ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 242፦
 
===የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና===
ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በዓማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ኢንተርኔት ላይ ብዙ የሉም። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው ኢትዮጵያውያን ፊደላቸውን በመጻፊያ መኪና መሣሪያ (Amharic typewriter / አማርኛ ታይፕራይተር) [http://inventors.about.com/od/tstartinventions/a/Typewriters.htm] ለመጠቀም ተመራምረው ከደረሱበት ዘዴ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል (Ligature) የኢ/ር [[ኣያና ብሩ]] የ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. ገደማ ግኝት ሥራ ላይ ውሏል። [https://www.youtube.com/watch?v=RsyYs333M64&feature=youtu.be] በእዚህ የተነሳ ኢንጂነሩ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ሊቅ ናቸው። ከመቶ በታች መርገጫዎች የኣሉት የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች እንዲብቃቃ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል ኣስፈለገ። “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ኣሉ እንጂ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” እና “ሡ” ስለሌሉ የመቀነስ ምልክትን የመሰለ “-” ከሌላ መርገጫ በመክተብ “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ጎን በማስቀመጥ ቅጥሎቹ ካዕቦቹን ስለሚመስሉ ተመልካቹ እንዲቀበላቸው ሆነ። ኣንዱን መቀጠያ ብዙ ቀለሞች ሊጋሩት ስለሚችሉ የሁሉም ቀለሞች በኣለመኖር የተነሳ መርገጫዎች መቆጠብ ተቻለ። “ሃ” እና “ማ’ እንጂ “ሂ”፣ “ሚ”፣ “ሄ” እና “ሜ” ስለሌሉ “ሃ” እና “ማ” እግሮች ጎን መስመር ወይም ቀለበት በማስቀመጥ እነዚያን በሚመስሉ ቅጥሎች እንድንጠቀም ሆነ። እነ “ቻ”ን የመሰሉ ቀለሞች ከታችና ከላይ ከሁለት መርገጫዎች “ተ” ላይ በሚቀጠሉ ነገሮች ስፍራው ወደኋላ እየተመለሰ ሦስት ነገሮች ኣንድ ፊደል እንዲመስል ተሠሩ። ስፍራ ስለኣነሰ እንደነ “ኳ” ያሉ ቀለሞች “ካ” ስር በተቀመጠ መስመር በሚሠሩ ኣዳዲስ ቀለሞች ተተኩ። የ“ላ”ን ግራ እግር ማሳጠር ስለኣልተቻለ “ለ” ቀኝ እግር ላይ ከመስመር በታች በወረደ መቀጠያ የ“ለ” ቀኝ እግር ረዝሞ ያልተለመደ መልክ ይዞ ቀረበ። በመቀጠል ሊሠሩ ለማይችሉ ቀለሞች የእራሳቸው ስፍራ ሲሰጣቸው ቦታ ስለኣልበቃ ካልገቡት መካከል የዓማርኛ ኣራት ነጥብ ኣሉበት። [http://www.quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf] ስለዚህ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና የተመረኮዘውና ኣከታተቡ የተንፏቀቀ ፊደል በኣንድ የእንግሊዝኛ ገበታ ምትክ መቀጠል ላይ ነው። የዓማርኛ ቀለም ግን እየኣንድኣንዱ እራሱን የቻለ ስለሆነና ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለማይበቃው የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደል ዓማርኛ ኣይደለም። [http://sirius-c.ncat.edu/EAS/news/EJSciTech/abera2.html] ፊደላት ለኮምፕዩተር ሲሠሩ ተለያይተው እንዲቀርቡ ሲደረግ የታይፕራይተሮቹ ግን እንዲነካኩ ተንፏቅቀው የተሠሩ ስለሆኑ ቦታዎቻቸውን የኣልጠበቁም ናቸው። ይህ ሁሉ ሲደረግ እንደእነ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የመሳሰሉት ሲጠቀሙ የነበሩት በትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና [https://zarayakob.blogspot.com/2012/10/blog-post_9.html] በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ተጀምሮ በደርግ ዘመን የኣበቃ ቴክኖሎጂ ነው።
 
የዓማርኛ ፊደል የመክተቢያ ገበታና ዘዴ ስለ ኣልነበሩት ዶክተሩ ፊደሉን ወደ ኮምፕዩተር ሲያስገቡ ዘዴዎቹን ለመጀሪያ ጊዜ ከመፍጠር ሌላ [http://mezmur.altervista.org/%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B/] የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቅጥልጥል ፊደልና ኣከታተቡ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ጽፈዋል። [https://www.facebook.com/notes/403555123037729/] ኣንዳንዶቹም የቆዩና ኣዳዲስ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።