ከ«የኡር-ናሙ ሕግጋት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
መጀመርያ የተገኘው ቅጂ በተሰበረ ጽላት በ[[ኒፑር]] ፍርስራሽ ሲሆን፣ በ[[1944]] ዓ.ም. ሊቅ [[ሳሙኤል ክሬመር]] አስተረጎሙት። ሆኖም ሰባራ ክፍሎች እንደ መሆኑ ከሕጎቹ ሁሉ 5ቱ ብቻ ሊታነቡ ይችሉ ነበር። ዳሩ ግን ሌሎች ቅጂዎች በኡርና በ[[ሲፓር]] ከተገኙ በኋላ አሁን ከ57 ድንጋጌዎች በጠቅላላ፣ 40 ያሕል ሊታወቁ ተቻለ።
 
የኡር-ናሙ ሕገጋት ከ[[ሃሙራቢ]] ሕጎች በ300 አመት አስቀደሙ። ሆኖም ሌሎች የሕገጋት ሰነዶች ከኡር-ናሙ ጊዜ በፊት በሱመርበ[[ሱመር]] እንደ ኖሩ ይታወቃል። የ[[ላጋሽ]] ንጉሥ [[ኡሪካጊናኡሩካጊና]] የሕግ ማሻሻል እንዳወጣ የሚል ጽላት ተገኝቷልና።
 
በዚህ ሰነድ ሕጎቹ «አንድ ሰው እንዲህ ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ» በሚመስል አባባል ይጻፋሉ። ይህም ዘዴ ደግሞ በኋለኛ ሕገ መንግሥታት ይታያል። ከንጉሡ («ሉ-ጋል» ወይም ታላቅ ሰው) በታች፣ ከኅብረተሠቡ 2 አይነት ማእረግ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም፦ 1) «ሉ» ወይም ነጻ ሰው እና 2) «አራድ» (ባርያ) / «ጌሜ» (ገረድ) ናቸው። የ«ሉ» ወንድ ልጅ ሚስት እስከሚያገባ ድረስ «ዱሙ-ኒታ» ይባል ነበር። የሴት («ሙኑስ») ሁኔታ ከሴት ልጅ («ዱሙ-ሚ») ጀመሮ እስከ ሚስት («ዳም») ከዚያም ከባሏ እረፍት ብትኖር ኖሮ እስከ ጋለሞታ («ኑማሱ») ድረስ ይደርስ ነበር።