ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

7 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
 
===ጥሬ ሥጋ===
ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዕድል በኣገኙ ቍጥር ችሎታቸውን ለሌሎች ከማስተማርና ስለሚያውቁት ከማስረዳት ኣይቆጠቡም። ለምሳሌ ያህል በ፳፻፭ ዓ.ም. ከኣንድ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. የዓማርኛ [[ሬድዮ]] ጣቢያ ጋር ስለ [[ጥሬ]] ሥጋ (Raw meat) ገለጻ ኣድርገው ነበር። ኢትዮጵያውያን ጥሬ ሥጋ ከሚበሉ ሕዝቦች መካከል ስለሆኑ [https://ethiopianfood.files.wordpress.com/2014/12/christmas-dinner-1902-with-menelik1.pdf] [https://munchies.vice.com/en_us/article/ethiopians-are-risking-salmonella-to-eat-raw-meat-delicacies] ኣትብሉ ማለት ብቻ ትክክል ስለኣልሆነ የሚያዋጣው በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ ነው። [http://www.kingcounty.gov/depts/health/environmental-health/food-safety/facts/raw-labeling.aspx] [http://www.voanews.com/a/health-risks-fail-to-deter-ethiopians-from-eating-raw-meat/1753640.html] [http://www.who.int/mediacentre/factsheets/fs399/en/] [http://www.bbc.com/news/magazine-35581830] በኣሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው [[ከብት]] በየቦታው እየታረደ ይበላ ስለነበረ [[ዩናይትድ እስቴትስ]] (ኣሜሪካ) ውስጥ እንዲቀር ተወስኖ በ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. ፌዴራል ድንጋጌ የኣልተመረመረና ንጹህ ያልሆነ ሥጋ ለሕዝብ ማቅረብ ክልክል ነው። [http://www.fsis.usda.gov/wps/portal/fsis/topics/rulemaking/federal-meat-inspection-act] ሕጉን ኣለማወቅ መከላከያ ኣይደለም። ሥጋው የተመረመረ ለመሆኑ ማሕተሙን ማየት ያስፈልጋል። እንዲህም ሆኖ ኣንድ ሰው የእራሱን [[እንሰሳ]] ኣሳድጎና ኣርዶ ሳያስመረምር ቤተሰቡን ብቻ የማብላት መብት ኣለው።
 
ጥሬ ሥጋ ጀርሞች ኣሉት። ስለዚህ የሚከተሉትንም ማወቅ ጠቃሚ ነው። [https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%88%AC#.E1.8B.A8.E1.89.A0.E1.88.AC_.E1.8C.A8.E1.8C.93.E1.88.AB] ፩. ኣንድ እንሰሳ ሲታረድና ቆዳው ሲገፈፍ ጀርሞች በተለያዩ ሁኔታዎች ሥጋው ውጭ ላይ ስለሚቀሩ ያንን ማስወገድ ኣይቻልም። ቆዳ ሲገፈፍ ቢላው እንዲጸዳ ሙቅ [[ውሃ]] ውስጥ እየተነከረ ነው። ፪. እንደ [[ባክቴሪያ]] የኣሉ ጀርሞች በእየ20 ደቂቃዎች ሁለት በመሆን ይራባሉ። ይኸን እርባታ [[ቅዝቃዜ]] ያዘገየዋል። ስለዚህ እንሰሳው እንደታረደ ሥጋው ጥቅም ላይ ከኣልዋለ ሁልጊዜ መቀዝቀዝ ወይም መፈረጅ (ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ) ኣለበት። ለብዙ ጊዜ መቀመጥ ከኣለበት ሥጋው ከውሃ በረዶ ቅዝቃዜ በኣነሰ ወይም መፈረዝ (ፍሪዘር መግባት) ኣለበት። ፫. ኣንድ እንሰሳ ከመታረዱ በፊትና ከታረደ በኋላ በእንስሳት ሓኪም መታየት ኣለበት። ሓኪም ከሌለ ረዳት ሓኪሞች ወይም በሥጋ ምርመራ የሰለጠኑ ኣይተው ኣጠራጣሪውን ለእንስሳት [[ሓኪም]] የሚያቆዩበት መዘጋጀት ኣለበት። ምክንያቱም ሓኪሞች ብቻ የሚያውቋቸው ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ ብዙ በሽታዎች ስለኣሉ ነው። [https://pubs.ext.vt.edu/400/400-460/400-460.html] [http://www.doh.wa.gov/YouandYourFamily/IllnessandDisease/AnimalTransmittedDiseases] [http://www.who.int/zoonoses/neglected_zoonotic_diseases/en/] [http://en.wikipedia.org/wiki/Tapeworm_infection] [http://www.ethiomedia.com/17file/2564.html]
Anonymous user