ከ«አገው ምድር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
 
መስመር፡ 218፦
ነፍስ ባይኖራቸውም በዱር በገደሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት
ለተዋደቁ ፈረሶች ምስጋና ይሆናል፡፡
=የአዊ ብሔረሰብ =
አዊ ብሔረሰብ
አስተዳደር አካባቢዎች
ለተለያዩ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ክዋኔዎች
ቀዳሚ ሚና
የሚጫወተው ፈረስ
ነው።
ፈረስ እርሻ በማረስ
የነዋሪዎችን ገቢ
ያሳድጋል፣ በአካባቢው
እንግዳ ከመጣ
የሚታጀበው በፈረስ ነው፣
ዓመታዊ ኃይማኖታዊና
ዓለማዊ በዓላት
የሚደምቁት በፈረስ ነው፣
ሠርግና ለቅሶ በአዊ
ያለፈረስ የማይከወኑ
ማህበራዊ ጉዳዮች
ናቸው።
• ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር
ባህል አልባሳቶቻችን
በየዓመቱ ጥር 23
የሚከበረው "የሰባት ቤት
አገው ፈረሰኞች ማኅበር"
ደግሞ የአዊ ብሔረሰብና
ፈረስ ያላቸውን ዘመን
ያስቆጠረ ቁርኝት
የሚያንጸባርቅ ኩነት ነው።
ማኅበሩ ታዲያ እንዲሁ
"በማኅበር እናቋቁም"
ምክክር የተመሰረተ
አይደለም። ታሪካዊ
ጅማሮውን 120 ዓመታትን
ወደኋላ ተጉዞ ከአድዋ
ጦርነት ይመዝዛል።
አለቃ ጥላዬ የማኅበሩ
ሊቀ መንበር ናቸው።
እርሳቸው እንደሚሉት
በ1888 ዓ.ም በተደረገው
የአድዋ ጦርነት
ኢትዮጵያዊያን አርበኞች
ወደ አድዋ የተጓዙትም
የተዋጉትም በፈረስ ነው።
በሁለተኛው የጣሊያን
ወረራም ወቅትም ፈረስ
ተመሳሳይ የአርበኝነት
ተጋድሎ ውስጥ ተሳትፎ፤
ከአምስት ዓመታት
ፍልሚያ በኋላ ጣሊያንን
ድል መንሳት ተችሏል።
በዚህ ሂደት ታዲያ ፈረስ
በብዛት ለጦርነቱ
ከተሳተፈባቸው ስፍራዎች
መካከል የአዊ አካባቢዎች
አንዱ ነበር።
ይህ በመሆኑም "የፈረስና
የአርበኛ ውለታው ምን
ይሁን" የሚል ሃሳብ ተነስቶ
የአካባቢው አረጋዊያን
ምክክር አድርገው
"በአድዋ፤ በኋላ
በነበረውም የአምስት
ዓመት የአርበኝነት ዘመን
አጥንታቸውን ለከሰከሱት
አርበኞችና ፈረሶች
እንዲሁም በድል
ለተመለሱት መታሰቢያ
ለማድረግ ሲባል ማኅበሩ
በ1932 ዓ.ም በሃሳብ
ደረጃ ተጠንስሶ በዓመቱ
1933 ዓ.ም በይፋ
ተቋቋመ" ይላሉ አለቃ
አሳዬ።
የፈረስ ጉግስ በአካባቢው
ለዓመታት የተለመደ
ቢሆንም በኃይማኖታዊ
በዓላት ላይ ወጣቶች
ውድድር አድርገው
ታዳሚውን ያስደምማሉ፤
በግልቢያ ችሎታቸው
ጉልምስናቸውን ያሳያሉ
