ከ«የቶሪኖ ከፈን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Removing Link FA template (handled by wikidata) - The interwiki article is not featured
ዓ/ም
 
መስመር፡ 2፦
'''የቶሪኖ ከፈን''' ወይም መከፈኛ ጨርቅ የተሰቀለ ሰው ምስል የሚታይበት ጥንታዊ በፍታ ነው። ዛሬ የሚገኘው በ[[ቶሪኖ]] [[ጣልያ]] ባለበት ቤተ ክርስትያን በመሆኑ «የቶሪኖ ከፈን» ይባላል። ይሄው በፍታ በመቃብር ውስጥ ሲቆይ [[ኢየሱስ ክርስቶስ]]ን የከፈነው እንደሆነ በሱም ላይ ምስሉ በተአምር እንደተቀረጸ የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም። ሌሎች ግን የጥርጣሬ ባሕርይ ይዘው ይህን ሳይቀበሉ በሰው ልጅ ሰዓሊነት እንደ ተፈጠረ ባዮች ናቸው። ስለዚህ ከበፍታው የተነሣ ብዙ ክርክሮች ሲደረጉበት ውለዋል።
 
ከሁሉ የሚያስገርመው ዕድሜው [[ካሜራ]] ወይም [[ፎቶ]] የማንሣት ዕውቀት መቸም ከኖረ ምናልባት ወደ 1800 ዓመታት በፊት የሚጠጋው ምስል እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ በመሆኑ ሲሆን፡ ምስሉ መጀመርያ በግልጽ የታየበት ወቅት በ[[ግንቦት 21]] ቀን [[1890]] ዓ.ም. [[ሴኮንዶ ፒያ]] የተባለ አንድ የፎቶ አንሺ ፎቶውን ካነሣ በኋላ ያነሣው ፎቶ በታጠበ ጊዜ ኔጋቲቩን አይቶ በዚያን ጊዜ ምስሉ እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ እንደሆነ ተረዳ። ከ[[1818]] ዓ/ም አስቀድሞ ስለ ፎቶ ኔጋቲቭ ምንም ዕውቀት አለመኖሩ እርግጠኛ ነው። ሆኖም ይህ በፍታ በታሪክ መዝገብ ቢያንስ ከ[[1349]] ዓ.ም. መገኘቱ ደግሞ እርግጠኛ ነው። ስለዚህ ምስሉን በተመለከተ በቀላል የማይመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ቀርተዋል።
 
:ደግሞ ይዩ፦ [[የጄኖቫ ቅዱስ መልክ]]