ከ«ቅዱስ ሩፋኤል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
መስመር፡ 33፦
 
፲፩ ፤ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኛት ልዩ ስጦታ ላለው ለሩፋኤል ሰላም እላለሁ ደዌ ኃጢያትን ይፈውሳል ቁስለ ነፍስንም ያክማልና ። ስለዚህም እውነትን የሚከተሉ ይቅርታን ያገኛሉ ። በተንኮል ጎዳና የሚግዋዙ ግን በነፍሳቸውም በሥጋቸውም ጥፋትን ያስከትላሉ ሲል ለ[[ጦቢት]] አስረዳው አስገነዘበው ።
== ድርሳነ ሩፋኤል ክፍል ፪ ==
 
፲፪ ፤ አባ ዮሐንስ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የክብሩ ዜና ዳግምኛም የቁስጥንጥንያው አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ይህን የገናናነቱን ነገር ተናገረ፣
ደገኛውን ንጉሥ አኖሬዎስን አንዲህ አለው ንጉሥ ሆይ ዕወቅ እኛ ወደ አንተ ልንመጣ በመረከብ ተሳፍረን ነበርና ስንሔድ ሳለን በከበረች በቀዳሚት ቀን በደሴት ላይ የተሰራች አንዲት ቤተ ክርስቲያን አየን። ከወደቡ ደረስን በዕለተ እሑድም ሥጋውን ደሙን እንቀበል ዘንድ ከዚያ አደርን ። በዚች ቤተ ክርስቲያን አጠገብም ትንሽ ገዳም አገኘን ። በውስጧም መነኮሳት አሉ ። ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ እነሱ ደረስን ። መነኮሳቱንም ከቀደሙት ሰዎች ዘመን የተላለፈ ብሉይ መጽሐፍ ከእናንተ ዘንድ እንደ አለ እመከርበት ዘንድ ስጡኝ አልኳቸው ። አንሆ በቤተ ክርስቲያን ብዙ መጻሕፍት አሉ ትርጓሜያቸውን ግን እኛ አናውቅም ብለው መለሱልኝ ።