ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

326 bytes added ፣ ከ8 ወራት በፊት
፲፫. “ው”ን አንጂ “ዉ”ን የሚጠቀሙ ብዙ የዓማርኛ ቃላት የሉም። በቅርቡ ግን በኣለማወቅ በ“ው” ቀለም ምትክ “ዉ”ን በግድፈት የሚጠቀሙ ፀሓፊዎች እየበዙ ነውና ቢታሰብበት ኣይከፋም። [[መዝገበ ቃላት]]ም ጠቃሚዎች ናቸው። ([[እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት 1972]])። “ው”ን በትክክል ከ40 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [http://www.dejeselam.org/2014/03/blog-post_29.html] “ው”ን በስሕተት ከ400 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [https://hornaffairs.com/am/2017/01/24/committed-leadership-corruption/] ፲፬. የግዕዙ “ሀ” ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ነው። “አ” እና “ኣ” ድምጽ ኣይጋሩም። [http://www.ethiopic.com/amharic/errors.pdf] [http://web.archive.org/web/20030315142841/] [http://web.archive.org/web/20120111013212/http://www.ethiopic.com/ethiopic_alphabet.htm] [http://dagmawibelete.blogspot.com/2013/05/ethiopic.html] ፲፭. ኣንዳንድ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ (“፣”) ምትክ ኮማ (“,”) (Comma) በኣራት ነጥብ (“።”) ምትክ ፔርየድ (“.”) (Period) መጠቀም ስለጀመሩ ፊደሉንና ቋንቋውን እያበላሿቸው ናቸው። ፲፭. ኣንዳንድ ምሁራን ስለማያስተውሉ ሁሉንም የዓማርኛ ቃላት መክተብ በማይችሉ እየተጠቀሙ የሚያወሩትን መጻፍ ኣይችሉም። የግዕዝ ፊደል ታዋቂነት የኣለ እስፔሊንግ ስሕተት ድምጽን በማስፈር ትክክክለኛ ድምፃዊ ፊደል መሆኑ ነው። ፲፮. ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። (Typing any Ethiopic glyph with three keystrokes is a waste of time and effort.) ምክንያቱም የዶክተሩ ኣሠራር እንግሊዝኛውን ከኣጋጠመው ችግር ጭምር ለማላቀቅ እንጂ ለግዕዙ የእንግሊዝኛውን ችግር ለማካፈል ስለኣልሆነ ነው። ፲፯. ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች የተሳሳቱ ቅርጾች ያሏቸውን ቀለሞች እየተጠቀሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የ“ኩ” እና የ“ቡ” መቀጠያዎች ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ የኣሉ ፊደላት የተሳሳቱ ከሆኑ መሳሳቱ ስለማይታወቅ የተሳሳቱ ቀለሞች ተለምደው መቸገርና ማስቸገር ኣይቀርም። እነ “ቋ”፣ “ኋ”፣ “ኳ” እና “ጓ” እራሳቸውን የቻሉ መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች እንጂ እነ “ቀ”፣ “ኃ”፣ “ካ” እና “ጋ” ስር በተጋደሙ መስመሮች የሚቀርቡ ኣዳዲስ የታይፕራይተር የእውሸት ፈጠራዎች ተቀጣጥለው እንደ ኣዳዲስ ቀለሞች ማቅረብ ተገቢ ኣይደለም። የ"የ”ን እንዚራን መለየት ለኣቃታቸው ኣንድኣንድ ምሁራን የኣሌሉ ቀለሞችን መልኮች ማስተዋወቅ ኣይበጅም። [http://www.danielkibret.com/2013/11/blog-post_29.html] ስለዚህ የግዕዝን ፊደል ከመለገስ መለየቱ ቢቀድም ሳይሻል ኣይቀርም። ፲፰. መስከረምና ሰፕቴምበር ብዙ ቀናት ይጋራሉ እንጂ ኣንድ ኣይደሉም። መስከረም 1 ሰፕቴምበር 1 ወይም September 1 ኣይደለም። ፲፱. ሁለት ዓመታት ወይም ዓመቶች እንጂ ሁለት ዓመት በማለት መጻፍ ስሕተት ነው። ፳. በግዕዝ ጽሑፍ ውስጥ ኣራት ነጥብና የመሳሰሉት (በቀለማት እንጂ) በባዶ ስፍራ መቀደም የለባቸውም። ምክንያቱም ግዕዝ ከእጅ ጽሑፍና የማተሚያ ቤቶች [https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/e/e3/Tsehai_mesfin.pdf] ኣጠቃቀም ወደ ኮምፕዩተር ሲሻሻል መለ'የት የሚገባቸውን ዶክተሩ ስለኣቀረቡ ነው።
 
