ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

36 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
 
፩. ጥንትም ቢሆን ፊደላት በእጅ ጽሑፍ ሲጻፉ ላቲን ከግዕዙ በፍጥነት የተከተበበት ጊዜ ኣልነበረም። ምክንያቱም ግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም ሲያሰፍር ለኣብዛኛው የላቲን ድምጾች ሁለትና ከእዚያም በላይ ቀለሞች ስለሚያስፈልጉት ነው። ፪. የላቲንና ግዕዝ ቀለሞች (ኦሮምኛውን ግዕዝ ጨምሮ) በማተሚያ መሣሪያዎች ሲከተቡ የሁለቱም ቀለሞች መረጣዎች ኣጠቃቀሞች እኩል ነበር። በእዚህ ዘዴ በግዕዝ ቋንቋ በ1513፣ [https://kingscollections.org/exhibitions/specialcollections/psalter1513/] [https://kingscollections.org/exhibitions/specialcollections/psalter1513/psalms1-50#Gallery[gallery1]/0/] ኦሮምኛ ዓማርኛ መተርጐሚያ (Lexicon) በግዕዝ ፊደል በ1850 ግድም በኣቶ ሓብተ ሥላሴ ታትሟል። [https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8D%8B%E1%8A%95_%E1%8A%A6%E1%88%AD%E1%88%9B_%E1%88%9B_%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0_%E1%89%83%E1%88%8B%E1%89%B5_1850] መጽሓፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ የመተርጐሙንም ሥራ በማስፋፋት ከሌሎች የቋንቋው ተናጋሪዎች ጋር (ዋሬ፣ ሩፎ፣ ሾለን፣ ጀገን እና ገብረሚካኤል) በመተባበር ሙሉውን ኣዲስ ኪዳን ወደ ኦሮምኛ ተርጕመው በሰኔ 1862 ዓ.ም. ኣገባደዱ። ይህም ትርጕማቸው ለኦሮምኛ ሥነጽሑፍ የመጀመሪያው ኣዲስ ኪዳን መሆኑ ነው። ከጥቂት ዓመታት በኋላም ሚስዮኑ ክራጵፍ ([[J.L. Krapf]]) በ፲፰፻፸፩ ዓ.ም. በራሱ ስም ያሳተመው ይህንኑ የነ[[ኣለቃ ዘነብ]]ን ፲፰፻፷፪ ዓ.ም. ሥራ “ቁልቁሎታ መጻፎታ ከኩ ሐረዋ” ነበር። [https://andemta.com/2017/06/26/%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%89%83-%e1%8b%98%e1%8a%90%e1%89%a5/] ኣለቃ ዘነብ ወደ ፲፰፻፸ ዓ.ም. ግድም የ“ኦሮምኛና ኣገውኛ መዝገበ ቃላት” ጽፈዋል ይባላል። የ[[ኣስቴር ጋኖ]]ን የትርጕም መጽሓፍ በመጠቀም በ፲፰፻፹፯ ዓ.ም. የታተመም የኦሮምኛ [[ሓዲስ ኪዳን]]፣ [https://en.wikipedia.org/wiki/Aster_Ganno] [[መጫፈ ቁልቁሉ]] በ፲፰፻፺፱ እ.ኤ.ኣ. (፲፰፻፺፪ ዓ.ም.) በቅዱስ [[ኦነሲሞስ ነሲብ]]፣ [https://en.wikipedia.org/wiki/Onesimos_Nesib]
[https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A6%E1%8A%90%E1%88%B2%E1%88%9E%E1%88%B5_%E1%8A%90%E1%88%B2%E1%89%A5] እና ከእዚያም ወዲህ እንደነ [[በሪሳ]] [https://www.press.et/Ama/?p=15303] የኣሉ ጋዜጣዎች በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ታትመዋል። መጫፈ ቁልቁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ቋንቋ የተጻፈ የፈረንጁ (King James Version) መጽሓፍ ቅዱስ ትርጕም ነው። ቀደም ብሎም በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ከቀረቡት መረጃዎች ኣንዱ [[ጀምስ ብሩስ]] የወሰደው የ1790 የኦሮምኛ ትርጕምና የ[[ቻርለስ ዊሊየም ኢዘንበርግ]] ጽሑፍም ኣሉ። [https://m.facebook.com/photo.php?fbid=1066288513502794&id=100003649675444&set=a.749136815217967.1073741828.100003649675444&source=57] ፫. በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ የሆነው ግዕዝ እ.