እንጂ በተደራጀ መልኩ
የሚደረግ ዓመታዊም ሆነ
ወርሃዊ ውድድር
እንዳልነበረው አለቃ
ጥላዬ ይናገራሉ።
በኦሮምኛና
በትግርኛ አፋቸውን
የፈቱ የአማርኛ ሥነ
ጽሑፍ ባለውለታዎች
የ75 ዓመቱ አዛውንት
አለቃ አሳዬ ተሻለ
ከታዳጊነት የእድሜ
ዘመናቸው ጀምረው
አብዛኛውን እድሜያቸውን
በአገው ፈረሰኞች ማኅበር
ውስጥ አሳልፈዋል።
አባታቸው ግራዝማች
ተሻለ የማኅበር ምስረታ
ሃሳቡን በማመንጨትና
ማህበሩን በማቋቋም
ረገድ ስማቸው ከሚነሳ
ጥቂት ሰዎች መካከል
አንዱ መሆናቸውን
ያስታውሳሉ።
የፎቶው ባለመብት, AWI
የምስሉ መግለጫ,
የአዊ ፈረሰኞች
በወቅቱ የአሁኑ አዊ
ብሔረሰብ አስተዳደር
ባንጃና አንከሻ የሚባሉ
ሁለት ወረዳዎች ነበሩት።
አርበኞች ጣሊያንን ካባረሩ
በኋላ የፈረስንና
የአርበኞችን ገድልና ውለታ
ለመዘከር ከባንጃ ወረዳ
16 ሰው፤ ከአንከሻ ወረዳ
16 ሰው በድምሩ 32
ሰው ሆነው የሰባት ቤት
አገው ፈረሰኞች ማህበርን
በ1933 ዓ.ም
መመስረቱን ይገልጻሉ።
"በጊዜው በዓመት ሁለት
ጊዜ እንዲከበር ተወስኖ
የነበረ ሲሆን ሚያዚያ 23
እና ጥቅምት 23 ደግሞ
በዓሉ የሚከበርባቸው
ቀናት ነበሩ" በማለት አለቃ
አሳዬ የሰባት ቤት አገው
ፈረሰኞች ማኅበርን
ታሪካዊ ዳራውን
ይተነትናሉ።
የኬንያ ዳኞችን
አለባበስ የቀየረች
ኢትዮጵያዊት
ማኅበሩ በተቋቋመበት
ወቅት የፈረስ ጉግስ
በማድረግና የቅዱስ
ጊዮርጊስን ማሕበር
በመጠጣት እንደተጀመረ
የሚናገሩት አለቃ አሳዬ፤
ማህበሩን ያቋቋሙትም
ከባንጃ ወረዳ አለቃ
መኮንን አለሙና
ግራዝማች ንጉሤ፤
ከአንከሻ ወረዳ ደግሞ
ቀኛዝማች ከበድ ንጉሤና
ግራዝማች ተሻለ (የአለቃ
አሳዬ አባት) መሆናቸውን
ይናገራሉ።
በበዓሉ የተመረጡ ሰጋር
ፈረሶች በተለያዩ አልባሳት
አሸብርቀው ይቀርባሉ።
ፈረሶቹ ለበዓሉ ማድመቂያ
ብቁ መሆናቸው
በአካባቢው ሰዎች
ተረጋግጦ የተሻሉት ብቻ
ለበዓሉ ይጋበዛሉ።
ከሁሉም አካባቢዎች
የመጡ ልምድ ያላቸው
ጋላቢዎች ደግሞ በጉግስ፣
ሽርጥና በሌሎች
የውድድር ዓይነቶች
እነዚህን ፈረሶች
በመጋለብ፤ በታዳሚው
ፊት ልክ በጦርነት ወቅት
ፈረሶች እንደነበራቸው ሚና
በማስመሰል ትርዒት
ያሳያሉ፤ በውድድሩ አሸናፊ
የሆኑትም ሽልማት
እንደሚበረከትላቸው
የማኅበሩ ሊቀመንበር
አለቃ ጥላዬ ያስረዳሉ።
የፎቶው ባለመብት, AWI
የምስሉ መግለጫ,
የአዊ ፈረሰኞች
በዓሉ በዚህ ሁኔታ ለብዙ
ዓመታት በዓመት ሁለት
ጊዜ እየተካሄደ ከቀጠለ
በኋላ፤ የማኅበሩ አባላት
እየበዙ በመምጣታቸውና
