላም]] ጸሐፊዎች በግብጻዊው [[እብን አብድ ኤል-ሀከም]] እና በፋርሳውያን [[[[አል-ታባሪ]]ና [[ሙሐመድ ቈንዳሚር]] መጻሕፍት ሲገኝ፣ [[ፒራሚዶች]]፣ [[የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ|እስፊንክስ]] ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም (ማሣር ወይም መሥር) ተሠጠ ብለው ጻፉ።
 
በ[[ፊንቄ አፈ ታሪክ]] ደግሞ «[[ሚሶር]]» የሚባል ሰው የ[[ታዓውቶስ]] አባት ሲሆን የ[[ቢብሎስ]] ንጉሥ [[ክሮኖስ]] ግብጽን ለዚሁ ታዓውቶስ እንደ ሰጠ ይታመን ነበር።