ከ«ሰፍነግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

31 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
No edit summary
 
 
ጥልቅ በሆነ ባሕር ውስጥ የሚገኘውና [[የቬነስ አበባ ቅርጫት]] እየተባለ የሚጠራው የሰፍነግ ዝርያ ስፔኪዩሎችን ተጠቅሞ በጣም ውብ የሆነ የአበባ ጥልፍ መሥራት ይችላል። እነዚህ እንደ ብርሌ የጠሩ የመስታወት ቃጫዎች ለስልክ ማስተላለፊያ የሚያገለግሉትን ዘመናዊ ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶች ይመስላሉ። አንድ ሳይንቲስት “እነዚህ ሕያው ቃጫዎች በጣም ጠንካራ ናቸው” ብለዋል። አክለውም “በኃይል ብትቋጥራቸው እንኳ እንደ ሰው ሠራሾቹ ቃጫዎች አይበጠሱም” በማለት ተናግረዋል። እነዚህ ውስብስብ ቃጫዎች በባሕር ውስጥ እንዲሁም ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ባለበት አካባቢ እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ሳይንቲስቶች በውል ሊረዱት አልቻሉም። የቤል ቤተ ሙከራ ባልደረባ የሆኑት [[ቼሪ ሙሬይ]] “በዚህ መንገድ፣ ውስብስብነት የሌለው ይህ ፍጥረት ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶችንና እንደ ሴራሚክ ያሉ ነገሮችን በመሥራት ረገድ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አገልግሏል” ብለዋል።<ref>በአውስትራሊያ የሚገኘው ''የንቁ!'' ዘጋቢ</ref>
 
[[መደብ:እንስሳት]]
505

edits