ከ«ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
corrections
No edit summary
መስመር፡ 16፦
በ'ሲቡላውያን ንግሮች' ዘንድ፣ ከሲቡሎቹ የአንዲቱ ስም ለ'''ዛልበጥ''' ተመሳሳይ ነበረ፤ እሷም የ«ባቢሎን ሲቡል» '''ሳምበጥ''' ነበረች። ከጥፋት ውሃ 900 አመት በኋላ ወደ [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] አገር ሄዳ የንግሮች ጽሑፍ እንደ ጀመረች ብላ ጻፈች። ከዚያ በላይ የጻፈችው ጽሁፍ ከማየ አይህ አስቀድሞ የነበሩ የቤተሠቧ ስሞች ይታርካል። እነሱም አባቷ ''ግኖስቲስ''፣ እናቷ ''ኪርኬ''፤ እህቷም ''ዒሲስ'' ናቸው። በሌሎች ጥንታዊ ምንጮች ደግሞ '''ሳባ''' የምትባል ሲቡል ኖረች።
 
በ[[15ኛ ክፍለ ዘመን]] አውሮፓዊ መነኩሴ [[አኒዮ ዳ ቪተርቦ]] ዘንድ፣ [[ከለዳዊ]]ው [[ቤሮሱስ]] ([[ክ.በ. 280]] ዓመት ያህል የጻፈ) የልጆቹ ሚስቶች '''ፓንዶራ፣ ኖኤላ፣ ኖኤግላ''' የኖህም ሚስት '''ቲቴያ''' ተብለው እንደ ተሰየሙ ብለው ነበር። ነገር ግን ይህ አኒዮ ዛሬ አታላይ ጸሐፊ እንደ ነበር ይታመናል[http://books.google.com/books?id=FyskAAAAMAAJ&pg=PA207&lpg=PA207&dq=berosus+pandora+noela&source=web&ots=yq6RpckzkN&sig=l-bE36p_2w521y1-H3GNyqtgYgs#PPA207,M1] ።
 
በ[[አይርላንድ]] አፈ ታሪክ ስለ ሦስቱ ልጆችና ስለ ሚስቶቻቸው የሚተረተው ብዙ አለ። በዚሁ ምንጭ ሚስቶቹ '''ኦላ፣ ኦሊቫ፣ ኦሊቫኒ''' ይባላሉ። እነኚህም ስሞች የተወሰዱ [[ኮዴክስ ጁኒየስ]] ከተባለው ጥንታዊ ([[700]] ዓ.ም.) [[እንግሊዝ]] [[ብራና ጥቅል]] ይመስላል። ይኸው ጽሕፈት እንደ ረጅም [[ግጥም]] ሆኖ በገጣሚው በ[[ካድሞን]] እንደተጻፈ ይታሥባል። እዚህ ደግሞ የኖህ ሚስት '''ፔርኮባ''' ትባላለች።