ከ«የወፍ በሽታ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
የወፍ በሽታ በእንግሊዘኛው ደግሞ ጀውንዳይስ (jaundice) የሚባለው ራሱን የቻለ አንድ በሽታ ሳይሆን የብዙ በሽታወች ምልክት ነው። የወፍ በሽታ የሚከሰተው በደማችን የሚገኜው ቢሊሩቢን (bilirubin) የተባለው ከሚካል መጠን ሲጨምር ነው። ይህ ከሚካልም ለቆዳችንና ለአይናችን ነጭ ክፍል ቢጫ ወይም ቢጫማ አረንጛደ ቀለም ይሰጣቸዋል። ይህ ምልክት ብቻውን ወይም ከለሎች ምልክቶች ለምሳለ ማሳከክ፤ የሰገራ ቀለም ወደ ቢጫነት እና የሽንት ወደ ጥቁርነት መቀየር እና ሆድ ህመም በተለይም በቀኝ በኩል ጉበት አካባቢ ይገኙበታል። የወፍ በሽታ በሁሉም እድሚ ክልል (ከጨቅላ ህጻናት እስከ አዋቂወች) ያሉ ሰወችን ያጠቃል። የወፍ በሽታ በጨቅላ ህጻናት ላይ ብዙውን ጊዚ በተወለዱ በመጀመሪያው ሳምንት የሚከሰት ሲሆን የከፋ ጉዳትም አያደርስም።
 
የወፍ በሽታ ከቀላል እስከ ከባድ በሆኑ በሽታወች ምክኒያት ሊመጣ ይችላል። በጢነኛ ሠው ደም ውስጥ ያለው የቢሊሩቢን መጠን ከ፩ ሚግ/ደሊ (1mg/dL) ያነሰ ሲሆን ይህ ምልክት ባለባቸው ሰወች ግን በትንሹ ከ ፪ ነጥብ ፭ እስከ ፫ ሚግ/ደሊ ነው። በተጨማሪም ይህ ምልክት ጨቅላ ህጻናት ላይ ሲከሰት የቢሊሩቢን መጠን ከ ፭ሚግ/ደሊ ያላነሰ መሆኑን ያመለክታል። ከፍተኛ የቢሊሩቢን መጠን ያልተጣበቀ (ኢ-ቀጥተኛ - unconjugated) ወይም የተጣበቀ (ቀጥተኛ - conjugated) ቢሊሩቢን ሊሆን ይችላል። ያልተጣበቀ ቢሊሩቢን መጠን መጨመር የቀይ ደም ህዋሳቶች መሞትን ሲያመለክት የተጣበቀ ቢሊሩቢን መጨመር ደግሞ የጉበት ወይም የሃሞት መፍሰሻ ቦይ ህመምን ያመለክታል።
የወፍ በሽታ ህክምና እንደ አምጭው የበሽታ አይነት ይወሰናል። ይህም ከመድሃኒት እስከ ኦፕራሲዮን ድረስ ሊሆን ይችላል።
 
'''የወፍ በሽታ የሚያመጡ በሽታወች'''