ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 319፦
፩. እንደ ኤውሮጳ ኣቆጣጠር ማጠር ያለበት በ“እ.ኤ.ኣ.” እንጂ “እ.ኤ.ኣ” ማድረግ ከሚገባው በታች ማሳጠር ነው። ኣንድ ሰው በስሕተት የተጠቀመበትን ኣሠራር ሌሎቻችን በሚገባ ሳናስተውል መከተል የለብንም። “ኣ” ጎን ነጥብ ከኣሌለ “ኣ” ብቻውን እንዳለ ቃል መቆጠሩ ስለሆነና ኣጠቃቀሙም ትክክል ስለኣልሆነ ቋንቋ ሲበላሽ ዝም ብሎ መመክልከት ተገቢ ነው? ፪. “ዓመተ ምሕረት” ማጠር ያለበት በ“ዓ.ም.” እንጂ “ዓ/ም” ያሳስታል። የእዝባር ጥቅም እንደ “ወይዘሮ” የሚጻፉትን ቃላት በ“ወ/ሮ" ለማሳጠር እንጂ ሁለት ቃላትን ለማሳጠር ኣይመስልም። ፫. የ“ሊቅ” ብዙ “ሊቆች” ወይም “ሊቃውንት” እንጂ “ሊቃውንቶች” የሉንም። እዚህ ላይ በተለይ ከግዕዝ የመጡ ቃላት ላይ መጠንቀቅ ሳይጠቅም ኣይቀርም። ኣባላት፣ መምህራን፣ መኳንንት የመሳሰሉ ቃላት የብዙ ቍጥሮች ናቸው። ፬. ሞክሼ ቀለሞች የተለያዩ ጥቅሞች የኣሏቸው ለግዕዝ ቋንቋ እንጂ ለዓማርኛ ኣይደለም የሚባለው ትክክል ኣይደለም።
 
፭. ዌብ (Web) ድር፣ ዌብፔጅ (Webpage) ድረገጽ ወይም ገጸድር ነው። ድህረገጽ ከገጽ በኋላ ስለሆነ ትክክል ኣይደለም። ይህ ስሕተት ምን ያህል እንደተስፋፋ ለማስተዋል ድህረገጽ፣ ድኅረገጽ እና ድሕረገጽ ቃላት ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ መመልከት ይቻላል።ይቻላል።ድሕር ማለት ኋላ ነው። Website ድረገጽ ነው። ስለዚህ ድሕረገጽ Website ኣይደለም። ፮. የ“ው” ድምጽ ሳድስ እንጂ ካዕቡ “ዉ” ስለኣልሆነ “ነው” መከተብ ያለበት በሳድሱ ነው። ዓማርኛ “ዉ” የሚጠቀምባቸው ብዙ ቃላት ስለሌሉት መጠንቀቅ ጠቃሚ ነው። ፯. “[[ጊዜ]]” እንጂ “ግዜ” ዓማርኛ ኣይደለም። ፰. ኣንዳንድ ደራስያን “እ” ቀለምን መቀነስ ይወዳሉ። “ተእኛ” እና “ተኛ” እንዲሁም “የእርሷ” እና “የርሷ” የተለያዩ ናቸው።
 
፱. ኣራት ነጥብ (“።”) እራሱን የቻለ ኣንድ የግዕዝ የምልክት ቀለም ነው። ኣንዳንድ ደራስያን ምልክቱን ከሁለት ባለሁለት ነጥቦች (ነቊጦች) ወይንም በእንግሊዝኛ ኮለን (“Colon”) መክተብ ስለጀመሩ ይህ ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ኣስፈላጊ ያልሆኑ ሁለት መርገጫዎች በማስጨመር ጊዜና ስፍራ የሚያስባክን ግድፈት ነው። ከሁለት ቀለሞች የተሠሩትን ለመሠረዝም ሁለት መሠረዣዎች ያስፈልጋሉ። ኣራት ነጥቦች የሌሉት ጽሑፍም ችግር ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ፲. ዶክተሩ የእንግሊዝኛው ኮለን ለግዕዝ እንዲጠቅም ያደረጉት በኮለንነት ስለሆነ የግሉ የዩኒኮድ ቊጥር ከኣለው ባለሁለት ነጥብ (ወይም ነቊጥ) የባዶ ስፍራ የግዕዝ ምልክታችን ጋርም ኣንድ ኣይደለም። ኣራት ነጥብን ከሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች (“፡”) በኮምፕዩተር መክተብም ግድፈት ነው። ምክንያቱም ይህ ኣሠራር ኣራት ነጥቦች ከሌሉት የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ የመጣ የኣሠራር ችግር ስለሆነ [http://web.archive.org/web/20120107191057/http://www.ethiopic.com/Rabies_in_Amharic.pdf] እንጂ ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች ኣራት ነጥቦች የሚሆኑበት ኣከታተብ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ዶክተሩ ከተከላከሉት ኣንዱ የጎደለ ኣጠቃቀም ነው። [http://sirius-c.ncat.edu/eas/news/EJSciTech/abera2.html] በሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲት በኮምፕዩተርና ግዕዝኤዲት በእጅ ስልክ የግዕዝ ኣራት ነጥብ ምልክት የተከተበውና እየተከተበ የኣለው በሁለት መርገጫዎች (“ዝቅ 3”) ነው። በግዕዝ ዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንደሚታየው [http://unicode.org/charts/PDF/U1200.pdf] እና እዚህ ጎን ላይ የኣለው ሥዕል እንደሚያሳየው ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ሁለት ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ኢትዮጵያውያንም ኣራት ነጥብን በማያስከትብ ፕሮግራም መጠቀም የለባቸውም። ፲፩. የመጽሓፎች ይዘት (Contents) እና ማውጫ (Index) የተለያዩ ናቸው። ፲፪. የኣንዳንዶች ስሕተቶች ምንጮች የተሳሳቱ ፊደላት ወይም መክተቢያዎች ናቸው፦ ምሳሌ “ቍጥር”ን በ“ቁጥር” መጻፍ።