ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 336፦
የዓማርኛ ሞክሼዎችን ማስወገድ በሚከተሉት ምክንያቶች ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ፩. ሞክሼዎች ኣንድ ስለኣልሆኑ ኣንድ ናቸው ብሎ ኣንዱን ማንሳትና ሌላውን መጣል ከመነሻውም የተሳሳተ ኣስተሳሰብ ነው። ፪. የእነዚህ ሞክሼዎች ፊደላት ድምጾች እስከ ፲፭፻፴ ዓ.ም. ድረስ ማለትም እስከ ዓፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት ድረስ ተለይቶ ሲነገር ነበር። [https://eotcmk.org/a/%E1%88%9E%E1%8A%AD%E1%88%BC-%E1%8D%8A%E1%8B%B0%E1%88%8B%E1%89%B5/] ሞክሼ ቀለሞች ይቀነሱ የተባለው ኃሳብ የመጣው በታይፕ መኪና ዘመን መርገጫዎቹ ስለኣነሱ ነበር። የኣማርኛ የጽሑፍ መሣሪያ ዓማርኛ ስለኣልጻፈና ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ዲጂታይዝድ ስለሆነ የታይፕ መሣሪያውና ቅጥልጥል ቅርጾቹ ቀርተዋል። ኣሁን ሁሉም ቀለሞች ዲጂታይዝድ ስለሆኑ የዱሮ ችግሮችም መፍትሔ ኣግኝተዋል። መፍትሔ የፈጠሩትን ማመስገንና ሥራዎቻቸውን ማስተዋወቅ የጥቂቱ ብቻ መሆን የለበትም። ፫. የኣማርኛ ታይፕራይተር ፊደል የዩኒኮድ ፊደል እንዲሆን የሞከሩት በሳይንሳዊ መረጃ ተሸንፈው ቀርተው ትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ስዉ የሚያውቃቸው ቀለሞች ይቀነሱ ማለት የተማረውን ማስቸገር ስለሆነ ተገቢ ኣይደለም። ምክንያቱም እየኣንድኣንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ በኋላም ከኣንድ መርገጫ የተረፉት ኣብላጫዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የሚከተቡት በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ የሞክሼዎች መኖር የፈጠረው ችግር የለም። ኣንዳንዶቹ ሞክሼዎችን የሚከትቡት ከኣንድ የመርገጫ ቍልፍ ስለሆነ ኣንድኣንዱን ሞክሼዎች የሚከትቡት ብዙ መርገጫዎችን በመጠቀም ነው። ሞክሼዎችን የሚጠሉት የማያዋጣው መክተቢያዎቻቸውን ለመጥቀም ሊሆን ይችላል። ይህ በተለይ የዓማርኛውን ቀለሞች በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብ የሚፈልጉትን ይመለከታል። ፬. በስመ ሞክሼና መሻሻል ሞክሼዎች የኣልሆኑትን መቀነስ የፈለጉ ኣሉ። ምሳሌ፦ “ጐ”ን በ“ግወ” መተካት። ይህ ድምፃዊ ፊደላችንን ወደ ኣክሳሪው ፊደላዊ ፊደል በመቀየር ያዳክመዋል። የፊደል ጥቅም ቋንቋን ለመግለጽ እንጂ ለፊደል ኣጠቃቀም ሲባል ቋንቋን መቀየር ወይም መቀነስ ኣይደለም።
 
፭. የሞክሼዎቹ ማንነት በጥናት ላይ የተመረኰዘ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል መንትያ እንጂ ሞክሼዎች ኣይደሉም የሚሉ ኣሉ። [http://ethpress.gov.et/addiszemen/index.php/news/national-news/item/7054-2016-05-16-17-30-13] ፮. ሞክሼዎችን መቀነስ ጥቅም ቢኖረው ኖሮ የ“ከ" ቤት ድምጽን የሚጋሩትን “C” (“ሲ”)፣ “K” (“ኬ”) እና “Q” (“ኪው”) (ምሳሌ “Cake” እና “Queen” ወይም “ኬክ” እና “ኲን”) የላቲን