ከ«የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: Reverted Visual edit
No edit summary
Tags: Reverted Emoji በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 1፦
ዘላለማዊ ውልደት
 
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
 
19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
 
በ 325 ድኅረ ልደት የተሰተበሰቡት የኒቂያ ጉባኤ ኢየሱስን፦ “አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፤ ከአካሉ አካልን ወስዶ ተገኘ ወይም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ሲሉት በ 381 የተሰበሰቡት የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ደግሞ፦ "ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት ተወለደ" አሉት፥ ይህ አወላደል "ዘላለማዊ ውልደት"eternal generation" ይሉታል። ኢንሻሏህ ለዚህ አስተምህሮት ድምዳሜ ላይ አደረሱን የሚሏቸውን የባይብል አናቅጽ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስንና እያደማን እናየዋለን፦
ምሳሌ 8፥25 ግዕዙ፦ "ወዘንበለ አድባር ይተከሉ፥ ወእምቅድመ አውግር “ወለደኒ”።
 
ትርጉም፦ "ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት “ወለደኝ”።
 
ይህንን ጥቅስ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የይሆዋ ምስክሮች ለኢየሱስ ሲያውሉት በተቃራኒው ፕሮቴስታንት፣ የፕሮቴስንታንት ግልባጭ ተሐድሶያውያን እና የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የፈጣሪ ባሕርይ ለሆነው ለጥበብ ያውሉታል።
በግዕዝ “ወለደኒ” ማለት “ወለደኝ” ማለት ሲሆን “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት እንደሆነ አንድምታው እና ሃይማኖተ-አበው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ነግረውናል፦
ምሳሌ 8፥25 አንድምታ፦ “ወለደኒ” ስለ ስጋ “ፈጠረኝ” አልሁ።
 
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦ “ወለደኒ” ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ “ፈጠረኒ” በእንተ ትስብእቱ።
 
ትርጉም፦ “ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለት ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል።
 
“ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ከሆነ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት መወለድን ሳይሆን ከድንግል ማርያም መፈጠርን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፥ ኢየሱስ "ልጅ" የተባለው ከአብ ምንነትና ማንነት ስለወጣ እና ስለተገኘ ቢሆን ኖሮ "መንፈስ ቅዱስም ከአብ የወጣ እና የተገኘ ነው" ስለምትሉ መንፈስ ቅዱስም "ልጅ" ይባል ነበር። ነገር ግን "ልጅ" የተባለበት ትርጉም "ፍጡር" ማለት ነው፥ በአምላክ ልብ ቀድሞውኑ መወሰኑ ለማመልከት ከፍጥረት በፊት እንደተፈተጠረ መናገሩ ጉልኅ ማሳያ ነው፦
ምሳሌ 8፥22 ግዕዙ፦ "እግዚአብሔር ፈጠረኒ ቀዳሜ ኩሉ ተግባሩ"።
 
ትርጉም፦ "እግዚአብሔር በቀድሞ ሥራው ሁሉ ፈጠረኝ"
 
አንድምታው፦ "በአዲስ ተፈጥሮ ከሚፈጥራቸው ምእመናን አስቀድሞ እግዚአብሔር አስቀድሞ ፈጠረኝ"
 
በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር አዲስ ፍጥረት ከመፍጠሩ በፊት ኢየሱስን በድንግል ማርያም ማሕፀን ውስጥ መፍጠሩን የሚያሳይ ነው፦
አንድምታው፦ "የምእመናን የሥራቸው በኲር እሆን ዘንድ እግዚአብሔር ፈጠረኝ"
 
የአንጾኪያው ኤዎስጣቴዎስ በ 337 ድኅረ ልደት ይህንኑ ጉዳይ በአጽንዖት እና በአንክሮት ያጠናክርልናል፦
"የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ጌታ ፈጠረኝ" የሚለው ንግግር የተነገረው በድንግል ማሕፀን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ የተተከለውን ከሴት የተወለደውን ሰው ነው"።
Ancient Christian Commentary On scriptures page 63.
 
