ከ«የሐዋርያት ሥራ ፯» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
መስመር፡ 59፦
የአብርሃም፡አምላክ፣የይሥሐቅም፡አምላክ፣የያዕቆብም፡አምላክ፡ነኝ፡ብሎ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።ሙሴም፡
ተንቀጥቅጦ፡ሊመለከት፡አልደፈረ
33፤ጌታም፦የቆምኽባት፡ስፍራ፡የተቀደሰች፡ምድር፡ናትና፥የእግርኽን፡ጫማ፡አውልቅ።
34፤በግብጽ፡ያሉትን፡የሕዝቤን፡መከራ፡ፈጽሜ፡አይቼ፡መቃተታቸውንም፡ሰምቼ፡ላድናቸው፡
ወረድኹ፤አኹንም፡ና፥ወደ፡ግብጽ፡እልክኻለኹ፡አለው።
35፤ሹምና፡ፈራጅ፡እንድትኾን፡የሾመኽ፡ማን፡ነው፧ብለው፡የካዱትን፥ይህን፡ሙሴን፡በቍጥቋጦው፡
በታየው፡በመልአኩ፡እጅ፡እግዚአብሔር፡ሹምና፡ቤዛ፡አድርጎ፡ላከው።
36፤ይህ፡ሰው፡በግብጽ፡ምድርና፡በቀይ፡ባሕር፡በምድረ፡በዳም፡አርባ፡ዓመት፡ድንቅና፡ምልክት፡እያደረገ፡
አወጣቸው።
37፤ይህ፡ሰው፡ለእስራኤል፡ልጆች፦እግዚአብሔር፡ከወንድሞቻችኹ፡እንደ፡እኔ፡ያለ፡ነቢይ፡
ያስነሣላችዃል፤ርሱን፡ስሙት፡ያላቸው፡ሙሴ፡ነው።
38፤ይህ፡ሰው፡በሲና፡ተራራ፡ከተናገረው፡መልአክና፡ከአባቶቻችን፡ጋራ፡በምድረ፡በዳ፡በማኅበሩ፡ውስጥ፡
የነበረው፡ነው፤ይሰጠንም፡ዘንድ፡ሕይወት፡ያላቸውን፡ቃላት፡ተቀበለ፤
39፤ለርሱም፡አባቶቻችን፡ሊታዘዙት፡አልወደዱም፤ነገር፡ግን፥ገፉት፡በልባቸውም፡ወደ፡ግብጽ፡ተመለሱ፤
40፤አሮንንም፦በፊታችን፡የሚኼዱ፡አማልክት፡ሥራልን፤ይህ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣን፡ሙሴ፡ምን፡እንደ፡
ኾነ፡አናውቅምና፡አሉት።
41፤በዚያም፡ወራት፡ጥጃ፡አደረጉ፡ለጣዖቱም፡መሥዋዕት፡አቀረቡ፥በእጃቸውም፡ሥራ፡ደስ፡አላቸው።
42፤እግዚአብሔር፡ግን፡ዘወር፡አለ፡የሰማይንም፡ጭፍራ፡ያመልኩ፡ዘንድ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥በነቢያትም፡
መጽሐፍ።እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፥አርባ፡ዓመት፡በምድረ፡በዳ፡የታረደውን፡ከብትና፡መሥዋዕትን፡
አቀረባችኹልኝን፧
43፤ትሰግዱላቸውም፡ዘንድ፡የሠራችዃቸውን፡ምስሎች፡እነርሱንም፡የሞሎክን፡ድንኳንና፡ሬምፉም፡የሚሉትን፡
የአምላካችኹን፡ኮከብ፡አነሣችኹ፤እኔም፡ከባቢሎን፡ወዲያ፡እሰዳችዃለኹ፡ተብሎ፡እንዲህ፡ተጽፏል።
