ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 354፦
፴፫. የግዕዝ ፊደል ውስጥ ለሌሉ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፊደላችን ለሌሎች ቋንቋዎችና ፊደላትም እንዲጠቅም ያስችላል። ዓማርኛ ከግዕዝ የወረሳቸውን ቃላት እየተጠቀመ እየኣደገ ነው። ፊደላቱ እንዳይቀነሱ ከሚፈልጉት ኣንዱ ዶ/ር [[ኣምሳሉ ኣክሊሉ]] ናቸው። [http://ethiopiaforums.com/ethioforum/viewtopic.php?t=2031] ይህ በእንዲህ እንዳለ ግዕዝ ውስጥ የኣሉት በተናጠል እየቀጠሉ ሞክሼዎች የሚሆኑት ዓማርኛ ስለሆኑ የሚመስላቸው ኣሉ። ይህ እውነት ኣይደለም። ፴፬. ኢትዮጵያውያን ቀለሞቻቸውን ሳይቀንሱ በብራናና ማተሚያ ቤቶች ብዙ ደክመው በሚገባ ተጠቅመውባቸው ኣቆይተውናል። ይኸንኑ ፍላጎት ዶክተሩ በኮምፕዩተር ከማሳካት ሌላ ለዩኒኮድ ኣቅርበው የፊደሉ ፍላጎት ተሟልቷል። የግዕዝን ፊደል ሳይጽፍ የእንግሊዝኛውን የታይፕ መሣሪያ ዓማርኛን እንደጻፈ መቍጠርና ይኸንኑ በኮምፕዩተር መጠቀም እራስን ማታለል ነው። ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ከታይራይተር ጋር ጊዜው የኣለፈበት ኣስተሳሰብ ነው። ፴፭. በኣንድ በኩል ፊደል በዛ እያሉ በሌላ በኩል የሚጠብቅና የሚላሉ ቃላት ችግር ፈጥረዋል የሚሉ ኣሉ። [http://www.cyberethiopia.com/warka14/viewtopic.php?f=1&t=50680] የፊደል ቀናሾች ስንፍና [http://www.danielkibret.com/2013/11/blog-post_29.html] ወደ ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ስለገባና ኣንድኣንዱን ሰው ከሚገባው በላይ ቸልተኝነት ስለተጠናወተው መቀስቀስ ኣስቸግራል። ስለ ቴክኖሎጂ ኣንብቦ ከመረዳት ይልቅ በወሬ የተገኘውን ሶፍትዌር እየተጠቀመ ፊደል ሲጎድልበት መጠየቅ የማይችል ሆኗል። ፴፮. በተቀነሱ ቀለሞች የሚጠቀሙ ደራስያን ጽሑፎች ኢንተርኔት ላይ ተፈልገው ላይገኙ ስለሚችሉ እራሳቸውና ሥራዎቻቸውን ከጥቅም ውጪ እያደረጉ ናቸው።
 
፴፯. ሁለተኛው የሞክሼዎች ጥቅም ዓማርና ከሌሎች ሴማዊ ቋንቋዎች ጋር ያለውን ዝምድና ስለሚያመላክቱ ነው። [http://senamirmir.org/downloads/Homonyms-Note01.pdf] የዓማርኛ ሞክሼዎችን ለመለየት ከቃላቱ ብቻ ፍንጭ ማግኘት ስለሚቻል ምሳሌዎችን ከመሸምደድ ይልቅ መረዳት ሳይጠቅም ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። ለምሳሌ ያህል “ፀሓይ" የሚለ ቃል ውስጥ “ፀ" የጠበቀ ስለሆነ ፀሓዩን “ፀ" መጠቀም ይጠቅማል። “ንሥር"ና “ንስር"ን ለመለየት የቋንቋው ተናጋሪ በድምጽ ስለሚለያቸው “ንስር"ን ከእሳቱ “ሰ" ጋር በማያያዝ ኣገባቡን መለየት ይቻላል። ሌላ ምሳሌ “ምሥር" እና “ምስር" ሲሆን የጠበቀው እንደንጉሡ “ሠ” ባለ ንጉሡ “ሠ” “ምሥር" መሆኑ ነው። "ኣባይ"ና "ዓባይ" ኣጻጻፎቹም ሆኑ ኣነጋገሮቻቸው ኣንድ ስለኣልሆኑ ሞክሼ ናቸው የሚሏቸው ለመሳሳታቸው ምስክሮች ናቸው። “ዓባይ”ን ኣጥፍቶ እንደ “ኣ'ባይ” መጻፍ ሥፍራና መርገጫዎች በማስጨመር ያካስራል። “ኣባይ” እንዲሁ ወይም (Default) ያልጠበቀ ሲሆን “ዓባይ” እንደ ዓይኑ “ዐ” የጠበቀ ስለሆነ ኣነጋገሩን ከፊደሉ ማገናኘት ሳይጠቅም