እሩቅ ሳንሄድ እግዚአብሔር ኢየሱስ የሾመው እኮ በአዲስ ኪዳን ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኃላ ነው፥ ነገር ግን መሾሙ እንቅድመ ዓለም በልበ አምላክ ቀድሞውኑ አስቀድሞ ስለተወሰነ፦ "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፥ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ" ብሏል፦
ምሳሌ 8፥23 "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፥ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ"።
 
መቼም እምቅድመ ዓለም ሿሚ እና ተሿሚ ካለ አንዱ ጋር ያለው ሌላው ጋር የሌለ ሹመት እና ስዩም አለ ማለት ነው፥ የእስክንድርያው አርጌንስ፦ "አብ በላጭ ገዢ ወልድ ተበላጭ ተገዢ በመሆን "ዘላለማዊ የአገልግሎት መገዛዛት"eternal functional subordination"(EFS) በአብ እና በወልድ መካከል አለ" ለማለት ያስደፈረው "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ" የሚለው ጥቅስ ነው።
 
ስንቀጥል ፈጣሪ ኢየሱስን ከድንግል ማርያም በማኅፀኗ ውስጥ ያለ አባት ዘር"sperm cell" ፈጥሮታል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ግዕዙ፦ "ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል"
 
ትርጉም፦ “እርሱ ሥጋውን በድንግል ማኅፀን ፈጠረ"
 
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 124፥19
ግዕዙ፦ "ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት"
 
ትርጉም፦ "ከሴት በሥጋ ስለተወለደ "ፍጡር ነው" እንላለን"
 
ሃይማኖተ-አበው ዘጎርጎርዮስ 35፥6
ግዕዙ፦ "ወዓዲመ ይትበሀል "ፍጡረ" በእንተ ዘኮነ ሥጋ"
 
ትርጉም፦ "ሥጋ ስለሆነ "ፍጡር" ይባላል"
 
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76፥19
ግዕዙ፦ "ተፈጥረ እምከርሠ ድንግል"
 
ትርጉም፦ "ከድንግል ማኅፀን ተፈጠርኩኝ"
 
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76፥21
ቄርሎስም አለ፦ "እግዚአብሔር ዘፈጠረኒ እምከርሥ"
 
ትርጉም፦ "በማኅፀን የፈጠረኝ እግዚአብሔር"
 
እንግዲህ ፈጣሪ ኢየሱስን ከድንግል ማርያም እንደፈጠረው ካየን ዘንዳ ይህንን ጉዳይ እምቅድመ ዓለም በልበ አምላክ ከእርሷ ማኅፀን እንደፈጠረው ይናገራል፦
መዝሙር 110፥3 ግዕዙ፦ "ወለድኩከ እም ከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"
 
ትርጉም፦ "ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን ወለድኩህ"
 
"ከማኅፀን ወለድኩህ"I have begotten thee from the womb" የሚለው ቃል ግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ የሚገኝ ሲሆን የዕብራይስጡ ማሶሬት፣ አብዛኛው እና አብላጫው እንግሊዝኛ ቅጂዎች እና በዐማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ ግን"ከንጋት ማኅፀን በቅዱስ ግርማህ ደምቀህ የጎልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ"Arrayed in holy splendor, your youth will come to you like dew from the morning’s womb" ብለው አቀምጠውታል።
"ከርሥ" ማለት "ማኅፀን"the womb" ማለት መሆኑን "እምከርሠ ድንግል" "ውስጠ ከርሠ ድንግል" የሚል ብዙ ቦታ ስላለ ይህ ማኅፀን የድንግል ማርያም ማኅፀን ነው፥ ድንግል ማርያም በልበ አምላክ እምቅድመ ዓለም ነበረች፦
ነገረ-ማርያም ቅዱስ ያሬድ በዚቅ
"ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር፣ ወዘእበለ ይሳረር ምድረ ገነት ሀለወት ስብሕት፣ ቅድስት፣ ወቡርክት ይእቲ ማርያም"
 
ትርጉም፦ "የተመሰገነች፣ የተቀደሰች እና የተባረከች እርሷ ማርያም ሰማይ እና ምድር ሳይፈጠር እና የገነት ምድር ሳይመሠረት ነበረች"
 
