ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

218 bytes added ፣ ከ8 ወራት በፊት
ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በዓማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ኢንተርኔት ላይ ብዙ የሉም። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው ኢትዮጵያውያን ፊደላቸውን በመጻፊያ መኪና መሣሪያ (Amharic typewriter / አማርኛ ታይፕራይተር) [http://inventors.about.com/od/tstartinventions/a/Typewriters.htm] ለመጠቀም ተመራምረው ከደረሱበት ዘዴ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል (Ligature) የኢ/ር [[ኣያና ብሩ]] የ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. ገደማ ግኝት ሥራ ላይ ውሏል። [https://www.youtube.com/watch?v=RsyYs333M64&feature=youtu.be] በእዚህ የተነሳ ኢንጂነሩ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ሊቅ ናቸው። ከመቶ በታች መርገጫዎች የኣሉት የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች እንዲብቃቃ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል ኣስፈለገ። “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ኣሉ እንጂ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” እና “ሡ” ስለሌሉ የመቀነስ ምልክትን የመሰለ “-” ከሌላ መርገጫ በመክተብ “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ጎን በማስቀመጥ ቅጥሎቹ ካዕቦቹን ስለሚመስሉ ተመልካቹ እንዲቀበላቸው ሆነ። ኣንዱን መቀጠያ ብዙ ቀለሞች ሊጋሩት ስለሚችሉ የሁሉም ቀለሞች በኣለመኖር የተነሳ መርገጫዎች መቆጠብ ተቻለ። “ሃ” እና “ማ’ እንጂ “ሂ”፣ “ሚ”፣ “ሄ” እና “ሜ” ስለሌሉ “ሃ” እና “ማ” እግሮች ጎን መስመር ወይም ቀለበት በማስቀመጥ እነዚያን በሚመስሉ ቅጥሎች እንድንጠቀም ሆነ። እነ “ቻ”ን የመሰሉ ቀለሞች ከታችና ከላይ ከሁለት መርገጫዎች “ተ” ላይ በሚቀጠሉ ነገሮች ስፍራው ወደኋላ እየተመለሰ ሦስት ነገሮች ኣንድ ፊደል እንዲመስል ተሠሩ። ስፍራ ስለኣነሰ እንደነ “ኳ” ያሉ ቀለሞች “ካ” ስር በተቀመጠ መስመር በሚሠሩ ኣዳዲስ ቀለሞች ተተኩ። የ“ላ”ን ግራ እግር ማሳጠር ስለኣልተቻለ “ለ” ቀኝ እግር ላይ ከመስመር በታች በወረደ መቀጠያ የ“ለ” ቀኝ እግር ረዝሞ ያልተለመደ መልክ ይዞ ቀረበ። በመቀጠል ሊሠሩ ለማይችሉ ቀለሞች የእራሳቸው ስፍራ ሲሰጣቸው ቦታ ስለኣልበቃ ካልገቡት መካከል የዓማርኛ ኣራት ነጥብ ኣሉበት። [http://www.quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf] ስለዚህ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና የተመረኮዘውና ኣከታተቡ የተንፏቀቀ ፊደል በኣንድ የእንግሊዝኛ ገበታ ምትክ መቀጠል ላይ ነው። የዓማርኛ ቀለም ግን እየኣንድኣንዱ እራሱን የቻለ ስለሆነና ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለማይበቃው የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደል ዓማርኛ ኣይደለም። [http://sirius-c.ncat.edu/EAS/news/EJSciTech/abera2.html] [http://web.archive.org/web/20170505120629/http://sirius-c.ncat.edu/EAS/news/EJSciTech/abera2.html] ፊደላት ለኮምፕዩተር ሲሠሩ ተለያይተው እንዲቀርቡ ሲደረግ የታይፕራይተሮቹ ግን እንዲነካኩ ተንፏቅቀው የተሠሩ ስለሆኑ ቦታዎቻቸውን የኣልጠበቁም ናቸው። ይህ ሁሉ ሲደረግ እንደእነ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የመሳሰሉት ሲጠቀሙ የነበሩት በትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች ነበር።
 