ኣይቀርም። የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ኃይማኖታዊ ነው የሚሉም ኣሉ። [http://gothenburggebriel.com/2015/09/21/%e1%88%9e%e1%8a%ad%e1%88%bc-%e1%8d%8a%e1%8b%b0%e1%88%8b%e1%89%b5/] "ዓይን"ና "ዓመት" የጠበቁ ናቸው ቢባል የወንዙን ስም በ"ኣባይ" የሚጽፉ ኣሉ። [http://senamirmir.org/downloads/Homonyms-List02.pdf] ፴፰. የሞክሼ ተብዬዎቹ መኖር ዓማርኛውን ኣዳበረው እንጂ ኣልጎዳውም። ይህ ፊደሉን የሚጠቀሙ ሌሎች ቋንቋዎችንም ሊመለከት ይችላል። የላቲን ፊደል ስለኣስቸገረ ፈረንጆች ኣዳዲስ ፊደላት እየፈጠሩ እያሻሻሉት ነው። ስለዚህ የወንዙን ስም “ኣባይ" ብሎ መጻፍ የእስፔሊንግ ችግር የሌለውን ዓማርኛ በእስፔሊንግ ማበላሸትም ነው። ፴፱. የሞክሼ ፊደል ጉዳይ ጊዜው የኣለፈበት ክርክር ነው። በኮምፕዩተር ዘመን ቴክኖሎጅው ችግሮቻችንን ስለሚፈታ ፊደል ለመቀነስ መከራከር ግዕዛዊ ኣይደለም። ትክክለኛዎች ቀለሞች ከሌሉ ወደፊት ኮምፕዩተሩን ማናገር ቀላል ኣይሆንም። ሞክሼዎችን በሚፈልጉና በማይፈልጉ መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች ሰዉ ላይ ሥራ ያበዛሉ። ፵. ኆኄያትን መጠበቅ ቅኔ ላይ ትንሽ ችግር ሊፈጥር ይችላል። [http://senamirmir.org/downloads/Homonyms-Note01.pdf] ፵፩. በቅርቡ በግዕዝ ፊደል መብዛት የተነሳ መዝገበ ቃላትን መጠቀም ኣስቸገረ በማለት ፊደል እንዲቀነስ የሚል መጽሓፍ ተጽፏል። [http://www.tigraionline.com/articles/language-reform-ethiopia.html] ይህ ጊዜው ያለፈበት ኣስተያየ ነው። ወደፊት ኣንድ የሚፈለግን ቃል ጽፎ ኮምፕዩተር ካለበት ያወጣዋል እንጂ መጽሓፍ ማገላበጥ ኣያስፈልግም።
በሌላ በኩል የዓማርኛን ሞክሼዎች መወገድ የሚፈልጉ ምክንያቶች ቢኖሯቸውም [https://dawitworku.wordpress.com/2013/09/25/%E1%8C%89%E1%8A%95%E1%8C%AD-%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%8D%8B%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B-%E1%8D%8A%E1%8B%B0%E1%88%8D-%E1%88%98%E1%89%80%E1%8A%90%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%88%88/] ኣንዳንዶቹ ከላይ ተጠቃቅሰዋል። ፩. ስድስት ዓይነቶች “ሀ”ዎች ቢኖሩም በሃሌታው “ሀ” እና እንዚራኖቹ ብንጠቀም የእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኈ”፣ “ኸ” እና “ዀ” እንዚራኖች ጭምር ድምፆች ኣንድ ዓይነት በመሆናቸውና ዓማርኛ ውስጥ ስለጠፉም ስለማያስፈልጉ የቀለሞች ቍጥር ይቀንሳል ነው። ፪. ሞክሼዎች ቢቀነሱ ግዕዝን ለመክተብ በሁሉም ቍልፎች መጠቀም ኣያስፈልግም የሚሉ ኣይጠፉም። ፫. የኣለነው ዓለም እየሰለጠነና ነገሮች እየቀለሉ በኣሉበት ዘመን ስለሆነ መቀነስ የምንችላቸው ስለኣሉ መጓተት ኣያስፈልግም የሚሉ ኣሉ። ፬. በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙ የተለያዩ ቋንቋዎች ድምፆችን የሚወክሉት ኣዳዲስ ቀለሞች ተሠርተው ሥራ ላይ ስለዋሉ የማያስፈልጓቸውን ሞክሼዎች ማስወገጃ ጊዜው ኣሁን ነው የሚሉ ኣይጠፉም።