ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 164፦
የኣንድኣንድ የቦታዎች ስሞችም እየተለዋወጡ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ምሳሌ በረራ [https://ethiopianege.com/archives/4463]
 
======የቋንቋዎች ፊደላት======
 
ከግዕዝ በፊት የደኣማቱ ቅድመ-ግዕዝ (Proto-Ethiopic) ፊደል ነበር። [https://enacademic.com/dic.nsf/enwiki/7349877] ግዕዝ (Ethiopic) የሚለው ቃል ሁለት ትርጕሞች ኣሉት። ኣንደኛው የግዕዝ ቋንቋ ስም ሲሆን ሌላው የፊደሉ (Script) [https://en.wikipedia.org/wiki/Ge%27ez_script] ነው። የግዕዝን ፊደል የሚጠቀሙት የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለሞች ኣሏቸው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደሉን ብቻውን ሲጠቀም ቆይቶ ሌሎች ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለማትን ጨምረውበት ተስፋፍቷል ይባላል። [https://www.merriam-webster.com/dictionary/Ethiopic] ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ብዙ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ ቢጋሩም ሁሉም የእየራሳቸው ብቻ የሆኑ ቀለማት ኣሏቸው። ቢሆንም ግዕዝ የሁሉም ተጠቃሚ ቋንቋዎች የፊደል ስምም ነው። ከእነዚህም መካከል ብዙ ተጠቃሚዎች የኣሉት የዓማርኛ [http://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A3%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B_%E1%8D%8A%E1%8B%B0%E1%88%8D] ፊደል ነው። የዓማርኛው ፊደልም በቅርቡ የተጨመረለትን የ“ቨ” ቤት ጨምሮ ከ፸ በላይ የግዕዝ ቋንቋ የሌለውን እነ “ሸ”፣ “ቸ”፣ “ኘ”፣ “ጀ”፣ “ጨ”፣ “ኸ”፣ “ዠ” እና ሌሎችንም ቀለማት ያካትታል። (ይህ ገለጻ ዓማርኛ የኣልሆነውን የታይፕራይተር ፊደል ስለማይመለከት ቅጥልጥል ፊደሉም ግዕዝ ኣይደለም።) ስለዚህ ዓማርኛ የሚጠቀመው በእራሱ ፊደል ነው። ይህ ኣገላለጽ የሌሎች ቋንቋዎች ፊደላትንም ይመለከታል። ለምሳሌ ያህል ሁሉም የዓማርኛ ቀለሞች የትግርኛው ውስጥ እንደሌሉት ሁሉም የትግርኛ ቀለሞች (ለምሳሌ “ቐ”) ዓማርኛው ውስጥ የሉም። ኣንዳንድ ሰዎች በስሕተት ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል (Amharic Alphabet) የኣለው ቋንቋ [https://en.wikipedia.org/wiki/Ge%27ez_script] ነው። የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። የግዕዝ ወይም Ethiopic የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ኦሮሞም የእራሱ የግዕዝ ፊደል ኣለው። እንዲሁም ሁሉም የኦሮሞ ፊደላት (ምሳሌ “ዸ”) የዓማርኛው ውስጥ የሉም። የኤርትራው ቢለንና የጎጃሙ ኣገው ቋንቋዎች ፊደላት ቀለሞች ኣንድ ዓይነት ናቸው። ጉራጌኛ ሰባቱንም ቤቶች ያጠቃልላል። [https://am.wiktionary.org/wiki/Wiktionary:%E1%8C%89%E1%88%AB%E1%8C%8D%E1%8A%9B_%E1%88%B7%E1%8B%B4%E1%88%BD]