ከ«የሎናይፍ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''የሎውናይፍ''' ([[ዶግሪብኛ]]፦ ሶምባኬ) በ[[ካናዳ]] [[ስሜን-ምዕራብ ግዛቶች]] ውስጥ ዋና ከተማ፣ እንዲሁም አንድያ ከተማ ነው። ከ[[ስሜናዊ ክበብ]] 400 ኪ.ሜ (250 ማይል) በስተደቡብ፣ በ[[ታላቅ ስለይቭ ሐይቅ]] ስሜን ዳርቻ ላይ፣ በ[[የሎውናይፍ ባሕር ስላጤ]] ምዕራብ ላይ፣ በ[[የሎውናይፍ ወንዝ]] አፍ አጠገብ ይገኛል።
 
የ«የሎው ናይፍ» ትርጉም ከ[[እንግሊዝኛ]] «ቢጫ ቢላዋ» ሲሆን ይሄው ስያሜ በዙሪያው ከሚገኙት [[ዴኔ]] ኗሪዎች፣ እነሱም የ«ቢጫ ቢላዎች» ወይም የ«መዳብ» (የሎውናይቭዝ ወይም ኮፐር) ዴኔ ጥንታዊ ሕዝብ ተብለዋል። እነዚህ በ[[አርክቲክ ውቅያኖስ]] አካባቢ ከተገኘው [[መዳብ]] ማዕድን ወስደው ዕቃዎችንም ሰርተው ይነግዱበት ነበርና። የከተማው ሕዝብ ቁጥር ባለፈው [[2008]] ዓም ቆጠራ 19,569 ሰዎች ነበር። ከስሜ-ምዕራብ ግዛቶች አስራ አንድ ይፋዊ ቋንቋዎች መካከል፣ ፭ቱ በብዛት በየሎውናይፍ ሊሰሙ ይቻላል፤ እነሱም [[ቴኔ ሱጢኔኛ]]፣ ዶግሪብኛ፣ [[ስለይቪኛ]]፣ እንግሊዝኛ እና [[ፈረንሳይኛ]] ናቸው። የከተማ ስም በዶግሪብኛ «ሶምባኬ» ማለት «ገንዘቡ ያለበት» ነው። አሁን የ[[የሎውናይቭዝ ዴኔ]] ብሔር አባላት በአቅራቢያው ባሉት በ[[ዲሎ]] እና በ[[ደታህ]] ሠፈሮች ይገኛሉ።