የዓማርኛ ፊደል የመክተቢያ ገበታና ዘዴ ስለ ኣልነበሩት ዶክተሩ ፊደሉን ወደ ኮምፕዩተር ሲያስገቡ ዘዴዎቹን ለመጀሪያ ጊዜ ከመፍጠር ሌላ [http://mezmur.altervista.org/%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B/] የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቅጥልጥል ፊደልና ኣከታተቡ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ጽፈዋል። [https://www.facebook.com/notes/403555123037729/] የአማርኛ ታይፕራይተርም ሆነ ዘዴውን ኮምፕዩተራዝ ያደረጉት ሥራዎች በዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራዝ ማድረግ የተነሳ ኣብቅቶላቸዋል። ኣንዳንዶቹም የቆዩና ኣዳዲስ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
 
፩ኛ. የዓማርኛ ፊደላት ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ዓማርኛ ያልሆኑ ፊደላት መኖር ዋጋ የለውም። በእንግሊዝኛው የጽሕፈት መኪና በዓማርኛ ለመጠቀም የተሠራው ዘዴ ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂ ነው። እንኳን ዓማርኛውን የማይጽፍ የጽሕፈት መኪና በሚገባ እንግሊዝኛውን የሚጽፈው የእንግሊኛ የጽሕፈት መኪና ዋጋ ኣጥቶ ሙዚየም ገብቷል። ስለዚህ የኮምፕዩተር ኣከታተብ ማሰልጠኛዎች የኣማርኛ ታይፕራይተር ኣከታተብ ማስተማር መተው ይጠበቅባቸዋል። ፪ኛ. የእንግሊዝኛው የመጻፊያ መኪና የተሠራው ለእየኣንድኣንዱ የላቲን ፊደል መክተቢያና የመርገጫ ስም በመመደብ ሲሆን የዓማርኛው የመጻፊያ መኪና እነዚያን የሉትም። ዶክተሩ ለግዕዙ መክተቢያና የመርገጫ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኮምፕዩተር ፈጥረውለታል። ፫ኛ. የዓማርኛ የመኪና ፊደላት የሚሠሩት ለተወሰነ መጠን ተስተካክለው ወረቀት ላይ እንዲሰፍሩ ነው። በኮምፕዩተር ግን ኣንዱን መጠን መጨመርና መቀነስ ይቻላል። የመኪና ፊደላት ቁርጥራጮች መጠን ሲለወጥ ቅጥሎቹ ይደበቃሉ ወይም ክፍተታቸው ይጨምራል። የገጹ ስፋት ሲጠ'ብ ወይም ሲሰፋ ቅጥሎቹ ብቻቸውን ወደ ኣዲስ መስመር ሊዞሩ ይችላሉ። ቅጥሎቹ ስለሚበጣጠሱ ማሕተምን የመሳሰሉ ነገሮች ኣያሠሩም። ስለዚህ ቅጥልጥል የመኪና ቀለሞች የትክክለኛው ፊደል ተጠጊ እንጂ እራሳቸውን ችለው ሁሉንም ሥራዎች ስለማያሠሩ ኣስፈላጊ ኣይደሉም ብለው ዶክተሩ ጽፈዋል። በቅጥሎች ተንቀሳቃሽ የሚገላበጡ የሲኒማ፣ ቴሌቪዥና ቪድዮ ፊደላት ሊሠሩባቸው ኣይችልም። ፬ኛ. የላቲኑ የመጻፊያ መኪና እየኣንድኣንዱን ቀለም የሚከትበው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን የዓማርኛው መኪና ከእዚያ በላይ መርጫዎችን ይጠይቃል። ስለዚህ ዓማርኛ ሳያስጽፍ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት በሚያስፈልግ ዘዴ ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ከቀረበ ከ፴ ዓመታት በኋላ ዛሬም በ፳፻፱ ዓ.ም. መቀጣጠል ጥቅም የለውም። [http://www.youtube.com/watch?v=CMQYuhaAKH4] በ[[ኣብሻ]] ሥርዓት የተከተበውን ትክክለኛ ቀለም ለመሰረዝም ኣንድ መርገጫ በቂ ነው። ለኣስቀጣይና ተቀጣይ ግን ኣንድ መሰረዣ በቂ ኣይደለም።
 
Anonymous user