ከ«ኤዎስጣጤዎስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
መስመር፡ 36፦
 
==ያደረጉት መንፈሳዊ አስተዋጾ==
ኤዎስጣጤዎስ ከአባ ዳንኤል የቅስና መዐረጋቸውን ካገኙ በኋላ የራሳቸውን ደብር በ([[:en:Serae|ሰራይ]]) መሠረተው በዚያም በማስተማር ብዙ ተማሪዎችን አፈሩ ። በሰንበት ላይ ያተኮረ አመለካከታቸውን ለይተው ያስተምሩ ነበር ፣ የሚቃወማቸው አቡነ ያቆብ ፫ኛው አስኪመጣ ድረስ። ከዛ ግን ከተከታዮቻቸው ከባካርሞስ ፣ መርቆርዮስ ፣ ገብረእያሱ ጋር ኢትዮጵያን ለቀው ወደ [[ግብፅ]] (ካይሮ) ገብተው በአሌክሳንድሪያው ጳጳስ ቢንያም ፪ኛው ፊት በሰንበት ባላቸው አመለካከት ፀንተው ከዛም ወደ [[ኢየሩሳሌም]] አምርተው በመጨረሻም የሕይወታቸው ማብቂያ ወደ ሆነችው አርሜኒያ ገብተው ኖሩ<ref>ታሪካቸው በኢትዮጵያ [http://www.stmichaeleoc.org/Synaxarium/Archive.htm የእንግሊዘኛ ሥንክሳር] ወይም በ[[https://play.google.com/store/apps/details?id=patristicpublishing.eth Ethiopian Synaxarium ]] [[(ጉግል ፕሌይ ስቶር ይገኛልላይ በሚገኘው አፕ.)]] በመስከረም ፲፰ የሰማዕታትና ቅዱሳን ታሪክ ውስጥ ይነበባል</ref>።
የኤዎስጣጤዎስ የሰንበት አመለካከት የሚከተለው ነበር፡ ቅዳሜና እሁድ ፡ዝቅተኛውና ዋናው ሰንበት ፣ የቅዳሜው ለብሉይ ኪዳን ሲሆን የእሁዱ ደግሞ [[ኢየሱስ|ለጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ]] ለ[[አዲስ ኪዳን]] ማለት ነው ። ይህንንም ከመጻሕፍ ቅዱስ ከአሥርቱ ቃላትና ከአዲስ ኪዳን ተረድተው እንጂ የገዛራሳቸው አመለካከት እንዳልነበር የሃይማኖት ታሪክ ዘጋቢዎች<ref>ታደሰ ታምራት Church and State in Ethiopia (Oxford: Clarendon Press, 1972), page 209</ref> ያስታውቃሉ ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም የሁለቱንም ቀን ሰንበትነት አክብራ ትጠቀምበት ነበር ፣ በተወሰነ ጊዜ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ስሕተት ነው ብላ እንዲቀር እስካረገቺው ቀን ድረስ ማለትም ከኤዎስጣጤዎስ መነሳት በፊት ።