ከ«ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 14፦
[[ጆን ጊል]] ([[1697 እ.ኤ.አ.|1697]]-[[1771 እ.ኤ.አ.]]) በመጽሓፍ ቅዱስ ነክ አስተያይቶቹ ስለ አንድ የ[[ዓረብ]] አፈ ታሪክ የጻፈው እንዲሁ ነው፤ «የሴም ሚስት ስም '''ዛልበጥ''' ወይም '''ዛሊጥ''' ወይም '''ሳሊት''' ሲሆን፣ የካምም ደግሞ '''ናሓላጥ''' ተባለች፣ የያፌትም ደግሞ '''አረሢሢያ''' ተባለች።
 
''[[ኪታብ አል-ማጋል]]'' የተባለው ጥንታዊ [[አረብኛ]] መጽሐፍ (ከ'[[ቄሌምንጦስ]] መጻሕፍት' መሃል)፣ በ[[ጽርዕ]] የተጻፈው መጽሐፍ [[የመዝገቦች ዋሻ]] (350 ዓ.ም. ገዳማ) እና የ[[እስክንድርያ]] አቡነ [[ዩቲኪዮስ]] (920 ዓ.ም. ገዳማ) ሁሉ ሲስማሙ የኖህን ሚስት '''ሃይኬል''' ይሏታል፤ እርስዋም የናሙስ ልጅ፣ ናሙስም የሄኖክ ሴት ልጅ፣ ይህም ሄኖክ የማቱሳላ ወንድም እንደ ነበሩ ይላሉ። ''ኪታብ አል-ማጋል'' ደግሞ የሴም ሚስት የናሲህ ልጅ '''ልያ''' ብሎ ይሰይማታል።

[[የሳላሚስ አጲፋንዮስ]] የጻፈው ''[[ፓናሪዮስ]]'' ደግሞ የኖህ ሚስት '''ባርጤኖስ''' ይላታል። በ5ኛ ክፍለ ዘመን አካባቢ በ[[ግዕዝ]] የተሠራው [[መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን]] ግን የኖህ ሚስት '''ሃይካል''' ሲጠራት ይቺ የአባራዝ ልጅ፣ አባራዝም የ[[ሄኖስ]] ልጆች ሴት ልጅ ናት ይላል። አንዳንድ ጸሐፊ ስለዚህ የአጲፋንዮስ 'ባርጤኖስ' ማለት ከእብራይስጥ 'ባጥ-ኤኖስ' መሆኑን አጠቁሟል።<ref>[http://books.google.com/books?id=G0uQfRWuU4wC&pg=PA268&lpg=PA268&dq=abaraz+enos&source=web&ots=SgeVHo6Cvw&sig=Xf4POxB51QCMhFNI2CZyQdO4GlY ''A Dictionary of Christian Biography, Literature, Sects...'' p. 268]</ref>.
 
በ'ሲቡላውያን ንግሮች' ዘንድ፣ ከሲቡሎቹ የአንዲቱ ስም ለ'''ዛልበጥ''' ተመሳሳይ ነበረ፤ እሷም የ«ባቢሎን ሲቡል» '''ሳምበጥ''' ነበረች። ከጥፋት ውሃ 900 አመት በኋላ ወደ [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] አገር ሄዳ የንግሮች ጽሑፍ እንደ ጀመረች ብላ ጻፈች። ከዚያ በላይ የጻፈችው ጽሁፍ ከማየ አይህ አስቀድሞ የነበሩ የቤተሠቧ ስሞች ይታርካል። እነሱም አባቷ ''ግኖስቲስ''፣ እናቷ ''ኪርኬ''፤ እህቷም ''ዒሲስ'' ናቸው። በሌሎች ጥንታዊ ምንጮች ደግሞ '''ሳባ''' የምትባል ሲቡል ኖረች።
Line 25 ⟶ 27:
 
በደቡብ [[ኢራቅ]] በሚኖሩት በጥንታዊ [[ማንዳያውያን]] ሐይማኖት ተከታዮች መጻሕፍት ዘንድ፤ የኖህ ሚስት '''ኑራይታ''' ወይም '''አኑራይጣ''' ተባለች።
 
በ[[ግብጽ]] 1-3 ክፍለ ዘመናት ዓ.ም. የተገኘው [[ግኖስቲክ]] ሃይማኖት መጻሕፍት ዘንድ የኖህ ሚስት '''ኖሬያ''' ስትሆን ''መጽሐፈ ኖሬያ'' የሚባል ጽሕፈት ነበራቸው።
 
አይሁዳዊ [[ሚድራሽ]] 'ራባ' እና በ11ኛ ክፍለ-ዘመን የኖረው አይሁድ ጸሐፊ [[ራሺ]] እንዳለው የኖህ ሚስት የላሜህ ሴት ልጅና የ[[ቱባልቃይን]] እኅት '''ናዕማህ''' ነበረች። እንዲሁም ከ[[1618]] ዓ.ም. ብቻ በሚታወቀው ሚድራሽ «ያሻር መጽሐፍ»፣ የኖህ ሚስት ስም የ[[ሄኖክ]] ልጅ '''ናዕማህ''' ተባለች። ነገር ግን፤ ጥንታዊ መጽሀፈ ኩፋሌ ስምዋ '''አምዛራ''' ተብሎ ይሰጣል። «ናዕማህ» የሚለው የካም ሚስት ስም ለኖህ ሚስት ስም በአይሁድ ልማድ እንደ ተሳተ ጆን ጊል ሐሳቡን አቅርቧል።
 
በ[[ሮዚክሩስ]] («የጽጌ ረዳ መስቀል ወንድማማችነት»፤ ምስጢራዊ ማኅበር) ጽሕፈት ''ኮምት ደ ጋባሊስ'' (1672) ዘንድ፣ የኖህ ሚስት ስም '''ቨስታ''' ትባላለች።
 
በመጨረሻም፣ በ[[ዩናይትድ ስቴትስ]] በሚገኘው በ[[ሞርሞን]] ሃይማኖት ('የየሱስ ክርስቶች መጨረሻ ዘመን ቅዱሳን') መጻሕፍት ዘንድ፣ የካም ሚስት ስም '''ኢጅፕተስ''' ነበረ።