ከ«የሎናይፍ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''የሎውናይፍ''' ([[ዶግሪብኛ]]፦ ሶምባኬ) በ[[ካናዳ]] [[ስሜን-ምዕራብ ግዛቶች]] ውስጥ ዋና ከተማ፣ እንዲሁም አንድያ ከተማ ነው። ከ[[ስሜናዊ ክበብ]] 400 ኪ.ሜ (250 ማይል) በስተደቡብ፣ በ[[ታላቅ ስለይቭ ሐይቅ]] ስሜን ዳርቻ ላይ፣ በ[[የሎውናይፍ ስላጤ]] ምዕራብ ላይ፣ በ[[የሎውናይፍ ወንዝ]] አፍ አጠገብ ይገኛል።
 
የ«የሎው ናይፍ» ትርጉም ከ[[እንግሊዝኛ]] «ቢጫ ቢላዋ» ሲሆን ይሄው ስያሜ በዙሪያው ከሚገኙት [[ዴኔ]] ኗሪዎች ደረሰ፣ እነሱም የ«ቢጫ ቢላዎች» ወይም የ«መዳብ» (የሎውናይቭዝ ወይም ኮፐር) ዴኔ ጥንታዊ ሕዝብ ተብለዋል። እነዚህ በ[[አርክቲክ ውቅያኖስ]] አካባቢ ከተገኘው [[መዳብ]] ማዕድን ወስደው ዕቃዎችንም ሰርተው ይነግዱበት ነበርና። የከተማው ሕዝብ ቁጥር ባለፈው [[2008]] ዓም ቆጠራ 19,569 ሰዎች ነበር። ከስሜከስሜን-ምዕራብ ግዛቶች አስራ አንድ ይፋዊ ቋንቋዎች መካከል፣ ፭ቱ በብዛት በየሎውናይፍ ሊሰሙ ይቻላል፤ እነሱም [[ቴኔ ሱጢኔኛ]]፣ ዶግሪብኛ፣ [[ስለይቪኛ]]፣ እንግሊዝኛ እና [[ፈረንሳይኛ]] ናቸው። የከተማ ስም በዶግሪብኛ «ሶምባኬ» ማለት «ገንዘቡ ያለበት» ነው። አሁን የ[[የሎውናይቭዝ ዴኔ]] ብሔር አባላት በአቅራቢያው ባሉት በ[[ዲሎ]] እና በ[[ደታህ]] ሠፈሮች ይገኛሉ።
 
[[ወርቅ]] በአቅራቢያው ከተገኘ በኋላ በ[[1926]] ዓም የተቋቋመው ሲታመን፤ ሆኖም በውሃ ዳርቻ ዙሪያ የንግድ እንቅስቃሴ እስከ [[1928]] ዓም ድረስ አልተጀመረም። ከዚያ በቅርቡም የሎውናይፍ የግዛቶቹ የንግድ እንቅስቃሴ ማዕከል ሆነ፤ በ[[1959]] ዓም ደግሞ የሰሜናዊ ምዕራብ ግዛቶች መቀመጫ ከተማ ሆኖ ተሰየመ። በ[[1980ዎቹ እ.ኤ.አ.]] ላይ የወርቅ ምርት እያለቀ፣ የሎውናይፍ የማዕድን ከተማ ከመሆኑ የመንግሥት አገልግሎት መኃል ወደ መሆን ተሸጋገረ። ሆኖም በ[[1983]] ዓም [[አልማዝ]] ከከተማው ስሜን ከተገኘበት ጀምሮ፣ ይሄ ለውጥ ይመለስ ጀመር። ባለፉት ቅርብ ዓመታትም ላይ፣ [[ቱሪዝም]]፣ [[መጓጓዣ]]፣ እና [[ኮሙኒኬሽን]] ዋና የየሎውናይፍ ኢንዱስትሪዎች ለመሆን ጀምረዋል።