በዝግጅቱ ውበትም ብዙ
ሰው እየተማረከ
በመምጣቱ ሰፋ ባለ
ዝግጅት በዓመት አንድ
ጊዜ ብቻ እንዲከበርና
ቀኑም ጥር 23 እንዲሆን
ተወስኖ በየዓመቱ በዚሁ
ዕለት እየተከበረ
እንደሚገኝ አለቃ ጥላዬ
ለቢቢሲ በሰጡት መረጃ
አረጋግጠዋል።
የብስክሌት
ጀልባ የሠራው
ወጣት
በታሪክ በዓሉ
የተከበረባቸው ሦስቱም
ቀናት በተለያዩ ወራት
ቢሆንም '23' በመሆናቸው
ግን ልዩነት የለም። ለዚህ
ደግሞ አለቃ ጥላዬ ዋነኛ
ምክንያት ብለው
የሚያስቀምጡት፤ በአድዋ
ጦርነት ወቅት የቅዱስ
ጊዮርጊስ ታቦት ወደ
ቦታው ተጉዞ ነበር
ስለሚባል፤ ቀኑ
የተመረጠው የቅዱስ
ጊዮርጊስን መታሰቢያ
ዕለት ምክንያት በማድረግ
ነው ይላሉ።
በ32 አባላት የተጀመረው
የፈረሰኞቹ ማኅበር ዘንድሮ
በ80ኛ ዓመቱ የአባላት
ብዛቱን 53 ሺህ 2 መቶ
21 ማድረሱን ሊቀ
መንበሩ አለቃ ጥላዬ
ተናግረዋል።
የማኅበሩ አባል ለመሆን
ጾታ የማይለይ ሲሆን
በእድሜ በኩል ከ18
ዓመት በላይ መሆን እና
በአካባቢው ማሕበረሰብ
ዘንድ የተመሰከረላቸውና
ምስጉን መሆን ብቻ ብቁ
ያደርጋል። ከአባልነት
የሚጠየቀው መዋጮም
በዓመት 8 ብር ብቻ ነው
ይላሉ አባላቱ።
የአዊ ብሔረሰብ
አስተዳደር በዘጠኝ
ወረዳዎችና በሦስት ከተማ
አስተዳደሮች የተዋቀረ
ነው። ሁሉም ወረዳዎችና
የከተማ አስተዳደሮች
"የሰባት ቤት አገው
ፈረሰኞች ማኅበር" አባል
መሆናቸውን የአዊ ባህልና
ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ
አቶ መለሰ አዳል
ያስረዳሉ።
• ጣልያን በተሸነፈችበት
አድዋ ቆንስላዋን ለምን
ከፈተች?
በዓሉ በእነዚህ ወረዳዎች
በየዓመቱ በየተራ
ይዘጋጃል የሚሉት አቶ
መለሰ ተረኛ የሆነ ወረዳ
ለበዓሉ ታዳሚ ባህላዊ
ምግቦችንና በዓሉ
በሚከበርበት ወቅት
ተሳታፊ የሚቀመጥበትና
ተወዳዳሪዎች
የሚጋልቡበት የመጫወቻ
ሜዳንም ያዘጋጃል
ብለዋል።
ዛሬ እየተከናወነ ያለው
80ኛው የአገው ፈረሰኞች
በዓልም በተለያዩ
የብሔረሰቡ አካባቢዎች
ሲካሔድ ቆይቶ
የማጠቃለያ ፕሮግራሙ
በ2 ሺህ ፈረሶች
አማካኝነት በእንጅባራ
ከተማ እየተከበረ መሆኑን
ኃላፊው አስታውቀዋል።
የአካባቢው ሕዝብ በዓሉን
በጉጉት ይጠብቀዋል።
በበዓሉ የሚታዩ ትርኢቶች
ተመልካችን ያስደምማሉ።
ፈረስ ጋላቢዎች በሺዎች
ለሚቆጠሩ ታዳሚያን
ችሎታቸውን ለማሳየት
ብቸኛዋ ቀን ጥር 23 ናት።
የፎቶው ባለመብት, AWI
የምስሉ መግለጫ,
የአዊ ፈረሰኞች
አምና በውድድሩ
የተሸነፈው ዘንድሮ
ለማሸነፍ፣ አሸናፊው
