ከ«ኤርትራ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ፋይሉ «Map_of_Eritrea_under_Ethiopia_rule.jpg» ከCommons ምንጭ በP199 ዕጅ ጠፍቷል! ምክንያቱም፦ per c:Commons:Deletion requests/File:ETHIOPIA political.jpg
መስመር፡ 143፦
 
=== የኤርትራ ምክር ቤት ===
 
[[ስዕል:Map of Eritrea under Ethiopia rule.jpg|280px|thumb|በኢትዮጵያ አገዛዝ ሥር የኤርትራ ካርታ]]
[[የኤርትራ ምክር ቤት]] (ባይቶ ኤርትራ) በእንግሊዞች አቀናባሪነትና አገር አቀፍ ምርጫ መጋቢት 1952ዓ.ም. ሲመሰረት በዚሁ ወቅት የኤርትራን ህገ መንግስትና የፌደሬሽኑን ደንብ አጸደቀ። እንዲሁም አቶ [[ተድላይ ባይሩ]]ን እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ና አቶ [[አሊ አህመድ ሙሳ ረዳይ]]ን እንደ ፕሬዜዳንት አድርጎ መረጠ። በዚያው አመት መስከረም ላይ የኢትዮጵያም መንግስት እንዲሁ ሁለቱን አጸደቀ። መስከረም 15 ላይ የአስተዳደሩ ሃይል ወደ ፌዴራል መንግስት ተዛወረ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያውም ሆነ የኤርትራው ውገኖች ለራሳቸው በሚስማማ መልኩ የፈዴሬሽኑን ደንቦች በመተርጎም ቀስ በቀስ የፖለቲካ ውጥረት ተነሳ። የአንድነት ደጋፊ የነበሩት አቶ [[ተድላ ባይሩ]] 1953 ላይ የፖለቲካ ተቃውሚዎቻቸው [[ወልደ አብ ወልደ ማርያም]]ንና [[አብርሃ ተሰማ]]ን በመወንጀል ጥቃት ጀመሩ። የ[[አንድነት ፓርቲ]] አቶ ተድላ ባይሩን በመደገፍ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ጋር ማዋሃድ አላማው አድርጎ ተነሳ። እኒህ የአንድነት ደጋፊዎች በመንግስት ቢሮዎች ለየት ያለ ስራ የማግኘት እድል ስላገኙ የተገንጣይ ሃይሎች (የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) እጅግ ተበሳጩ። በተለይ በእስላማዊው ምዕራብ ኤርትራ ግንባሩ ከፍተኛ ድጋፍን ማግኘት ጀመረ። የኢኮኖሚው እየወደቀ መሄድ፣ የግብር መጨመርና የቁሳቁሶች ዋጋ መጨመር ለውጥረቱ መባባስ አስተዋጽኦ አደረጉ። በዚህ ወቅት ኤርትራ የምታስገባውና የምታስወጣው ዕቃ ላይ 25% የግብር ጭማሪ ተደርጎ ነበር። የጣሊያን ዜጎችም በጦርነቱ ያጡትን የኢንደስትሪ፣ ማዕድን ማውጣት፣ እርሻ ወዘት መብቶች ከእንደገና በማግኘታቸው አገሬው ህዝብ እንዲበሳጭ ካደረጉት ጉዳዮች አንዱ ነበር።