፳፩. የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን የግዕዙን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል። ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱ"ን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የኦሮምኛው ፊደል የዶክተሩ ሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲትና ሌሎች ፕሮግራሞች ውስጥ ቀርበው የሚፈልጓቸው ተጠቅመውባቸዋል። ፳፪. ሁሉንም ቀለማት የሌሉት ወይም የማይከትቡ ዓማርኛ እየተባሉ ሲቀርቡ ኣለተቃውሞ መቀበል ነውር ነው። ምክንያቱም ይህ ለፊደሉና ለሰዋሰው የኣለመጨነቅን ስለሚያሳይ የፀሓፊዎችን ችሎታ ጥያቄ ውስጥ ስለሚያስገባ ነው። ፳፫. ዓማርኛ “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” የሚለውን በማጥበቅ መለየት ኣይችልም የሚሉ ኣሉ። [http://www.ethiomedia.com/1012pieces/oromiffa_in_geez_part_two.pdf] [https://www.youtube.com/watch?v=spzKJUn-KWY] “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” ሁለት ትርጕሞች ያሏቸው ቃላት እንጂ በማጥበቅ የሚለዩ ኣይደሉም። በማጥበቂያ ምልክት የሚለዩ ቃላት ምሳሌ መደመርና መደ'መር ናቸው። ፳፬. በኮምፕዩተር ሁለት ነጥብ “፡” የግዕዝ የባዶ ስፍራን ምልክት ነጥብ በሌለው የባዶ ስፍራ የእንግሊዝኛው ኣጠቃቀም ጋር ደርበው ዓማርኛውን የሚያቀርቡ ኣሉ። ከሁለቱ ዘዴዎች ኣንዱን መምረጥ እንጂ ሁለቱንም መውደድ ኣያዋጣም።
 
፳፭. ኣንዳንድ ሰዎች ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል (Amharic Alphabet) የኣለው ቋንቋ ነው። [https://en.wikipedia.org/wiki/Ge%27ez_script] የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። ግዕዝ (Ge'ez) ወይም Ethiopic የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ፳፮. የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የእውሸት (Fake) ወይም የፈጠራ የዓማርኛ ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ትክክለኛ ቀለሞች ነበር። መጽሓፍት በብራናም ይሁን ሕዝቡ በእጁ ሲጽፍ የነበረው በግዕዝ ፊደል እንጂ በኣማርኛ ታይፕራይተር ፊደል ኣልነበረም። ኣሁንም ቢሆን በድሮው ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት መነሻው ይህ ፊደል በሆነው የዩኒኮድ የግዕዝ ፊደል ዓይነት ነው። [http://unicode.org/charts/PDF/U1200.pdf] የታይፕራይተርንና የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። ፳፰. በወልጋዳ፣ የተሳሳቱና ከሲታ ቀለማት ተጽፈው የሚቀርቡ ጽሑፎችና መጻሕፍት እየበዙ ነው። የፊደል መልክ ከኣላማረ ለማንበብም ኣያጓጓም። ጥሩ የግዕዝ ፊደል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “ነጋሪት ጋዜጣ”ን ሲያትምበት የነበረው ፊደል ነው። ብዙ መጻሕፍትም ታትመውበታል። [https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%8B%B0%E1%89%A5:%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB_%E1%8C%B8%E1%88%93%E1%8D%8A%E1%8B%8E%E1%89%BD]
 
፳፱. ግዕዝ ኮምፕዩተራይድ ስለሆነ በኮምፕዩተር የሚቀርቡት በዓለም ዙሪያ ሊታዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ኣሉ። ግዕዝ ድምጻዊ ስለሆነ የተለያዩ ቋንቋዎችን ያስከትባል። እንግሊዝኛ ውስጥ የኣሉ ኣንድኣንድ ችግሮችም የሉትም። [https://www.youtube.com/watch?v=06JhqTexYsM] ፴. ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ሆኗል። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ያካስራል። ይህ የእጅ ስልኮችንም (Smartphones) ኣጠቃቀም ይመለከታል። ፴፩. ከላይ የተጠቀሱት ስሕተቶች ጥቂቶቹ ትግርኛንም ያጠቃልላሉ። ፴፪. ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ቀርቧል። ወጉንና ሕጉን ጠብቆ መጠቀም የእራስንና የፈጣሪዎችን መብት መጠበቅ ነው። በተሰረቁ፣ በማይጽፉና የኣልተሟሉ ሶፍትዌሮች መጠቀም ለእራስና ለሌላው መብት ኣለመጨነቅን ያሳያል። ለጽሑፍ ጥቅም የሚያስፈልጉ ነፃ ሶፍትዌሮች ስለኣሉ ከእንደግዕዝኤዲት ዓይነት በስተቀር መግዛት ግዴታ ኣይደለም።
 