ኤ.ኣ. በ1987 ለገበያ ቀርቦ በማተሚያ ቤቶች ፊደላት (ሞደት ፕሮግራም) መክተብ ስለተጀመረ ምሁራን ደስ ሊላቸውና ሳይንሱንና ቴክኖሎጅውን ማወቅና ማስተዋወቅ በተገባ ነበር። ይህ በኣለመደረጉ እ.ኤ.ኣ. በ1992 [http://www.ethiopians.com/bayeyima.html] በፕሮፌሰር [[ጥላሁን ጋሜታ]] ወደ ላቲን ለማዞር ከቀረቡት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናን የሚመለከቱት ጊዜ ለኣለፈባቸውና ኮምፕዩተርን የማይመለከቱ ምክንያቶች መልሶችም ነበሩ። [https://archive.li/WIjry] [https://www.facebook.com/notes/geezedit/advances-made-by-ethiopians-in-the-computer-technology-1991/403555123037729] [http://www.ethiopians.com/bayeyima.html] ስለዚህ በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ፊደላት ሲጻፉ የነበሩት በኮምፕዩተር ስለቀረቡ ቴክኖሎጂው ስለተሻሻለና ስለቀለለ ጉዳዩ ይመለከተናል የኣሉት የኦሮሞ ምሁራን ሊደሰቱ የሚገባ እንጂ ወደ ላቲን የሚያስዞር ኣዲስ ምክንያት ኣልነበረም። በጊዜውም በፕሮፌሰር [[ባዬ ይማም]] በዓማርኛ መልስ ቀርቦ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽና ፕሮፌሰር ሳሙኤል ክንዴ ወደ እንግሊዝኛ ተርጕመውታል። [http://www.ethiopians.com/bayeyima.html] ለምሳሌ ያህል ወደ ላቲን የተዞረው ብዙ የግዕዝ ፊደላትን ከማስተማር የኣነሱትን ላቲን ማስተማር ይቀልላል የሚሉ ኣሉ። የላቲኑ ፊደል በቍጥር ማነስ ዕድሜ ልክ እስፔሊንግ ማጥናትንና ኣለመጨረስን ኣስከትሏል። የግዕዝ ፊደላት ቤቶች፣ ቅርጾችና ድምጾች በወጉ የተሠሩ ውብና ግሩም ፈጠራዎች ናቸው። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤት ፊደላትን ድምጾች ለማሰማት ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ሲያስፈልግ በቅርጽ ከግዕዙ የሚለዩት ከቀኝ ጎን መሥመር በማስጨመር ነው። የስምንተኛው ቤት ድምጾች የሚጻፉት ከግዕዙ ወይም ራዕቡ ግርጌ ወይም ኣናት ላይ መስመር በመጨመር ዓይነት ነው። [https://www.facebook.com/notes/403555123037729/] ስለዚህ ኣንድ ሕጻን ከ“ሀ” እስከ “ፐ” የኣሉትን ከተማረ የሌሎቹን ቤቶች ድምጾችና ኣቀጣጠል መማር እንደላቲኑ እስፔሊንግ
ከማስታወስ ይገላግላል። ፬. ላቲን የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው። [http://www.i18nguy.com/twain.html] [http://www.smart-jokes.org/english-spelling-reform.html] [https://www.youtube.com/watch?v=06JhqTexYsM] [https://www.theguardian.com/media/mind-your-language/2014/dec/11/mind-your-language-english-spelling] በዶክተሩ ግኝት እየኣንድኣንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብ ተችሏል። ላቲን ይኸን እየኣንዳንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች የመክተብ ችሎታ ስለሌለው ግዕዝን በግዕዝ ፊደል መክተብ ብልጫ ኣገኘ። ስለዚህ ኦሮምኛን በላቲን ፊደል መክተብ (ቁቤ) መሻሻል ኣይደለም።
 
Anonymous user