44፤እንዳየው፡ምስል፡አድርጎ፡ይሠራት፡ዘንድ፡ሙሴን፡ተናግሮ፡እንዳዘዘው፥የምስክር፡ድንኳን፡ከአባቶቻችን፡
ዘንድ፡በምድረ፡በዳ፡ነበረች፤
45፤አባቶቻችንም፡ደግሞ፡በተራ፡ተቀብለው፡እግዚአብሔር፡በፊታቸው፡ያወጣቸውን፡የአሕዛብን፡አገር፡
በያዙት፡ጊዜ፡ከኢያሱ፡ጋራ፡አገቧት፥እስከዳዊት፡ዘመንም፡ድረስ፡ኖረች።
46፤ርሱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሞገስ፡አግኝቶ፡ለያዕቆብ፡አምላክ፡ማደሪያን፡ያገኝ፡ዘንድ፡ለመነ።
47፤ነገር፡ግን፥ሰሎሞን፡ቤት፡ሠራለት።
48-50፤ነገር፡ግን፥ነቢዩ፦ሰማይ፡ዙፋኔ፡ነው፥ምድርም፡የእግሬ፡መረገጫ፡ናት፤ለእኔ፡ምን፡ዐይነት፡
ቤት፡ትሠራላችኹ፧ይላል፡ጌታ፥ወይስ፡የማርፍበት፡ስፍራ፡ምንድር፡ነው፧ይህንስ፡ዅሉ፡እጄ፡የሠራችው፡
አይደለምን፧እንዳለ፥ልዑል፡የሰው፡እጅ፡በሠራችው፡አይኖርም።
51፤እናንተ፡ዐንገተ፡ደንዳናዎች፥ልባችኹና፡ዦሯችኹም፡ያልተገረዘ፥እናንተ፡ዅልጊዜ፡መንፈስ፡ቅዱስን፡
ትቃወማላችኹ፤አባቶቻችኹ፡እንደ፡ተቃወሙት፡እናንተ፡ደግሞ።
52-53፤ከነቢያትስ፡አባቶቻችኹ፡ያላሳደዱት፡ማን፡ነው፧የጻድቁንም፡መምጣት፡አስቀድሞ፡የተናገሩትን፡
ገደሏቸው፤በመላእክት፡ሥርዐት፡ሕግን፡ተቀብላችኹ፡ያልጠበቃችኹት፡እናንተም፡አኹን፡ርሱን፡አሳልፋችኹ፡
ሰጣችኹት፥ገደላችኹትም።
54፤ይህንም፡በሰሙ፡ጊዜ፡በልባቸው፡በጣም፡ተቈጡ፡ጥርሳቸውንም፡አፋጩበት።
55፤መንፈስ፡ቅዱስንም፡ተሞልቶ፡ወደ፡ሰማይ፡ትኵር፡ብሎ፡ሲመለከት፡የእግዚአብሔርን፡ክብር፡ኢየሱስንም፡
በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ቆሞ፡አየና፦
56፤እንሆ፥ሰማያት፡ተከፍተው፡የሰው፡ልጅም፡በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ቆሞ፡አያለኹ፡አለ።
57፤በታላቅ፡ድምፅም፡እየጮኹ፡ዦሯቸውን፡ደፈኑ፥ባንድ፡ልብ፡ኾነውም፡ወደ፡ርሱ፡ሮጡ፥
58፤ከከተማም፡ወደ፡ውጭ፡አውጥተው፡ወገሩት።ምስክሮችም፡ልብሳቸውን፡ሳውል፡በሚሉት፡ባንድ፡ጐበዝ፡
እግር፡አጠገብ፡አኖሩ።
59፤እስጢፋኖስም፦ጌታ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ነፍሴን፡ተቀበል፡ብሎ፡ሲጠራ፡ይወግሩት፡ነበር።
60፤ተንበርክኮም፦ጌታ፡ሆይ፥ይህን፡ኀጢአት፡አትቍጠርባቸው፡ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ።ይህንም፡
ብሎ፡አንቀላፋ።ሳውልም፡በርሱ፡መገደል፡ተስማምቶ፡ነበር።