ደግሞ አሸናፊነቱን
ለማስቀጠል የሚያደርገው
ትንቅንቅ፤ ፈረሶች በኋለኛ
ሁለቱ እግሮቻቸው ብቻ
ቀጥ ብለው ሲቆሙ ማየት
ታዳሚያን በዓሉን
እንዲናፍቁ ከሚያደርጉ
ትዕይንቶች መካከል አንዱ
ነው።
አለቃ አሳዬ አባታቸው
በመሰረቱት የፈረስ
ማኅበር ውስጥ
ተወዳዳሪም የማህበሩ
የበላይ ጠባቂም በመሆን
ከግማሽ ክፍለ ዘመን
በላይ አሳልፈዋል።
ዘንድሮም በ75 ዓመት
የእድሜ ዘመናቸው፤ 80ኛ
የማህበሩን በዓል
ለማክበር እንጅባራ
ተገኝተዋል።
በ1962 ዓ.ም አለቃ አሳዬ
መኖሪያቸውን ከአንከሻ
ወደ ቻግኒ ቀይረዋል፤
በአዲሱ የመኖሪያ
አድራሻቸውም ላለፉት 50
ዓመታት በበዓሉ ግንባር
ቀደም ፈረስ ጋላቢ
በመሆንና ማኅበሩን
በማጠናከር የማይተካ
አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ
ቆይተዋል።
ሰክሮ በፈረስ
ግልቢያ ውድድር ላይ
የተሳተፈው ታሰረ
እርሳቸው ከሚኖሩበት
ቻግኒ ከተማ በዓሉ
እስከሚከበርበት እንጅባራ
ያለው ርቀት 60 ኪሎ
ሜትር የሚጠጋ ነው።
ይህንንም ርቀት
ፈረሳቸውን ጭነው
ባለፉት 50 ዓመታት
ሲጓዙት ኖረዋል።
ዘንድሮም ዕድሜ
ሳይገድባቸው ይህንን 60
ኪሎ ሜትር ርቀት በ4
ሰዓታት በሰጋር ፈረሳቸው
ተጉዘው እንጅባራ
ተገኝተዋል።
"ሚሊዮን ብር ሰጥተው
ከፈረስ ማኅበሩ በዓል
እንድቀር አማራጭ
ቢሰጠኝ ዝግጅቱ ላይ
መገኘትን እመርጣለሁ"
የሚሉት አንድም ቀን
ከበዓሉ ተለይተው
የማያውቁት አለቃ አሳዬ
ዛሬም ለውድድር
ባይሆንም ፈረስን እንዴት
በቄንጥ መጋለብ
እንደሚቻል በማሳየት
ታዳሚን ጉድ ሊያስብሉ
ተዘጋጅተዋል።
• በአውስትራሊያ ፈረሶች
እየታረዱ ነው በሚል
ውንጀላ ላይ ምርመራ
ተጀመረ
በአሁኑ ወቅት የበዓሉ
አድማስ ከአካባቢው
ማህበረሰብ አልፎ በአገር
አቀፍ ደረጃ ቦታ
የሚሰጠው ሆኗል።
በየዓመቱ በርካታ የአማራ
ክልል ባለስልጣናትና
ነዋሪዎች በዓሉን
ለመታደም ወደ አካባቢው
ይተማሉ።
ከክልሉ ውጭ የሚገኙ
ነዋሪዎችና የመንግሥት
የሥራ ኃላፊዎችም
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
በበዓሉ ተማርከው ጥር
23ን በአገው ምድር
እንጅባራ ማሳለፍን
ምርጫቸው እያደረጉ
ነው።
በዘንድሮው በዓልም
ምክትል ጠቅላይ
ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣
የባህልና ቱሪዝም
ሚንስትሯ ሂሩት ካሳው
(ዶ/ር) እና ሌሎች በርካታ
የፌደራልና የክልል
ባለስልጣናትም የበዓሉ
ተሳታፊዎች ናቸው።