ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

144 bytes added ፣ ከ8 ወራት በፊት
ኣንድ ፓተንት የኣለው ፈጣሪ በፈጠራው ላይጠቀም ወይም ውጤቱን ላይሸጥ ይችላል። ቴክኖሎጂ ዓለምን ስለኣቀራረበና በፍጥንት እያደገ ስለሆነ ፓተንት ማግኘት ቀላል ነገር ኣይደለም። በፓተንት የሚጠበቅ ግኝት መጀመሪያ ለመንግሥት እንጂ ለሕዝብ መቅረብ የለበትም። በግዕዝ ፊደል ለብዙ ሺህ ዓመታት ስንጠቀም ስለነበረ ኣጠቃቀሙም ሆነ ፊደሉ ኣዲስ ነገር ኣይደለም። ዶክተሩ የፓተንትን ጥቅም ቀደም ብለው ያውቁ ስለነበረ ቴክኖሎጂው እንደጀመረ በመረዳትና በማበልጸግ የሠሩት በሌሎች እንዳንቀደም ነበር። ቴክኖሎጂውንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚጋሩም በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለመንግሥት በጽሑፍ ቢገለጽም ስላልተባበሩ መብታቸውን ለማስጠብቅ ወደ ኣሜሪካ መንግሥት ስለተመለሱ ኣሜሪካም የኢትዮጵያ ባለውለታ ናት። ዶ/ር ኣበራ የግዕዝ ፓተንት ኣገኙ ማለት ሰዉ በፊደሉ እንዳይጠቀም ተደረገ ማለት ኣይደለም።
 
ሌላ የፓተንት ጥቅም ሌሎች ዓዋቂዎች ቀደም የኣሉትን እየጠቃቀሱ በማሻሻል ኣዳዲስ ፈጠራዎችን እንዲፈጥሩ ነው። የፓተንቶች በሌሎች መጠቀስ ለግኝቱ ፈጣሪ፣ ኩባንያና ኣገርም ክብር ነው። ለምሳሌ ያህል የዶ/ር ኣበራ ፈጠራዎች ከደርዘን በላይ የዓለም ፓተንቶችና ማመልከቻዎች ውስጥ ተጠቅሰዋል። የፓተንት መረጃዎችም ውስጥ ከግኝቱ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ሥራዎች በፈጣሪዎቹና መርማሪዎች ይጠቀሳሉ። በዶ/ር ኣበራ ሞላ ስምና በብቸኝነት እስከኣሁን (እ.ኤ.ኣ. 2018) የተሰጡዋቸው ፓተንቶች ቍጥር 9 ደርሰዋል። በኣሜሪካ ፓተንት የሚሰጠው ሰው ነዋሪነት (Citizen) እንጂ ዜግነት (Nationality) ኣይመዘገብም። ቍጥሩ 10,067,574 የሆነ ሦስተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የግዕዝ ፓተንት በቅርቡ ለዶክተሩ ተሰጥቷል። [http://patft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO1&Sect2=HITOFF&d=PALL&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsrchnum.htm&r=1&f=G&l=50&s1=10067574.PN.&OS=PN/10067574&RS=PN/10067574] በቅርቡም ቍጥሮቹ 74፣ 83 እና 193 የሆኑ የኢትዮጵያ ፓተንቶች ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ተሰጥተዋል።
 
ዶክተር ኣበራ ሌሎች ፓተንቶች እንዳሏቸው ቀደም ብሎ ተጠቅሷል። [https://archive.li/r1Est] [http://patft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO2&Sect2=HITOFF&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsearch-bool.html&r=1&f=G&l=50&co1=AND&d=PTXT&s1=Aberra&s2=Molla&OS=Aberra+AND+Molla&RS=Aberra+AND+Molla] እንዶድ ትላትልን እንደሚገድል በደረሱበት ትልቅ ኣስተዋጽዖዋቸው የኣሜሪካ ፓተንት በማግኘት የታወቁት ሌላው ኢትዮጵያዊ ዶ/ር [[ኣክሊሉ ለማ]] ናቸው። የኣሜሪካ ፓተንቶች ያሏቸው ኢትዮጵያውያንም እነዚህ ብቻ ኣይደሉም። የመጀመሪያው የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ከተሰጠበት 1790 ኤ.ዲ. ጀምሮ የኣሉት [https://en.wikipedia.org/wiki/Samuel_Hopkins_(inventor)] ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ።
Anonymous user