ከ«ኤስቶኒያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
Tags: Reverted Visual edit
መስመር፡ 24፦
ከፍተኛ_ደረጃ_ከባቢ = .ee
}}
[[ስዕል:Drone video of Estonia 2021.webm|thumb|ኤስቶኒያ 2021]]
'''ኤስቶኒያ''' በ[[ባልቲክ ባሕር]] ላይ የተገኘ አገር ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ ይኖሩበታል። መደበኛ ቋንቋቸው [[ኤስቶንኛ]] የ[[ፊንላንድኛ]] ዘመድ ነው። የኤስቶኒያ ብሔር ከጥንት ጀምሮ በአገሩ ኑረዋል። እስከ [[13ኛው ክፍለ ዘመን]] ድረስ [[አረመኔ]] አገር ነበረ፤ ያንጊዜ ክርስቲያን መስቀለኞች ያዙት። በ[[16ኛው ክፍለ ዘመን]] ከ[[ፕሮቴስታንት]] እንቅስቃሴና ከጦርነቶች በኋላ ኤስቶኒያ ለ[[ስዊድን]] ሥልጣን ወጣ፣ በ[[1713]] ዓ.ም. ወደ [[ሩስያ]] ተዛወረ። በዚህ ዘመን ሁሉ ግን እስከ [[1808]] ዓ.ም. ድረስ የኤስቶኒያ ሕዝብ ገበሬዎች ሆነው የ[[ጀርመን]] ገዢዎች ነበሩዋቸው። ጀርመኖች በ[[1ኛው ዓለማዊ ጦርነት]] ወርረው [[የሶቭየት ኅብረት]] በተነሣ ጊዜ ኤስቶኒያ ነጻ መንግሥት ሆነ። በ[[1932]] ዓ.ም. ግን የሶቭየት ኅብረት በግፍ ጨመረው። [[ዩናይትድ ስቴትስ]] ይህንን አድራጎት መቸም አልተቀበለም። የሶቭየት ህብረት በ[[1983]] ዓ.ም. በወደቀበት ዘመን ኤስቶኒያ ዳግመኛ ነጻ ሪፐብሊክ ሆነ። ፓርላማውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲሞክራስያዊ ምርጫ ይመረጣሉ። በ[[1996]] ዓ.ም. [[የአውሮፓ ኅብረት]] እንዲሁም የ[[ናቶ]] አባል ሆነ። ከ[[2003]] ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ ገንዘቡ [[ዩሮ]] ሆኗል።