ስለዚህ ማርያም ሆነ ልጇ በልበ አምላክ አስቀድመው ነበሩ እንጂ በህልውና ደረጃ ሁለቱም የተፈጠሩት ከጊዜ በኃላ ነው፥ ያለ ማርያም ማኅፀን አስቀድሞ ስላልፈጠረው ያሬድ በዚቁ፦ "አዝማንየ አዝማንኪ አምጣንየ አምጣንኪ፥ ማርያም አቀፍኪዮ ወአነ ዮም ወለድኩዮ"
 
ትርጉም፦ "ዘመኖቼ ዘመኖችሽ መጠኖቼ መጠንሽ ናቸው፥ ማርያም ሆይ! እኔ ዛሬ ወለድኩት አንቺ ደግሞ ታቀፍሺው"
 
"ዛሬ" የሚለው የጊዜ ተውሳከ ግስ ውልደቱ በጊዜ ውስጥ ጅማሮ እና መነሻ እንዳለው አመላካች ነው፥ ፈጣሪ ከድንግል ሆድ በማውጣት የላከው መልእክተኛ ከእርሷ የተወለደ ነው፦
መዝሙር 22፥9 "አንተ ግን "ከሆድ" አውጥተኸኛልና"።
መዝሙር 22፥10 "ከእናቴ "ሆድ" ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ"።
ገላትያ 4፥4 "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ"።
 
"ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ" የማርያም ሆድ ቃል በቃል እንዳልነበረ ሁሉ ኢየሱስም ቃል በቃል ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ አልተወለደም፥ ስለዚህ "ዘላለማዊ ውልደት" የሚለው የክርስትና ተስተምህሮት እንደዚህ ድባቅ ይገባል። መርየም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" ስትል አምላካችን አሏህ በመልአሉ፦ "አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ “ኹን” ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦
3፥47 ፦”ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፥ “ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ “ኹን” ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል” አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
 
አምላካችን አሏህ ነገርን መፍጠር በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ብሎ ወዲያውን የሚሆን ከሆነ ለእርሱ እምቅድመ ዓለም ሆነ ድኅረ ዓለም ከእከሌ የወለደው እርሱን የሚመስል እና የሚያህል የባሕርይ ልጅ የለውም፦
19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
 
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
 
✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
 
ወሠላሙ ዐለይኩም
 
 
[[ስዕል:Nicaea icon.jpg|320px|thumb]]
'''የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት''' በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የሚቀበል የ[[ክርስትና]] እምነት መግለጫ ነው።
Line 4 ⟶ 104:
እንዲያውም የዛሬው ጸሎት ከ[[ንቅያ ጉባኤ]] በኋላ፣ በ[[ቁስጥንጥንያ ጉባኤ]] የተዘጋጀው ነው። ሁለተኛው ጉባኤ አንዳንድ ቃላት በተለይም ስለ መንፈስ ቅዱስ በይበልጥ የሚገለጽ ቋንቋ ጨመረ። በመጀመርያውም እትም፣ መጨረሻው ዓረፍተ ነገር ሀረ ጤቆች ይወገዙ ይል ነበር፤ በዚህ ፈንታ አዲሱ ጸሎተ ሃይማኖት የ[[ጥምቀት]]፣ [[የሙታን ትንሳኤ]]ና ዘላለም ሕይወት እምነቶች ይጠቅሳል።
 
ከ372 ዓም ጀምሮ እስካሁን በምንም ሳይቀየር በ[[ተዋሕዶ]]፣ [[ምሥራቅ ኦርቶዶክስ]]፣ [[ሮማን ካቶሊክ]]ና [[ፕሮቴስታንት]] አብያተ ክርስቲያን ሁሉ በሙሉ ይቀበላል። [[ሞርሞኖች]] ወይም [[የይሆዋ ምሥክሮች]] ግን [[ሥላሴ]]ን የማይቀበሉ እምነቶች ናቸው።
 
==የሃይማኖት ጸሎት (የተሻለው 372 ዓ.ም. ቁስጥንጥንያ እንደ ተዘጋጀ)==