ከ«ጨው» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
cat
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ጨው''' ማለት በ[[ጥንተ ንጥር]] በተለይ NaCl (ሶዲየም ክሎሪድ) ነው። የተሠራ ከ[[ሶዲየም]] (Na) እና [[ክሎሪን]] (Cl) ነው። ይህ ማዕደን በምግብ ውስጥ ይበላል። ጣዕም ለመጨመር እንዲሁም የምግብን ኹኔታ ለማስጠበቅ በጣም ይጠቅማል።
 
==ታሪክ==
ጨው የምግብን ኹኔታ ስለሚያስቆይ፣ ሥልጣኔ በ[[ግብጽ]] ወዘተ. እንዲጀመር የጨው ጥቅም አይነተኛ ሚና ነበረው። ከጥቅሙ የተነሣ በ1 ወራት የሚበላሽ ምግብ እንግዲህ ከወራቱ በኋለ እንዲቆይ ተደረገ። ከዚህም በላይ፣ እንዲህ ያለ ምግብ በረጅም ጉዞ ላይ እንደ ሥንቅ መውሰድ ከዚያ ጀምሮ ተቻለ።
 
በጥንታዊ ዘመናት ጨው ዕጅግ ከፍ ያለ ዋጋ ስለነበረው በ[[ቻይና]] በ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] በ[[መከከለኛ ምሥራቅ]]ም ሆነ በ[[አፍሪቃ]] ውድ የንግድ ቅመም ሆኖ ተቆጠረ። በ[[ሜዲቴራኔያን]] ዙሪያ እንዲሁም በ[[ሮማ መንግሥት]]፣ ጨው እንደ ገንዘብ (አሞሌ) አገለገለ። ይሁንና ሰዎች ጨው ከውቅያኖስ ጨዋማ ውሃ ማስገኘት በተማሩበት ግዜ፣ የጨው ዋጋ ተቀነሠ። የ[[ፊንቄ]] ሰዎች ብዙ የውቅያኖስ ውኃ በየብስ ላይ አፍስሰው ውኃው ከደረቀ በኋላ ጨውን አከማችተው ይሽቱት ነበር።
 
አንዳንዴ ደግሞ ጨው በጦርነት ግዜ የከተማ ሰብል ለማበላሽ በእርሻ ላይ ተበትኖ እንደ ቅጣት መሣርያ ያገልግል ነበር። ለምሳሌ የ[[አሦር]] ሰዎች ይህን በጎረቤቶቻቸው ላይ እንዳደረጉ በታሪክ መዝገቦች ይባላል።
 
{{መዋቅር}}
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ጨው» የተወሰደ