ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

145 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
 
፳፭. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ኦሮምኛ 10 እንዚራን ሲያስፈልገው ግዕዝ ሰባት ብቻ ኣለው ይላሉ። ላቲን ኣምስት ዋየሎች ኣሉት ተብሎ ኣምስቱኑ ዋየሎች እየደራረቡ ኦሮምኛ ኣሥር ዋየሎች ኣሉት ማለት
ኦሮምኛውን መሳደብ ነው። ዋየል መደራረብም ትርፉ ስፍራ ማባከን ነው። የላቲን ዋየሎች ኣምስት ናቸው ቢባል እንኳን ለኦሮምኛ ኣምስት ዋየሎች በቂ ኣይደሉም። የቁቤ ዋየሎች ኣምስት ከሆኑ ከኣምስት በላይ እንዚራን ለኣላቸው የግዕዝ ቀለሞች ለመጠቀም ከላቲኑ ቁቤ የበዙ የእስፔሊንግ ችግሮች ይፈጥራል። [http://www.smart-jokes.org/english-spelling-reform.html] ለምሳሌ ያህል “ዸ”ን በስምንት ዋየሎቹ ለመክተብ ለቁቤ ላቲን ከ20 በላይ ቀለሞች ሲያስፈልጉት ለግዕዙ ፯ በቂ ናቸው። ፳፮. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት [https://www.ascii.cl/htmlcodes.htm] የግዕዙ ብዙ ናቸው ይላሉ። የላቲን "a" ዓይነቶች ከ26 በላይ ናቸው። ዋናዎቹ 26 የላቲን ቀለሞች እንደግዕዙ 37 የተሟሉ ኣይደሉም። የግዕዝ ፊደላት በ37 የግዕዝ ቤት ተከፋፍለው እንዚራኖቹ በድምጽና በቅርጽ በወጉ የተደረደሩ ስለሆነ ሕጻናትን ማስተማር እንደ “abcd” ቢሆንም የግዕዝ ተማሪ የሚማረው እስፔሊንግ እንዳያስታውስ እንጂ ዕድሜ ልኩን እስፔሊንግ እንዲፈልግ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤቶቹ ቀለሞች የሚከተቡት በግዕዞቹ ላይ ከቀኝ ጎን መስመር በመጨመር ሲሆን ድምጾቻቸው እንዲሰሙ ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ያስፈልጋል። ላቲን እራሱን ለማሻሻል ኣዳዲስ ፊደላትን እየቀረጸ ሲሆን ቁቤ ሊጠቀምባቸው ኣልተዘጋጀም። የቻይና ፊደላት ብዙ ቪህ ናቸው። [https://www.tutormandarin.net/en/how-many-characters-are-there-in-the-chinese-alphabet/] ፳፯. ግዕዝ በእጅ ኣይጻፍ ይመስል ስለላቲኑ የእጅ ጽሑፍ (Cursive) የሚያነሱም ኣሉ። ዶክተሩ ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተር ለመክተብ የሚያስፈልጉትን ከሠሩ በኋላ ለ24 ተነባቢና 10 ዋየሎቹ የኦሮምኛ ፊደላቱ 34 ቀለሞችን መፍጠር ስለሚያስቸግርና ኣስፈላጊ ኣይደለም ተብሎ ወደ ላቲን ዞርን ከቀረቡት ምክንያቶች ኣንዱ ነበር። ፳፰. ግዕዝ እንደኦሮምኛና ሲዳምኛ የኣሉትን (ኩሻዊ) ቋንቋዎችን [https://am.m.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB_%E1%89%8B%E1%8A%95%E1%89%8B%E1%8B%8E%E1%89%BD] [http://web.archive.org/web/20050206125215/http://www.worldscriptures.org:80/pages/sidamo.html] ጥሩ ኣድርጎ ኣይጽፍም የሚለው ወይም የግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም መወከል እንደችግር ተቆጥሮ ወደ ላቲን ለመዞር የቀረቡት ምክንያቶች ወደ እውነት የተጠጉ ኣልነበሩም። ግዕዝ ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለምና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ በማድረግ የተራቀቀ ፊደል ነው።
 
፳፱. በግዕዝና በላቲን የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ስለማይግባቡ በየእለቱ እየተራራቁ ናቸው። ኣንድ ሕዝብ [https://www.nazret.com/2017/03/04/ethiopia-adwa-when-oromos-fought-italy-as-abyssinians/] በተለያዩ ፊደላትና ቋንቋዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር። ኦሮሞው ዓማርኛና ፊደሉን እንዳይማር ተወስኖ የፌዴራል ሥራ እንዳያገኝ ሆኗል። ፴. ኣይርላንዳዊው በርናርድ ሿው ግዕዝን ዓውቆ ቢሆን ኖሮ ላቲን ቦታ ኣይኖረውም ነበር የሚል ጽሑፍ በሰይፉ ኣዳነች ቢሻው እዚህ ቀርቧል። [http://ethiopianege.com/archives/5408] የላቲን ፊደል ለእየኣንድኣንዱ ድምጽ ኣንድ ቀለም እንዲኖረው ተመኝተው ነበር። ላቲን የኣልተሟላና ኣክሳሪ ፊደል መሆኑንም ሿው ገልጸዋል። [http://www.digitalcomposition.org/essays-and-articles/george-bernard-shaw] ስለዚህ ባለቤቱ የጠላውን ኦሮሞው ኣዲስ ኣግበስባሽ መሆን የለበትም። ፴፩. ላቲን ማወቅ ኦሮሞዎችን ከፊደሉ ተጠቃሚዎች ያቀራርባል ተብሎ እንደምክንያት ቀርቧል። ኢትዮጵያውያን የላቲንን ፊደል ስለሚማሩ ኣልተጎዱም። ፴፪. በግዕዝ እንደኣስፈላጊነቱ መጠቀም እንዲቻል የማላልያ (Stretch) ምልክት የዶክተሩ ፓተንትም ውስጥ ተጠቅሷል። [https://patents.google.com/patent/US20090179778A1/en] የዩኒኮድ ግዕዝ መደብም ውስጥ ኣለ። ግዕዝ ኣንድን ቀለም ባለማጥብቅ፣ በማጥበቅና በማላላት ያስከትባል ይላሉ ዶክተሩ። [https://www.youtube.com/watch?v=7jLq0ZgpG_Y] ቁቤ የሚረዝሙ ድምጸ ልሳናትን የሚወክልበት ምልክት የለውም።
Anonymous user