ቀለሞች ተጠቃሚዎቻቸው ሊቀንሷቸውና ሦስቱንም በ“C” ብቻ መጠቀም በመረጡ ነበር። ይህ ኣስቸጋሪነቱን ለማመልከት የቀረበ ምሳሌ ነው። ፈረንጆች ለእነዚህ ቀለሞቻቸው የተለያዩ መርገጫዎች ቢመድቡም ለእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኸ”፣ የግሎቻቸው መርገጫዎች መመደብ ኣይገባም የሚሉ ኣሉ። ዶክተሩ ይገ‘ባል በማለት ይኸን ኣይደግፉም። ፯. ሞክሼዎች እንዲጠፉ ከመቸኰል ልዩነታቸውንና ጥቅሞቻቸውን ማስተማር ከምሁራን ይጠበቃል። ምሳሌ፦ [http://www.senamirmir.org/downloads/Homonyms-List02.pdf] [http://www.zoneniners.com/2012/10/AmharicSpelling.html] [http://gothenburggebriel.com/2015/09/21/%E1%88%9E%E1%8A%AD%E1%88%BC-%E1%8D%8A%E1%8B%B0%E1%88%8B%E1%89%B5/] [http://senamirmir.org/downloads/Homonyms-Note01.pdf] ኣለ። ፰. ሞክሼዎች የሌሉት ጽሑፍ ተለምዶ ሞክሼዎቹ ሊረሱ ይችላሉ። ሞክሼዎችን የማያውቋቸው ምሁራን የቆዩ ጽሑፎችን በሚገባ ላያውቁና ትርጕሞቻቸውን ላይረዱ ይችላሉ። ዶክተሩ የሠሩት የማጥበቂያና የማላልያ ቀለሞችም ላይጠቅሙ ይችላሉ። በቍጥሮቹ በኣለመጠቀም የተነሳ የግዕዝን ኣኃዞች የማይለዩ ምሁራን ኣሉ ይባላል።
 
፱. ምክሼዎችን የማይወዱ ጥቅሞቻቸውን መማር የማይፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ። የማይጽፉና ያልተሟሉ መክተቢያዎች የሚያቀርቡ ስለኣሉ ዘላቂ ችግሮችን ሲፈጥሩ ዛሬ መታገስ ኣስፈላጊ ኣይደለም። (የሞክሼዎች ኣለመኖር የፊደላቱን ቊጥሮች በማስቀነስ ኣከታተብ ቢያቀል'ም ኣማራጭ እንጂ ግዴታ መሆን የለበትም ባይ ናቸው ዶክተሩ። ምክንያቱም ኣማራጭነቱ አንደማያዋጣ ኣቅርቦ ማሳመን ስለሚቻል ነው።) ፲. ወደፊት በኮምፕዩተር እንድንራቀቅ ትክክለኛዎቹንና ሳይንሳዊ መሠረቶችን ስለፈጠርን ከሞክሼዎች መኖር ይልቅ ኣለመኖር ሊጎዳ ይችላል። ወደፊት ኮምፕዩተር ስለሚያስተካክለው የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ችግር ስለማይሆን የሚያስቸግሩት ቀለሞቹን የማያውቁት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት የኣናሳ ተናጋሪዎች ቋንቋዎች ቀለሞች የተሠሩት ሞክሼዎች የተባሉትን በመጠቀም ስለሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸውን የዓማርኛ ቀለሞች የማያውቁ ዓማርኛ ተናጋሪዎች መኖር ዓማርኛ ቋንቋንና ፊደሉን ይጎዷቸዋል እንጂ ኣይጠቅሙም። ስለዚህ በስመ ሞክሼ ዓማርኛውን ማዳከም ለዓለም ሕዝቦች ጭምር ጉዳት ነው። ፲፩. ኣንድ ጽሑፍ ሞክሼዎች በተባሉትም ይሁን በሌሎቹ ቢጻፍ ልዩነቶቻቸውን ለማያውቁ የሚፈጥሯቸው ችግሮች የሉም። ፲፪. ዓማርኛ የግዕዝ ቋንቋ ፊደል ላይ የሚያስፈልጉትን ኣዳዲስ ቀለሞች ጨመረ እንጂ የግዕዝን ፊደል ኣልቀነሰም። የግዕዝ ፊደል መክተቢያ ሁሉንም ቀለሞቹን ማስተናገድ የቴክኖሎጂው መጀመሪያ ነው። የኮምፕዩተር ቴክኖሎጂው የገላገለው የግዕዝን ቀለም ለዘመናት ሲለቅሙ የነበሩትን የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሠራተኞች ጭምር ነው። ይህ ጉዳይ የአማርኛ የታይፕ መጻፊያውን ኣይመለከትም።