ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 486፦
፲፯. በተሳሳተ ፊደል የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [https://www.cdc.gov/anthrax/pdf/evergreen-pdfs/anthrax-evergreen-content-amharic-508.pdf] ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾች ኮፒ ተደርገው http://www.freetyping.geezedit.com ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ፲፰. ኣንድ ቆንጆ የቁም ፊደል አጣጣል እዚህ ኣለ። [https://www.youtube.com/watch?v=L3iXWW9eJ1Y] ፲፱. በግዕዝ ፊደል ወግ ስምንተኛው ፊደል የሚቀርበው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ነው ። "ፏ" የተሠራው መስመሩን "ፋ" ኣንገት ላይ በመጨመር ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙዎቹ ቅጣዩን በስሕተት ከታች ሲያቀርቡ ኣንዱ በቅርቡ "ፍ" ላይ ኣድርጎታል። መሳሳታቸውን ከቆዩ ጽሑፎች ውስጥ ማየት ይቻላል። እንዲህ ዓይነቶችን ስሕተቶች ስር ሳይሰዱ ማረም ከኣልተቻለ ዛሬ "ኣበበ"ን እሞታታለሁ እንጂ በ"አበበ" ከኣልሆነ ኣልጽፍም እንደሚሉት ጥቂቶቹ በኋላ በትምህርት ማቃናት ሊያስቸግር ይችላል። ፳. ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ኣንድ ኣብሮት የኣለ የእንግሊዝኛ ፊደል ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ ለሰው የሚቀርበው የላቲን ፊደልም እንደግዕዙ የፊደል ሠሪው መሆን ይገባዋል። የግዕዙና የላቲኑም ፊደላት ቅርጾች የተቀራረቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
 
፳፩. ዩኒኮድ ለፊደላቱ መደብ ሰጠ እንጂ ፊደል ኣላቀረበም። የግዕዙ ፊደል ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ ከሌለ የግዕዝ ፊደል ኣይታይም። የሚታየውም እንደፊደሉ ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ ኣንድ ተጠቃሚ የሚጠቀምበትን መሣሪያ ላይ ያለውን የፊደል ስምና መልክ ማወቅ ኣለበት። ፳፪. ኣንድ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ቅርጾች ማወቅ ይጠበቅበታል። በኣሁኑ ጊዜ ግን ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን የማይለዩ ኣሉ። ፳፫. ከእዚህ በፊት ተዉ እያልናቸው በታይፕራይተር ዓይነት ፊደል ተታልለው መጽሓፍት ሲጽፉ ከርመው የተበሳጩ ኣሉ። ኣሁንም በተሣሣቱ የዩኒኮድ ፊደሎችና የዓማርኛ መጻፊያዎች እየተጠቀሙ እራሳቸውንና ዓማርኛውን እየጎዱ የኣሉ ኣሉና ይታሰብበት።
 
===ትርጕሞች===