ከ«ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 7፦
በዚህ ጦር [[ግንባር 9]] ወራት ለበሽሊንዲ፤ [[ዋቢ ሸበሌ]]፤ እና የመሳሰሉ ሥፍራዎች ከ እነ [[ባላምባራስ አየለ ወልደማርያም]] ጋር ሆነው ጠላትን ሲከላከሉ ከርመው ወደ ጎባ ተመለሱ። ከሰኔ 1928 ዓ.ም ጀምሮ እስከ [[ሚያዚያ 23]] ቀን [[1929]] ዓ.ም ድረስ ከ[[አሩሲ]]፤ ከ[[ሲዳሞ]]፤ ከ[[ሐረር]]ና ኦጋዴን ወደ ጎባ በሃይል የመጣውን የጠላት ጦር በራሳቸው መሪነት ሲዋጉ ከርመው፤ መጨረሻ ላይ ተማም ከሚባለው ሥፍራ ላይ በተካሄደው ጦርነት ላይ ማምለጥ በማይቻልበት ኹኔታ በጠላት እጅ ወደቀው ተማረኩ። ጠላትም ለአምስት ወራት በጽኑ እሥራት ከያዛቸው በኋላ፤ በጥር ወር [[1930]] ዓ.ም ጣሊያን መሳሪያ አስታጥቆ በሽፍን መኪና ከጎባ ወሊሶ አምጥቶ እስር ላይ አዋላቸው። ባሻ ኪዳኔም እዚሁ እስር ቤት እያሉ አብረዋቸው ከታሰሩት መሀል በምስጢር ቃለ መሃላ በመስጠት 100 ሰዎች አሳብረው እዚያ ያለውን የጠላት ጦር ፈጅተው ለመሸፈት ከወሰኑ በኋላ ወደ ባላምባራስ (በኋላ ደጃዝማች) [[ገረሱ ዱኪ]] የሚላክ ሰው በማፈላለግ ላይ እያሉ ጠላት ሰምቶ ኖሮ አጥብቆ ይከታታላቸው ጀመር። ይኼን ሲገነዘቡ ነገሩን አብርደው ሲጠባበቁ ወደ ባላምባራስ ገረሱ የላኩት ብሩ የሚባለው መልክተኛ [[ጥር 15]] ቀን 1930 ዓ.ም በጠላት እጅ ተይዞ ቀኑን ሙሉ ሲመረመር ዋለ። ባሻ ኪዳኔም በዚያው ዕልት ከምሽቱ 2 ሰዓት ሲሆን በቃለ መሃላ ያደራጇቸውን ሰዎች በያሉበት እየሄዱ ከነመሳሪያቸው እየሰበሰቡ ሲያከማቹ የጠላትም ዘቦች ነቅተው በተንቀቅ ተሰልፈው ይጠብቋቸው ጀመር። ባሻ ኪዳኔ ግን ወገኖቻቸውን ሸልሉ ብለው ሲያሸልሉ የጠላት ዘቦች ተደናግጠው እንዲያውም እነሱ ሳይተኩሱ አትተኩሱ የሚል ትእዛዝ አስተላልፈው ይጠባበቃሉ። ባሻ ኪዳኔም በዚህ ጊዜ ቃለ መሓላ ከሰጧቸው 100 ሰዎች ውስጥ 55 ወታደር ከነመሳሪያው፤ አራት ድግን መትረየስ፤ 10 ሣጥን ጥይት፤ 6 ሽጉጥ ከጠላት እጅ ነጥቀው እየተታኮሱ ሲወጡ የጠላት ኃይል 20 ወታደርና 1 መትረየስ ከ 2 ሣጥን ጥይት ጋር ብቻ ገንጥሎ ሲያስቀርባቸው የተረፈውን መሳሪያና ወታደሮች ጋር ድል አድርገው ሸፈቱ። ወዲያውም ኩሳ ኪዳነምሕረት ከሚባል ሥፍራ ላይ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ተገናኙ።
 
ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ከተቀላቀሉ በኋላም በደንዲ፤ በሶዶ፤ በበዳቄሮ እና በመሳስሉ ሥፍራዎች አርበኝነታቸውን እስከ ጥቅምት [[1931]] ዓ.ም ድረስ ሲያካሂዱ ከቆዮ በኋላ በዳቄሮ ከሚባለው ሥፍራ ላይ ከ [[ዱካ ዳኦስታ]]ና ከ [[ጄነራል ናዚ]] ተልኬያለሁ የሚለው [[ሙሴ ቀስተኛ]] (ሴባስቲያኖ ካስታኛ) የሚባለው ሰላይ ከሦሥት ባላባቶች ጋራ መጣ። አርበኞቹም ቀደም ሲል በ1930 ዓ.ም ይኼው ሰላይ ወደ ባላምባራስ [[አበበ አረጋይ]] ዘንድ ሄዶ የጦሩን ኃይል ከአየ በኋላ ብዙ አርበኛ እንዳስፈጀ ሰምተው ስለነበር እነሱንም እንደዚሁ ለማስፈጀት እንደመጣ ስለተገንዘቡት ባሻ ኪዳኔ ወልደመድኅን በመውዜር ጠመንጃ ሲመቱት 'ማማ ሚያ፤ ኢጣልያ ለዘለዓለም ትኑር ለኢጣሊያ ስል ሞትኩላት' ብሎ ሲናገር በሽጉጥ ራሱን መትተው ከገደሉት በኋላ የለበሰውን ሙሉ ገበርዲን ልብስና ካፖርት እንዲሁም የ [[ንግሥተንግስተ ነገሥታትነገስታት ዘውዲቱ]] ን ስዕል ያለበትን የብር ሰዐትና በቅሎውን ከነኮርቻው ማረኩት። እሱም እንደተገደለ አብረውት መጥተው የነበሩት ባላባቶች ለጄነራል ናዚ አስታውቀው ኖሮ 25 ባታሊዮን ወታደርና 28 አውሮፕላን ወደበዳቄሮ ዘምቶ ተርታውን ለሦሥት ቀን ሲከላከሉ ከቆዩ በኋላ አርበኞቹ ተሸንፈው ጠላትም የሙሴ ቀስተኛን እሬሳ አንስቶ ወሰደ። አርበኞቹም ከዚያ ሥፍራ ሸሽተው ሶዶ ላይ እንደገና ልስምንት ቀን ተዋጉ።
 
ባሻ ኪዳኔ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ከሙሴ ቀስተኛ የተማረከውን አላስረክብም በማለታቸውና በሌላም ምክንያቶች ባለመስማማታቸው፤ በኅዳር ወር 1931 ዓ.ም. አባሎቻቸውን አስከትለው ወደ ትውልድ አገራቸው ወደቡልጋ ተጉዘው በ12 ቀናቸውም ቡልጋ ገቡ። እዚሁም ከፊታውራሪ ኃይለማሪያም ማናህሌ እና ከፊታውራሪ ተረፈ ማናህሌ ጋር ተቀላቅለው እስከ መጋቢት 1931 ዓ.ም. ድረስ በውሽንግር፤ ጨፌ ዶንሳ ምሽግ፤ ነጭ ድንጋይ ምሽግ፤ ልዝብ ድንጋይ ከተባሉ ቦታዎች ላይ ከጠላት ኃይል ጋር ሲዋጉ ከርመው በመጋቢት ወር በሃገሩ ላይ ገብቶ በነበረው የ [[እንቅጥቅጥ በሽታ]] በጽኑ ታመው ከልዝብ ድንጋይ ምሽግና ቤቶች ነጭ ድንጋይ ጦስኝ ምሽግ ከወደምስራቅ ኮረማሽ መካከል ታመው ተኙ:: ወዲያው በሰኔ ወር ሦሥት አምባ ላይ ሰፍረው ሳሉ ጠላት በሦስት አምባ፤ በወይን አምባ እና በጦስኝ በኩል ወርዶ ሲከባቸው ባሻ ኪዳኔ ገመምተኛ ስለነበሩ መሮጥ አቅቷቸው ‘ተማረክ’ እያለ የከበባቸውን የጠላት ጦር እየተከላለከሉ ጫካ ገቡ የጠላትም ወታደሮች የገቡባት ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ባሻ ኪዳኔ ጎርፍ በጀለጣት ዛፍ ተንጠልጥለው ደፍጠው ሲጠባበቁ ጠላት ጫካውን በእሳት ነበልባል ግራና ቀኙን ሲያቃጥልው እሳቸው ያሉባት ሳትቃጠል ሊተርፉ ቻሉ። ከሦስት ቀንም በኋላ ጠላት ለቆ ሲሄድ ባሻ ኪዳኔ ከጅረት ወርደው ውሃ ሲጠጡ ደክመው ወድቀው ሳሉ ወንድማቸውና ሌሎች ሲፈልጓቸው በጥይት ያሉበትን አሳወቋቸውና መጥተው በቃሬዛ አዛውሯቸው፡