ከ«የአድዋ ጦርነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 97፦
ዋነኛው ድል በጦር ግንባር ፍልሚያ የተገኘው ድል ነው፤ ታላቁ የአድዋ ድል፡፡
 
የአድዋ ጦርነት(የጥቁሮች የነፃነት ተምሳሌት) የተደረገው በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የተደረገው የመቅደላ ጦርነትም በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው የተካሄደው፡፡ በአድዋ ጦርነት ፆምና ውጊያ አብሮ ስለማይሄድ ግብፃዊውን ጳጳስ ሠራዊቱን ይፍቱትና እንደ ልቡ ይዋጋ ቢባሉም ባለመፍታታቸው ከኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት ጿሚ የሆነው እየፆመ ለመዋጋት ተገዶአል፡፡ በመቅደላ ውጊያ ዓፄ ቴዎድሮስ [ካሣ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ (አባ ታጠቅ ካሣ) (መዩሣው ካሣ) (ወሬሣው ካሣ)]  ሊወጋቸው ለመጣው እንግሊዛዊው ጄኔራል ናፒዬርና ሠራዊቱ ፆምህን ፈትተህ ከእኔ ጋር ውጊያ ግጠም ብለው አንድ ሺህ በጐች ልከውለታል፡፡
 
ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች አሉ፡፡ የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ የበዛ በመሆኑ፡- መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting Corporation) የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ኦሮሞ ቤተሠብ በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ መላ ነው፡፡