ከ«ሹቡር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ሹቡር''' ([[ሱመርኛ]]፡ ሱቢር፣ ሱባር፣ ሹባር፣ ሹቡር፤ [[አካድኛ]]፦ ሱባርቱ፣ ሹባርቱም፣ ሱባርቱም፣ ሹባሪ) ከ[[ሰናዖር]] ወደ ስሜን በ[[ጤግሮስ ወንዝ]] ላይ የተቀመጠ አገር ነበረ። ይህም ስም በጥንታዊ [[አማርና ደብዳቤዎች]]ና በ[[ኡጋሪት]] መዝገቦች 'ሽብር' ተጽፎ ተገኝቷል።
 
ከሁሉ ጥንታዊ በሆነ ዘመን፣ ከሰናዖር (ሱመር) ዙሪያ ሌሎቹ '4 ሩቦች' 'ማርቱ' ([[አሞራውያን]])፣ 'ሱባርቱ'፣ [[ኤላም]]ና 'ኡሪ -ኪ' ([[አካድ]]) ነበሩ። እንዲሁም [[ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ]] በተባለው ሱመራዊ [[አፈ ታሪክ]]፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ [[ሐማዚ]]፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር ይባላሉ።
 
ሱባርቱ በ[[አዳብ]] ንጉስ [[ሉጋል-አኔ-ሙንዱ]] መንግሥት ውስጥ አንድ ክፍል ነበረ፤ በኋላ ዘመን የአካድ ንጉስ [[1 ሳርጎን]] በሱባር ላይ አንዳንድ ዘመቻ ያደርግ ነበርና ተከታዩ [[ናራም-ሲን]] ከገዛቸው አገራት መካከል ቆጠሩት። የ[[ኢሲን]] ንጉስ [[ኢሽቢ-ኤራ]] እና የ[[ባቢሎን]] ንጉስ [[ሃሙራቢ]] ደግሞ በሱባር ላይ እንዳሸነፉት ይታመናል።