፴፫. ትክክለኛ ሰዋስው፣ የተሟሉ ቀለሞች፣ ትክክለኛ ቅርጾች እና የመሳሰሉትን በኣሌላቸው መጠቀም ለቋንቋው መዳከም ምክንያቶች እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ኣስፈላጊዎች ናቸው። ስሕተቶች ሲደጋገሙ ሊለመዱ ይችላል። [https://www.facebook.com/getatchew.haile?hc_ref=ARRFkxIO467tAUBLSXTt7knkXxVL2anC-a6g_DTbwgxos8h3IbXzLdfI1m-Pb68lCJ8&fref=nf] ዶክተሩ ከሰዋስው ተሳሳቶች ኣንዱ ናቸው። ፴፬. ስለ ግዕዝና ዓማርኛ ፊደላት ሲጻፍ ስለ ግዕዝ ቋንቋ የሚመስሏቸው ኣሉና ይታሰብበት። ፴፭. ፊደላችን ለኣፍሪቃውያንና ሌሎችም እንዲተርፍ በወጉ መጠቀምና መንከባከብ ይጠቅማል። [https://ethiopianreporter.com/content/%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D-%E1%89%81%E1%8C%AD%E1%89%B5/] ፴፮. "ዓማርኛ" በግዕዙ "ዐ" የማይጻ'ፈው ቀለሙ ድምጹን ስለማይወክል ነው።
 
፴፯. ብዙ ስሕተቶችና ግድፈቶች የኣሉትን ጽሑፍ በዋቢነት ለመጠቀም ኣያስተማምንም። ምክንያቱም ደራሲው ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ኣለማድረጉን ስለሚያሳይ ኣለመግዛት ወይም መተቸት ሳይሻል ኣይቀርም። ለምሳሌ ያህል "ነው" እና "ነህ" የመሳሰሉትን ቃላት "ነዉ" እና "ነክ" የሚሉ ኣሉ። "ኢትዮጵያ"ን በትክክል መጻፍ የማይችሉ ፊደል በሚገባ ኣልቈጠሩም ወይም ረስተዋል ማለት ኣይደለምን? ፴፰. የኣንድኣንዶቹ ስሕተቶች ምንጮች ኣዳዲሶቹ ማተሚያ ቤቶች ናቸው። ለምሳሌ ያህል ቀደም የኣሉ ጽሑፎች ውስጥ የ"ፏ" ፊደል መስመሩ የኣለው ከላይ ሆኖ ሳለ የኣዳዲሶቹ ከታች ነው። ቀደም የኣለውን ምልክት ዶክተሩ ሲጠቀምሲጠቀሙ የተሳሳቱ የሚመስሏቸው ኣሉ። ይኸንኑ መቀጠያ ከግዕዝ ወግ ውጪ "ፍ" ላይ ተደርጎ በቅርቡ የቀረበ ፊደልም ኣለ። ማተሚያ ቤቶች በትክክለኛዎቹ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙ ስለሆኑ መሪዎች እንጂ ተከታይ መሆን የለባቸውም። ፴፰. ዓማርኛ ማጥበቅያ ኣይችልም የሚሉ ኣሉ። በዓማርኛ ፊደል ሲደረብ እንደእንግሊዝኛው ኣይጠብቅም። [https://en.wikipedia.org/wiki/Amharic] ፴፱. ኣንዳንድ የዓማርኛ ተጠቃሚዎች ዓማርኛ ሞክሼዎሞክሼዎች ጽምጾች የሉትም የሚሉ ኣሉ። "ኣባይ"ና "ዓባይ" ኣንድ ኣለመሆናቸው ለመሣሣታቸው ምስክሮች ናቸው።
 
===ሞክሼ ኆኄያት===
Anonymous user