ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 464፦
፬. ኢ/ር ኣያና ብሩና ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ የዓማርኛውን ፊደላት በመቀነስና ቆርጦ በመቀጠል ኣማርኛ በመሰሉ የፈጠራ ቅርጾች የኣቀረቧቸው ሥራ ላይ ውለዋል። እነዚህ ቍርጥራጮች ግን የዓማርኛ ፊደሎች ኣይደሉም። ለእነዚህ ከመቶ በኣነሱ መቀጣጠያዎች የሚሠሩ የፈጠራ የኣማርኛ ነገሮች የሚያስፈልጋቸው ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለሆነ በኣንዱ ገበታ ምትክ ብቻ የቀረቡ ናቸው። የዓማርኛ ቀለሞች ብዛት ከ200 በላይ ስለሆነ 100 ስፍራዎች ኣይበቁትም።
 
፭. ኆኄያቸውን የጠበቁ የግዕዝና ዓማርኛ ጽሑፎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ተጽፈዋል። ፮. በእጅ ጽሑፍም ወረቀት ላይ መክተብ ለኢትዮጵያ ሕዝብና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጠቅሟል። [https://henokspad.wordpress.com/2012/09/30/ሞክሼ-የአማርኛ-ፊደላት-እና-የባለሙያዎች/] ፯. ፊደል መቀነስ ትኩረት የኣገኘው “ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፍ በተቀነሱ ፊደላት በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ከታተመ በኋላ ነበር። [http://www.cyberethiopia.com/warka14/viewtopic.php?t=50680] እዚህ ላይ ተደርቦ ለታይፕራይተር ቴክኖሎጂ እንዲመች የፊደል ቅነሳ ክርክር ተጀምሮ በመጨረሻው ውድቅ ሆነ። ፰. የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መርሐ ልሳን [ኣካዴሚ] በ1973 ዓ.ም. ካወጣው የአጻጻፍ ሥርዓት ውሳኔ በስተቀር ሌላ ወሳኝ ጥናት ባለመደረጉ፣ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ሊሆን የሚችሉ መምህራንንም ስለዚህ ጉዳይ ሆን ብሎ ያስተማራቸው ሰው ባለመኖሩ እነሱ ራሳቸው በዘፈቀደ ስለሚጽፉ ተማሪዎቻቸውም የነሱን ፈለግ በመከተል በዘፈቀደ ይጽፋሉ፤ የሚሉት ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ "የአማርኛን ሞክሼን ሆሄያት ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ" የሚባል መጽሓፍም ጽፈዋል። ሃሌታው “ሀ”፣ ሓመሩ “ሐ”፣ ብዙኃኑ “ኀ”፣ ንጉሡ “ሠ”፣ እሳቱ “ሰ”፣ ኣልፋው “አ”፣ “ዓይኑ” “ዐ”፣ ጸሎቱ “ጸ”፣ ፀሐዩ “ፀ” የተባሉትን በማጥበቅና በማላላት ብቻ ለመግለጽ ኣስቸጋሪ ነው።
 
እንደ ዶ/ር ኣምሳሉ ተፈራ ኣገላለጽ "ከፊደላት ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ኣስመልክቶም በዓማርኛ ፊደል ገበታ ላይ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ስለሚገኙ፤ በኣጻጻፍ ረገድ በርካታ ልዩነቶች መኖራቸው፤ ራብዕ ድምፅ ያላቸው ከግዕዙ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ፊደላት መኖራቸው፤ ሳድስና ሳልስን እያቀያየሩ መጠቀም፣ ዲቃላዎችንና ፍንጽቅ ፈደላትን በዝርዝር የመጠቀም ዝንባሌ፣ በመሠረታዊ ቃሉ ላይ የሌለውን ቃል መጨመር፣ የኣናባቢዎች ቅጥል ኣለመለየት ችግሩን ይበልጥ እንዳሰፋው ጠቁመዋል። [https://eotcmk.org/a/%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8b%93%e1%89%80%e1%8d%8d-%e1%8b%90%e1%8b%8d%e1%8b%b0-%e1%8c%a5%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%8a%ab%e1%88%94%e1%8b%b0/]